Yebbo Communication Network | yebbo.com

Saturday, October 22, 2016

Ethiopian Live Broadcasting

Ethiopia Announces Restrictions Under State of Emergency (English and Amharic Version)

ክፍል አንድ


የተከለከሉ ተግባራት


ንዑስ ክፍል አንድ
በማንኛውም የሀገሪቱ ክፍሎች የተከለከሉ ተግባራት
አንቀፅ 1. ሁከትና ብጥብጥ የሚያስነሳ ቅስቀሳና ግንኙነት ማድረግ
ማንኛውም ሁከት፣ ብጥብጥና በህዝቦች መካከል መጠራጠርና መቃቃር የሚፈጥር፣ ይፋዊም ሆነ ድብቅ ቅስቀሳ በማናቸውም መልኩና ዘዴ ማድረግ፣ፅሁፍ ማዘጋጀት፣ ማተምና ማሰራጨት፣ ትእይንት ማሳየት፣ በምልክት መግለፅ ወይም መልእክትን በማናቸውም ሌላ መንገድ ለህዝብ ይፋ ማድረግ፣ፍቃድ ሳይኖር ማንኛውንም ህትመት ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ወይም ወደ ውጪ ሀገር መላክ፤ መልእክት በኢንተርኔት፣ በሞባይል፣ በፅሁፍ፣በቴሌቭዥን፣ በፌድዮ፣ በማህበራዊ ሚድያ ወይም ሌሎች የግንኙነት ዘዴዎች መለዋወጥ።

አንቀፅ 2. ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ማድረግ
በሽብር ከተሰየሙ ድርጅቶች እና ከፀረ ሰላም ቡድኖች ጋር ማናቸውንም ግንኙነት ማድረግ፣ የአሽባሪ ድርጅቶችን የተለያዩ ፅሁፎች መያዝማሰራጨት፣ አርማቸውን መያዝ ወይም ማስተዋወቅ፣ የቴሌቪዥን ወይም የሬድዮ ፕሮግራምን መከታተል፣ የኢሳት፣ የኦ.ኤም.ኤን. እና የመሳሰሉትንየሽብርተኛ ድርጅቶች ሚዲያዎችን ማሳየት፣ መከታተልና ሪፖርት ማድረግ የተከለከለ ነው።

አንቀፅ 3. ያልተፈቀደ ሰልፍና የአደባባይ ስብሰባ
የህዝብና የዜጎች ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ሲባል ከኮማንድ ፓስቱ ፈቃድ ውጭ ማናቸውም ሰልፍና የአደባባይ ስብሰባ ማድረግ የተከለከለ ነው።

አንቀፅ 4. ለህዝብ አገልግሎት አለመስጠት
(1)
ህዝብ የሚጠቀምባቸውን ወይም ፈቃድ የወጣባቸው የንግድ ስራዎች፣ ሱቆች ወይም የመንግስት ተቋማት መዝጋት ወይም ምርትና አገልግሎትማቋረጥ፣ ከስራ ቦታ ያለ በቂ ምክንያት መጥፋት ወይም ስራ ማቆም፣ ተገቢውን አገልግሎት አለመስጠት፣ ስራን መበደል፣
(2)
የመንግስት ወይም የግል ተቋማት ሰራተኞች ወደ መደበኛ ስራቸው እንዳይገቡ መዛትና ማስፈራራት የተከለከለ ነው።

አንቀፅ 5. በትምህርት ተቋማት አድማ ማድረግ
በትምህርት ቤቶች፣ በዩኒቨርስቲዎች እና በሌሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደትን የሚያውክ አድማ ማድረግ፣ የትምህርትተቋማትን መዝጋት ወይም በነዚህ ተቋማት ላይ ጉዳት ማድረግ የተከለከለ ነው።

አንቀፅ 6. በስፖርት ማዘውተሪያዎች አድማ ማድረግ
በስፖርት ማዘውተሪያ ማእከላት ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ የሆኑ ሁከቶችን፣ ብጥብጦችን መፍጠር የተከለከለ ነው።

