Shop Amazon

Thursday, September 8, 2016

የሽሮና ወጥ እና የወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ተመሳሳይነት

የሽሮና ወጥ እና ቅቱ  የኢትዮጵያ ሁኔታ  ተመሳሳይነት
ሽሮ  ኢትዮጵያ ምግቦች ሁሉ የመጀመሪያው የክፉ ቀን ደራሽ የሆነው፣ ካልሰለቹ በስተቀር  አመቱ ሙሉ ቢባላ ዶክተርም ሆነ በሀይማኖት ያልተከለከለ ታላቅ ምግብ ነው   የሚገርመው ግን ሽሮወች ሁሉ እኩል አልተፈጠሩም። ለስም ሁሉም  ሽሮወች ተመሳሳይ ቢሆኑም ነገር ግን በጣም ብዙ የተለያዩ ሽሮ ወጦች አሉ።

ለምሳሌ  አንዱ አንዱ  ቀጭን፣ አንዱ  በቅቤ አብዶ የተሰራ፣ አልጫ ሽሮ፣ ምጥን ሽሮ፣ ወፍራም  ወይም  ቀጭን ሽሮ የፈ ሽሮ፣ ያልፈላ ሽሮ፣ እና የሁሉም የሽሮ ወጦች  አለቃ ቦዘና ሽሮ ለአብነት ያክል የሚጠቀሱ ናቸው።

 ግን ይህን ሁሉ የተለያየ ሽሮ  አይነትን  ያመጣው የሽሮው ዱቄት ሳይሆን  የባለሙያው የአሰራር ችሎታ እና የጥበብ ልዩነት ነው።
ታዲያ መንግስትም ልክ እንደ ሽሮ አሰራር  ነው። ጥሩ አስተዳደር ጥሩ ሽሮ ወጥን ይፈጥራል ። መጥፎ አስተዳደር ደግሞ ቢበሉት  የሚያቅር፣ ውሃ ውሃ  ወይም  የሚያቃጥል  ሽሮ  ይሆናል ።
 በጣም የሚገርመው ግን ይህ አሁን በአገራችን የማየው ነገር ከሽሮ ወጥ ጋር መመሳሰሉ ነው። ለምን በሉኝ   ነገሩ እንዲህ ነው።
 በሽሮ ወጥ አሰራር ላይ ያሉትን ንጥረ ነገሮች እስኪ  አብረን ንቃኛቸው እና እያንዳንዱን ሂደት ደግሞ  ከኢትዮጵያ  ወቅታዊ   ሁኔታ ጋ አቻ ስያሜ እንስጠ
አንድን ሽሮ ወጥ ለመስራት የሚያስፈልጉ ነገሮች ለምሳሌ ውሃ፣ በርበሬ፣ ሽሮ፣ ጨው፣ ድስት፣ እሳት፣ ቅቤ ወይም ዘይት፣ ሽንኩርት እና የወጥ ማማሳያው ለአብነት ያክል የሚጠቀሱ ነገሮች ናቸው። ታዲያ እነዚህን ነገሮች  ከአገራችን  ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር እናመሳስላቸው። ድስትብ  ከነክዳኑ እንደ አገር  እንደ እማማ ኢትዮጵያ ሮን  ልክ እነደ ህዝብ እሳትን ደግሞ ልክ እነደ መንግስት ወይም  አስተዳደር እና  ሌሎች የቀሩት ደግሞ ልክ እነደ  ህግ እና ድንጋጌ ሲሆኑ ማንኪያውን ደግሞ ልክ እንደ ፖለቲካ እንያቸው።
                                                   
ታዲያ አንድ ሽሮ ጥሩ ሽሮ እንዲሆን በጥሩን ሁኔታ መዘጋጀት አለት። በአይነ ሂሊናችሁ  እስኪ  አንድ  እሳት ላይ የተጣደ  ገና በመብሰል ላይ ያለ ሽሮ ይታያችሁ ይህ ሽሮ ጥሩ ሽሮ ወጥ እንዲሆን ከፈለግን ከታች እሳቱን (መንግስት) እየተቆጣጠርን   ድስቱን (አገር) አንዴ ከፈት አንዴ ዘጋ እያደረግን በማማሰያ (ፖለቲካ) ቀስ እያልን ሸሮውን (ህዝቡን) እናስተዳድራለን። ነገር ከታች ያለው እሳት (መንግስት) ከሚገባው በላይ ከነደደ ሽሮ (ህዝብ) ይፈላና ቶሎ ብለን መላ ካልሰጠነው ቱግ ብሎ የደፋል። ዲያ በንዴት የወጣው ሽሮ ቶሎ ብለን እሳቱን ካልቀነስነው የድስቱ (አገር) ክዳን እንኳብ ሳይቀ ገልብጦት የደፋል
ዲያ አሁን ያለው የሀገራችን እሳት ልክ እንደ ሽሮ ወጡ ማብሰያ እሳት ነው። ዝም ብሎ ጫናውንና እንግልቱን ከጨመሩበት (እሳቱ) ማለት ነው። ህዝብ ከገነፈለ ማቆሚያው ከባድ ነው። አንዳንድ ሽሮ ከገነፈለ እራሱ እሳቱን ያጠፋዋል
  የሆነች የወጥ ሰራተኛ ግን ሽሮውን ቀስ እያለች እሳቱን (የመንግስት ) እየቀነሰች፣ በማማሰያው እያማሰለች ቀስ ብላ ቆንጆ ያበደ ሽሮ ትሰራለች። ታዲያ ከሽሮ የምንረዳው ታላቅ ነገር
 ሽሮ ቆንጆ የሽሮ ወጥ የሚሆ ጎበ የሽሮ ሰሪ (መሪ) ኖር ነው። ነገር ግን ዝም ብሎ ሽሮውን በድስቱ (አገር ) አፍኖ እሳቱን(መንግስት) ቢጨምሩበት ሽሮ ጭንቅ ስለማይ የድስቱን ክዳን ከፍቶ ይገነፍል እራሱ ሽሮውን  የሚያበስለውን እሳት (መንግስት) ያጠፋዋል።  ታዲያ ጥሩ ለመብላት እሳቱ ቀነስ፣ ዘናና ለቀቅ ማድረጉ ለሁሉም ይበጅል
 አለበዚያ ሽሮውን በእሳት ትርፉ  ሽሮው ገንፍሎ እራሱን መንግስቱን (እሳቱን) ያጠፋዋል። ሽሮው  ገንፍሎ  እሳቱ  አልጠፋ ካለ ሽሮው ይጎረና እና ሳይበላ  ይቀራል
ጠንቀቅ  ነው። ሽሮን  ቆንጆ  ሽሮ  የሚያደርገው ጎበዝ ባላሙያ ነው። ሀገርንም ጥሩ  አገር  የሚያደርገው መልካም  መሪ  ነው ::

አመሰግናለሁ
ለኢትዮጵያ አስተዋይ  መሪ ይስጣት