READ THIS
የቃላት ግድፈት ካያችሁ ገና በመስተካካል ላይ ነው። አማርኛ ታይፕ በጣ ም ከባድ ነው
የአሜሪካ የትራንስፖርቴሽን ንግድ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአበሻን ማህበረሰብ ሂወት ይዳስሳል። የታክሲን ስራ የገቢ ሚስጢሩን አቶ ኡበር(UBER) ግልጥልጥ አድርጎ ይፋ በማድረግ ለአለም ህዝብ እስከሚያስተዋውቀው ድረስ የታክሲ ስራ ከዶክተር እና ከኢንጅነሪንግ ስራ ጋር በገቢ አይተናነስም በማለት ስንት ይደርሳሉ የተባሉ ልጆች የታክሲን ስራ በመተማመን ትምህረታቸውን ወደ ጎን ጥለው ዳጎስ ያለ ገቢ ያገኙ ነበር። አሁንም ቢሆን ብዚም ባይሆንም ትንሽ አለ ። ድሮ የታክሲ ስራ በጣም የሚያዋጣ አለቃ የሌለበት በነጻነት የሚሰራ በዚያው ልክ ደግሞ ጥሩ ገቢ ያሚያስገኝ ስራ ነበር። በታክሲ ስራ ስንቶች ሚሊየነር ሆነዋል፣ስንቶች ባለ ንብረት ሆነዋል፣ስንቶች ወገኖቻቸውን እረድተዋል ፣ስንቶች ልጆቻቸውን አሳድገው ዩኒቨርስቲ ልከዋል። ነገር ግን ከትንሽ አመታት በፊት እንደ ሱናሜ (TSUNAMI) ከተፍ ያለው UBER ሁሉንም ነገር ዘጭ አድርጎት ትናንት ከ $150 000 ዶላር በላይ ይሸጥ የነበረው የታክሲ ፈቃድ ዛሬ በ $3000 እንኳ የሚነካው ጠፍቷል ።
መድሃኒቱ ከባድም ቀላልም ነው። መድሀኒቱ እንደ እድሜያችሁ እና እንዳላችሁ የትምህርት ደረጃ እንዲሁም እንደ ቤተሰባችሁ ብዛት ይለያያል ። እንደ አሜሪካው የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይም (DEPARTMENT OF LABOR) በአሜሪካ ውስጥ ከ 65ሺ በላይ የስራ አይነቶች አሉ (የስራ ብዛቶች አላልሁም) ነገር ግን አብዛኛው አበሻ ያተኮረው በጣም በጣት በሚቆጠሩ የስራ አይነቶች ላይ ብቻ ነው ። ሌሎች ላይስ?
ይህ "ተያይዞ ገደል" የሚሉት ስራ UBER እና LYFT የተባሉ ሁለት ኩባንያወች ገበያውን መቆጣጠራቸው አላንስ ብሎ
አበሻው እርስ በርሱ በተከራይ (DRIVER) እና አከራይ (OWNER) በሚሉት ጎራ ተከፋፍሎ እርስ በርሱ ሲናቆር አንዳንድ ከተሞች ላይ የከተሞች ህግን በመቀየር ለሁሉም ታክሲ ነጂ አቅሙ ካለው ድሮ በጥቁር ገበያ (BLACK MARKET) ከ $150 000 በላይ ያወጣ የነበረውን የታክሲ ፈቃድ ዛሬ በ $4000 ዶላር እንዲያገኝ በመፍቀዱ የታክሲው ባለቤት ከተሳፋሪው በላይ ሆኖ ሁሉም ተጠቃሚ ሳይሆን ለUBER እና ለLYFT ሾፌሮች የበይ ተመልካች ሆኗል ። ከሁሉ የሚያሳዝነው ደግሞ ገበያው መሞቱ ሳይሆን በዚያውም ልክ ህጉ መጠንከሩ ነው፡ ለምሳሌ ሳንድ ያጎ በምትባል የካሊፎርንያ ግዛት በምትገኝ ከተማ የወጣው ህግ አንድ የታክሲ ባለ ንብረት የታክሲ ፈቃዱን ካወጣ በኋላ ታክሲ አልነዳም ብሎ ታክሲውን ማቆም አይችልም ። ያንን ማድረግ ከፈለገ የተወሰነ ቀን ለማቆም ልዮ ፍቃድ አግኝቶ ጊዚያዊ የታክሲ ስራ ማቆም ፈቃድ ያገኛል ። ነገር ግን በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ስራውን መጀመር ሲኖርበት ያንን ካላደረገ ደግሞ ታክሲውን ፈቃድ ማስረከብ አለበት ።