አንቀፅ 7. የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ማወክ
የተሽከርካሪ፣ የእግረኛ እና ሌሎች የመጓጓዣ ዘዴዎችን እንቅስቃሴ መንገድ በመዝጋት በዛቻ እና በሌሎች መሰል ድርጊቶች ሰላማዊ እንቅሰቃሴንማወክ፣ አገልግሎት ማስተጓጎል፣ የመጓጓዣ ዋጋ ታሪፍ መጨመር፣ የሚመለከተው አካል ከደለደለው የስራ ስምሪት ውጪ መሆን የተከለከለ ነው።

አንቀፅ 8.በመሰረተ ልማቶችና ሃይማኖታዊ ተቋማት ላይ ጉዳት ማድረስ
በግል በህዝብና በመንግስት ማናቸውም ተቋማት፣ በመሰረተ ልማት፣ በኢንቨስትመንትና በሌሎች የልማት አውታሮች እንዲሁም በሃይማኖታዊተቋማት ላይ በማንኛውም መንገድ ጉዳት ማድረስ ወይም ዘረፋ መፈፀም የተከለከለ ነው።

አንቀፅ 9. ህዝባዊና ብሄራዊ በዓላትን ማወክ
ህዝባዊና ብሄራዊ በዓላትን በማንኛውም ሁኔታ ማወክ፣ ማደናቀፍ ወይም ከበዓሉ አላማ ጋር የማይገናኙ የፖለቲካ አጀንዳዎች ወይም መፈክሮችንበማንኛውም መንገድ ማስተጋባት የተከለከለ ነው።

አንቀፅ 10. ሀይማኖታዊ፣ ባህላዊና ህዝባዊ በዓላት ላይ ቅስቀሳ ማድረግ
ሀይማኖታዊ ተቋማት ውስጥ በሚደረጉ ስብከቶችና ትምህርቶች ሀይማኖታዊ አስተምህሮት ከማድረግ ውጪ በህዝቦች መካከል መጠራጠርናመቃቃርን የሚፈጥር፣ በህብረተሰቡ ላይ ስጋት የሚፈጥር፣ ሁከትና ብጥብጥ የሚቀሰቅስ ቅስቀሳ ማድረግ የተከለከለ ነው።

አንቀፅ 11. የህግ አስከባሪዎችን ስራ ማወክ
የህግ አስከባሪ አካላት የሚሰጡትን ማንኛውም ትዕዛዝ አለማክበር ስራቸውን ማደናቀፍ፣ ለፍተሻ አለመተባበር ወይም እንዲቆም ሲጠየቅ አለማቆም፣ኬላዎችን ጥሶ ማለፍ የተከለከለ ነው፡፡ በህግ አስከባሪ አካላት ባልደረቦች ላይ ጥቃት መፈፀም ወይም ለመፈፀም መሞከር የተከለከለ ነው፣

አንቀፅ 12. ያተፈቀደ አልባሳት መልበስ
የህግ አስከባሪ ሃይሎችን ዩኒፎርም መልበስ፣ ይዞ መገኘት፣ በቤት ማስቀመጥ፣ አሳልፎ መስጠትና መሸጥ ክልክል ነው።

አንቀፅ 13. የጦር መሳሪያ ይዞ መግባት
ማናቸውም የጦር መሳሪያ፣ ስለት ወይም እሳት የሚያስነሱ ነገሮችን ወደ ገበያ፣ ሀይማኖት ተቋማት፣ ህዝባዊ በአላት የሚከበሩበት ወይም ወደማናቸውም ህዝብ የሚሰበሰብበት ቦታ ይዞ መግባት የተከለከለ ነው።

አንቀፅ 14. ትጥቅን በሶስተኛ ሰው እጅ እንዲገባ ማድረግ
ማንኛውም የህግ አስከባሪ አካላት ባልደረባ ወይም ማንኛውም ህጋዊ ትጥቅ ያለው ሰው ትጥቁን በማንኛውም ሁኔታ በሶስተኛ ሰው እጅ እንዲገባማድረግ ክልክል ነው።

አንቀፅ 15. መቻቻልን እና አንድነትን የሚጎዳ ተግባር መፈፀም
ማንነትን ወይም ዘርን መሰረት ያደረገ ማንኛውም አይነት ጥቃት መፈፀም ወይም ጥቃት እንዲፈፀም የሚያነሳሳ ንግግር መናገር የተከለከለ ነው።አንቀፅ 16. የሀገርን ሉዓላዊነት፣ ደህንነት፣ ህገመንግስታዊ ስርዓት የሚጎዳ ተግባር መፈፀም
ማንኛውም ሰው ከውጭ መንግስታትም ሆነ ከውጭ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር የሀገር ሉአላዊነት፣ ደህንነትና ህገ-መንግስታዊ ስርዓትንሊጎዳ የሚችል ግንኙነትና የመልዕክት ልውውጥ ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ የሀገርን ሉዓአላዊነት፣ ደህንነት እና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን {የሚፃረር} ማናቸውም ጋዜጣዊ መግለጫ ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሚዲያዎች መስጠት ክልክል ነው።

አንቀፅ 17. ያልተፈቀደ ቦታ መገኘት
ከስደተኛ ካምፕ አግባብ ካለው አካል ከሚሰጥ ፈቃድ ውጭ መውጣት ወይም ህጋዊ ቪዛ ሳይኖረው ወደ ሀገር ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው።

አንቀፅ 18. ያለፈቃድ ስለሚደረግ የዲፕሎማቶች እንቅስቃሴ
የኮማንድ ፖስቱ እውቅናና ፈቃድ ሳያገኙ ዲፕሎማቶች ለራሳቸው ደህንነት ጥበቃ ሲባል ከአዲስ አበባ ከአርባ /40/ ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውጪመንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

አንቀፅ 19. የህግ አስከባሪ አካላት ግዳጅ ላይ ስለመገኘት
ማንኛውም የህግ አስከባሪ አካል ባልደረባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተፈፃሚ በሚሆንበት ጊዜ ከስራ መልቀቅ ወይም አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረበስተቀር የአመት እረፍት ፍቃድ መውሰድ ክልክል ነው።

አንቀፅ 20. የህዝብን ሰላምና ፀጥታ ለማደፍረስ ድጋፍ ማድረግ
በዚህ መመሪያ የተከለከሉ ተግባራትን በመተላለፍ ህገ ወጥ ድርጊት የሚፈፅሙ ሰዎችን፣ በገንዘብና በቁሳቁስ ወይም በማናቸውም ሌላ መንገድመደገፍ እንዲሁም ከለላ መስጠት፣ መደለያ መስጠት፣ ማበረታታት የተከለከለ ነው።

ንዑስ ክፍል ሁለት

በተወሰኑ
የሀገሪቱ አካባቢዎች እንዳይፈፀሙ የተከለከሉ ተግባራት
ከላይ በንዑስ ክፍል አንድ የተደነገነገው እንደተጠበቀ ሆኖ ከአንቀፅ 21-24 የተዘረዘሩት ክልከላዎች ኮማንድ ፖስቱ እየወሰነ ይፋ በሚያደረጋቸውቦታዎች ወይም አካባቢዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናሉ።

አንቀፅ 21. የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ
ማናቸውም የጦር መሳሪያ፣ ስለት ወይም እሳት የሚያስነሱ ነገሮችን ከግቢውና ይዞታው ውጪ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

አንቀፅ 22. በልማት አውታሮችና መሰረተ ልማቶች ላይ የሚሰነዘር ጥቃት
የኢኮኖሚ አውታሮች፣ መሰረት ልማትና የኢንቨስትመንት ተቋማት፣ የእርሻ ልማቶች፣ በፋብሪካዎች እና በመሰል ተቋማት አካባቢ ከቀኑ 12 ሰዓትበኋላ እስከ ንጋት 12 ሰአት ድረስ ከተፈቀደለት ሰራተኛ በስተቀር ማንኛውም ሌላ ሰው መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፡፡ ከላይ በተመለከቱት ቦታዎች የሰዓት እላፊውን ተላልፎ በተገኘ ማንኛውም ሰው ላይ የጥበቃ ወይንም የህግ አስከባሪ አካላት አስፈላጊውን እርምጃእንዲወስዱ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል።

ክፍል ሁለት

የተከለከሉ ተግባራት ተፈጽሞ ሲገኝ ስለሚወሰዱ የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎች

አንቀጽ.23. ስለ ሰዓት እላፊ
ማናቸውም ሰው በኮማንድ ፖስቱ ውሳኔ የሰዓት እላፊ በይፋ በሚገለጽበት ቦታና ጊዜ የሰዓት እላፊ ክልከላን በመተላለፍ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስአይፈቀድም፡፡

አንቀጽ 24. ሁከትን ለማስቆምና አደጋን ለመከላከል የሚደረግን እንቅስቃሴ ማወክ
ሰላምና ፀጥታን ሊያደፈርሱ ይችላሉ ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎች ወይም ቡድኖችን ወይም ለጉዳት ተጋላጭ ናቸው ተብለው የሚገመቱ ሰዎችወይም ቡድኖች ወደ ተወሰነ አካባቢ ወይም ህንፃ እንዳይገቡ ወይም በተፈቀደላቸው አንድ የተወሰነ አካባቢ ብቻ እንዲቆዩ የተሰጠውን ትዕዛዝመተላለፍ ክልክል ነው፡፡ ለአካባቢው ደህንነት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ወደ ተዘጋ መንገድ ማንም ሰው እንዳይገባ ኮማንድ ፖስቱ የሰጠውንእግድ ወይም ክልከላ መተላለፍ ክልክል ነው፡፡

ንዑስ ክፍል ሶስት
መረጃ የመስጠትና የማስታወቅ ግዴታ

አንቀጽ 25. የተከራይ መረጃ የመያዝና የመስጠት ግዴታ
ማንኛውም ቤት፡ ቦታ፡ ክፍል ወይም ተሽከርካሪ ወይም ተመሳሳይ መገልገያ አከራይ የሆነ ሰው የተከራዩን ማንነት በዝርዝርና በጹሁፍ የመያዝናበአቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡ በተጨማሪም የውጭ አገር ዜጋን ያከራየ እንደሆነ የፓስፖርቱንኮፒና የኪራዩን ውል በአቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡

አንቀጽ 26. መረጃ የመስጠት ግዴታ
የህዝብ ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ሲባል ማንኛውም ተቋም መረጃ እንዲሰጥ በየደረጃው ባለ የህግ አስከባሪ አካል ሲጠየቅ የመስጠትና የመተባበርግዴታ አለበት። አንቀጽ 27. እርምጃ ለመውሰድ ስልጣን ስላለው ሰው
ከላይ በክፍል አንድ ከአንቀጽ 1- 24 የተመለከቱ የተከለከሉ ተግባራትን ፈጽመው በተገኙ ሰዎችና ድርጅቶች ላይ የህግ አስከባሪዎች እናባልደረቦቻቸው በአዋጁና በዚህ መመሪያ የተዘረዘሩ የሚከተሉትን የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይችላሉ፡፡

አንቀጽ 28. ክልከላዎች ሲጣሱ ስለሚወሰዱ እርምጃዎች
ከላይ በክፍል አንድ የተመለከቱ ክልከላዎችን ተላልፎ በተገኘ ማንኛውም ሰው ላይ የህግ አስከባሪዎች
(1)
ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በቁጥጥር ስር ማዋል፣
(2)
አዋጁ ተፈጻሚነቱ እስከሚያበቃበት ጊዜ ድረስ ኮማንድ ፖስቱ በሚወስነው ቦታ እንዲቆይ ማድረግ፣
(3)
ተገቢውን የተሃድሶ ትምህርት በመስጠት የሚለቀቀውን እንዲለቀቅ፣ ወደ ፍርድ ቤት
የሚቀርበውን ደግሞ እንዲቀርብ ማድረግ፣
(4)
ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማናቸውም ሰዓት ብርበራ ማድረግ፣ የአካባቢውን ህዝብና ፖሊስ በማሳተፍ ማንኛውንም ወንጀል የተፈጸመበት ወይምሊፈጸምበት የሚችል ንብረት መያዝ ወይም ንብረቱ ባለበት እንዲጠበቅ ማድረግ፣
(5)
በማንኛውም ሬድዮ ቴሌቪዥን ጽሁፍ ምስል ፎቶ ግራፍ ቲያትርና ፊልም
የሚተላለፉ መልዕክቶችን መቆጣጠርና መገደብ፣
(6)
የተዘረፉ ንብረቶችን ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመፈተሽ ለባለቤቶቹ እንዲመለሱ ማድረግ፣
(7)
በትምህርት ተቋማት ሁከትና ረብሻ ተሳትፎ በሚያደርጉ ተማሪዎችና ሰራተኞች ላይ
ህጋዊ እርምት መውሰድ፣ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ለተቋማቱ ትዕዛዝ መስጠት፣
(8)
ማንኛውም የህዝብን ሰላምና ጸጥታን ሊያደፈርሱ ይችላሉ ወይም ለጉዳት ተጋላጭ
ይሆናሉ ተብለው የሚጠረጠሩና የሚታሰቡ ሰዎችን ወይም ቡድኖችን ወደ ተወሰነ አካባቢ
እንዳይገቡ፣ እንዳይገኙ ወይም በተወሰነ አካባቢ ብቻ እንዲቆዩ ማድረግ እና
(9)
አግባብነት ያላቸውን እርምጃዎችን መውሰድ ይችላል፡፡

አንቀጽ 29. እራስን ለመከላከል በሕግ አስከባሪዎች ስለሚወሰድ እርምጃ
ሕግ አስከባሪዎችናቀ በድርጅቶች ጥበቃ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ከላይ የተመለከቱትን ክልከላዎች እንዲሁም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸምበሚያደርጉት እንቅስቃሴ በጦር መሳሪያ ወይም በስለትና ሕይወታቸውን እና ንብረታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል ጥቃት በተሰነዘረባቸው ጊዜእራሳቸውን ለመከላከል የሚያስችላቸውን እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ፡፡

አንቀጽ 30. በትምህርት ተቋማት የመግባት ስልጣን
በትምህርት ቤቶች፣ በዩኒቨርስቲዎች እና በሌሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ አድማ የሚያደርጉ ሰዎችን ለመያዝና ችግሩን ለማስቆም የህግአስከባሪ አካላት በእነዚህ ተቋማት ውስጥ በመግባት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ይችላሉ፣ እንዲሁም በሌሎች የግልና የመንግስት ተቋማትውስጥ አድማ የሚያድርጉ ሰዎችን ለመያዝና ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ የሕግ አስከባሪ አካላት ባልደረቦች በእነዚህ ተቋማት ውስጥ ለመግባትእንዲሁም አስፈላጊ ከሆነ ሊቆዩ ይችላሉ፡፡

ክፍል ሶስት
ተሀድሶ እና ፍርድ ቤት ስለማቅረብ

አንቀጽ 31. በሕግ መሰረት በኮማንድ ፖስቱ የሚደረጉ የተሀድሶ እርምጃዎች
(1)
ለፍርድ መቅረብ ያለበትን ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ያደርጋል
(2)
ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በተፈጸሙ ሁከትና የብጥብጥ እንቅስቃሴዎች ላይ በቡድን ወይም በግል የተሳተፈ እና
(
) የጦር መሳሪያ ወይም ማንኛውንም የግልም ሆነ የመንግስት ንብረት የዘረፈ እና በአቅራቢያው ለሚገኝ የህግ አስከባሪ ሀይል የዘረፈውን መሳሪያናንብረት ይህ መመሪያ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ 10 ቀናት ውስጥ በአቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ የመለሰና እጁን የሰጠ ሰው፣
(
) ከዚህ በፊት ለህገ ወጥ ተግባራት የገንዘብና ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገና ይህ መመሪያ በወጣ 10 ቀናት ውስጥ ለፖሊስ ጣቢያ እጁን የሰጠ ሰው፣
(
) ወረቀት በመበተን፣ አድማ በማድረግ የተሳተፈ፣ ያነሳሳ ሰው ይህ መመሪያ በወጣ 10 ቀናት ውስጥ ለፖሊስ ጣቢያ እጁን የሰጠ ሰው፣
(
) ሰው የገደለ፣ ማንኛውንም ንብረት ያቃጠለ፣ ማንኛውንም ወንጀል የፈጸመ ይህ መመሪያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ 10 ቀናት ውስጥ ለፖሊስጣቢያ እጁን የሰጠ ሰው፣
እንደ የወንጀል ተሳትፎው ቀላልና ከባድነት፣ ዋና ፈፃሚና አባሪ ተባባሪ መሆኑ ታይቶ በኮማንድ ፖስቱ የተሀድሶ ትምህርት ተሰጥቶት እንዲለቀቅይደረጋል፡፡
አዲስ አበባ ጥቅምት 5 ቀን 2009 /
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት

PART I: Prohibited Activities
Part 1 A. Activities Prohibited Nationwide
 • Article 1— Agitation and Communication to Incite Violence and Unrest: Covert or overt  agitation and communication that could incite violence and chaos including: printing, preparing and disseminating any content that incites dispute, violence, conflict among people; importing or sending out any publication without prior approval; the exchange of messages via Internet, mobile, text, social media, and radio.
 • Article 2— Communicating with Terrorist Groups: Communicating in any manner with designated terrorist groups or anti-peace forces; storing and disseminating text or storing and promoting emblems of terrorist groups; listening to, watching, or reporting information from Ethiopian Satellite Television, Oromia Media Network, and other terrorist groups outlets is prohibited.
 • Article 3—Unauthorized Demonstrations and Town Hall Meetings: In the interest of protecting the safety and security of citizens, it is prohibited to stage any demonstration and town hall meeting without CP approval.
 • Article 4—Denying the Provision of Public Services: Closing shops and businesses with licenses, or government institutions, or refusing to deliver public services or being absent from work without sufficient reason is prohibited.  Threatening public or private employees from going to work is prohibited.
 • Article 5—Strikes in Educational Institutions: Strikes in any schools, universities, or other higher learning institutions or closing educational institutions or damaging property are prohibited.
 • Article 6—Strikes in Sports Facilities: Inciting unrest, disturbances, and violence in sports venues is prohibited.
 • Article 7—Disrupting Movement of Vehicles: Disrupting the movement of vehicles or pedestrians or other means of transportation by blocking roads or any other means, or increasing transportation fees is prohibited.
 • Article 8—Causing Damage to Infrastructure and Religious Institutions: Causing damage to or looting on private, public, and government property or infrastructure, investments or any other institutions or religious institutions is prohibited.
 • Article 9—Disrupting Public and National Holidays: Disrupting public and national holidays in any way or advancing any political agenda or chanting slogans unrelated to the holiday is prohibited.
 • Article 10—Incitement During Religious, Cultural, and Public Holidays: Inciting in sermons and teachings in religious institutions to induce fear among people or incite conflict is prohibited.
 • Article 11—Disrupting the Functions of Law Enforcement Bodies: Refusing to comply with any order given by law enforcement bodies, disrupting their duties, non-cooperation with searches, or attacking or attempting to attack law enforcement bodies is prohibited.
 • Article 12—Wearing Unauthorized Uniforms: The unauthorized wearing, storing, selling or transferring of official uniforms of law enforcement units is prohibited.
 • Article 13—Firearms or Flammable Materials: Bringing firearms or flammable or sharp materials into market places, religious institutions, or public places is prohibited.
 • Article 14—Transfer of Firearms: Any law enforcement officer or any individual with legally owned firearms is prohibited from transferring the same to a third party.
 • Article 15—Activities That Undermine Tolerance and Unity: Committing acts that undermine tolerance and unity; any attacks based on identity or ethnicity or speech that could incite such attacks is prohibited.
 • Article 16—Undermining National Sovereignty and Security: Any exchange of information or contact by any individual with foreign governments or nongovernmental organizations in a manner that undermines national sovereignty and security; any political party is prohibited from briefing local or foreign journalists in a manner that is anti-constitutional  and undermining sovereignty and security.
 • Article 17—Restricted Areas: Leaving refugee camps without permission from the authorized body or entering the country without visa is prohibited.
 • Article 18—Unauthorized Movement of Diplomats: In the interest of their safety and security, diplomats are prohibited from traveling no farther than 40 km outside of Addis without prior notification to and approval from the CP.
 • Article 19—Duty of Law Enforcement Officers: Any law enforcement officer is prohibited from resigning from their job or take leave during the SOE unless and otherwise forced by a situation.
 • Article 20—Contributing to Public Unrest and Instability: Providing, money, materials, shelter, encouragement, or any other support to those who commit illegal activities is prohibited. 
PART I: Prohibited Activities 
Part1 B. Restrictions in Specific Parts of the Country 
 • Article 21—Mobility with Firearms: Any firearms, sharp materials, or flammable items that could be used as a weapon may not be taken outside one’s home.
 • Article 22— Attacks Targeting Infrastructure and Economic Interests: Unauthorized persons are forbidden to be in the vicinity of economic interests, infrastructure, investments, industrial areas, and commercial farms from 6:00 pm to 6:00 am; law enforcement bodies are authorized to take any necessary actions against violators.
 • Article 23—Curfew: Any individual is not allowed to move from place to place violating curfews imposed by the CP in a specific location and time.
 • Article 24— Disrupting Efforts to Control Violence: It is prohibited to violate orders given to individuals or groups suspected of posing a threat, groups vulnerable to harm (who may be ordered to stay away from certain areas or buildings or to stay within certain areas); it is prohibited to enter a road blocked by the order of CP.
PART I: Prohibited Activities
Part I C. Providing Information and Notifying Authorities 
 • Article 25—Documenting rental units: Any person who rents out a house, room, place, vehicle, or similar item is required to document information about the identity of the renter and should report to police within 24 hours; in the case of a foreign national renter, the owner should make a copy of the passport and rental agreement and must report to a nearby police station. 
 • Article 26—Obligation to provide information: For the safety and security of the public, all organizations are required to give information when asked by law enforcement bodies at all levels.
            PART II: Power To Implement Measures
 • Article 27—Law enforcement bodies are authorized to take emergency action against: Any person or organization that violates prohibitions under articles 1-24.  (Note: it is not clear how the emergency actions are different from those authorized under article 28.)
 • Article 28—Consequences for violations of Part 1 (Articles 1-26): Individuals may be arrested without a court order and may be held at a location determined by the CP for a term up to the end of the SOE; detainees may be eligible for release after completing a rehabilitation program or will face trial based on the severity of their crime; law enforcement or the CP may censor any message transmitted by radio, television, video, text, image, theater, or film that violates the prohibitions listed in Part 1; authorities may confiscate and return to the original owner, any looted property discovered through the search of a suspected violator's house without a court order; authorities may take legal measures or order educational institutions to take measures against any student or staff member who violates the prohibitions in Part 1; any group(s) or individual(s) suspected of posing a threat to public peace and security or individuals or groups assumed to be vulnerable to harm can be prohibited from entering certain areas or may be confined within restricted areas; authorities may take other relevant measures.
 • Article 29—Authorization for law enforcement to exercise self-defense: law enforcement bodies and individuals engaged in protection duties may take any defensive measures necessary if attacked by firearms or sharp materials.
 • Article 30—Authority for law enforcement to enter into educational institutions: Law enforcement bodies may enter schools, universities, and other related institutions and can take measures to control strikes or protests; in addition to educational institutions, authorities may enter and occupy public and private organizations if necessary to arrest and control strikes or protesters.  They may stay inside these institutions whenever necessary.
PART III: Rehabilitation Measures
 • Article 31—Rehabilitation measures: The CP will bring to justice those who deserve it. Individuals or groups who were involved in conducting violence during the last year, upon returning looted property, including government firearms and private property to nearby police stations within 10 days of this announcement may receive rehabilitation as punishment; those who supported illegal activities materially or financially and surrender to the nearby police station within 10 days of this announcement may receive rehabilitation as punishment; anyone who was involved in protest by distributing materials, involved in murder, or destruction of property may turn themselves into police within 10 days of the enactment of this law; the duration of rehabilitation depends on the severity of the crime; individuals may be set free after undergoing rehabilitation programs.  (Note: It remains unclear whether the SOE and accompanying articles have been enacted by decree or must still be approved by parliament.)

Want to Advertize? Let me know

http://www.ethiotrans.com
For daily flight deals and sales to Africa Call 619 255 5530
Wikilina or the Ethiopian Power of Attorney

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or WIKILINA now on sale

Breaking News: Indonesian Jets Force Ethiopian Cargo Plane to Land Over Airspace Breach

የኢንዶኔዥን የአየር ክልል ካለ ፍቃድ አቋርጠሃል በሚል ሰበበ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላን በሁለት የጦር ተዋጊ ጀቶች ታጅቦ በግዴታ  ጃካርታ እንዲያርፍ ተደርጓል።  JAKARTA — Two Indones...