በዚህ የታክሲ ንግድ የገበያ ሽቅበት ላይ የተጠቀሙት የመኪና ሻጫች ፣ የታክሲ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች እና የታክሲ ፈቃድ ሰጪ መስሪያ ቤቶች ናቸው ። ለምሳሌ ሳንድያጎ ውስጥ መጀመሪያ በወጣው ህግ አንድ ግለሰብ የታክሲ ፈቃድ ካወጣ ማቅረብ ያለበት መኪና እድሜው ቢያንስ ቢያንስ 10 ዓመት በላይ ያልሆነ እና መኪናው የሚያወጣው ጭስ (EMISSION) የአየር ንብረትን የማይበክል መሆን አለበት የሚል በመሆኑ አብዛኛው ሾፌር TOYOTA PRIUS የምትባል በኤሌክትሪክ የምትሰራ መኪና ለማውጣት የተገደደ ሲሆን እንዲሁም ታክሲ እንደ ንግድ መኪና በመቆጠሩ ልዮ የሆነ ኢንሹራንስ (COMMERCIAL INSURANCE) መግባት ነበረበት። ሌላው ደግሞ በህጉ መሰረት አንድ ባለ ታክሲ የሬድዮ አገልግሎት (TAXI RADIO DISPATCHING SERVICE) መኖር አለበት ስለተባለ ያ የታክሲ ባለቤት በወር ቢሰራም ባይሰራም በወር ከ $1000 - $2000 ዶላር ወጪ አለበት ማለት ነው ። ይህ ደግሞ የታክሲ ገበያው በ UBER እና በ LYFT ከመወሰዱ ጋር ተቀላቅሎ ነው ። ታዲያ ድሮ የታክሲ ተከራይ ልክ እንደ ካልሲ ሲያማርጡ የነበሩ ከአንድ በላይ ታክሲ የነበራቸው ግለሰቦች ታክሲውን ማከራየት ባለመቻላቸው እና ታክሲው ቆሞ ለኢንሹራንስ እና ለፍቃድ የሚከፍሉት በጣም ብዙ ስለሆነ ያላቸው አማራጭ ድሮ $150,000 በላይ ያወጣ የነበረውን ታክሲ ዛሬ በነጻ መመለስ ነው።
ይህ በዚህ አላበቃም በአዲሱ ህግ የታክሲ ባለ ንብረት የነበሩት የታክሲ ሰራተኞች የመኪና ክፍያ ፣ኢንሹራንስ፣ነዳጅ ፣የፍቃድ ማደሻ እያለ ናላቸውን ስላዞረው ሳይወዱ በግዳቸው “ጎመን በጤና ” እንዲሉ የታክሲ ፍቃዳቸውን አስረክበው መኪናቸውን የቤት መኪና በማድረግ የUBER እና የLYFT ሾፌሮች ሆነዋል። አሁን በUBER እና LYFT ብዙ መንዳት ይጠበቃል እንጂ ገበያው አይከፋም ብለዋል ።
ግን ይህ የስራ እና የገቢ ግሽበት በታክሲ ብቻ አለበቃም ። የታክሲን ስራ በአፍ ጢሙ በመድፋት የገበያውን ሰላም ያደፈረሱት (MARKET DISTURBANCE) UBER እና LYFT አበሻውንም እንደ ማእበል ከወዲህ ወዲያ እያላተሙት ይገኛሉ። UBER የተባለው ለዚሁ ሁሉ ነውጥ ተጠያቂው ገና ስራውን ሲጀምር ከዚህ በፊት ይሰሩ የነበሩትን ባለ መኪኖችን ወደ ኡበር በማስገባት በጣም ታይቶ የማይታወቅ ገቢ ሲያስገኝላቸው ያንን ቆንጆ ገቢ በማየት በየከተማው ሁሉም ወደ ኡበር ፊቱን አዙሮ ከዚያም የUBERን ገቢ ያየው LYFT ደግሞ በተራው የራሱን ኩባንያ ከፍቶ ሾፌሮችን በቤት መኪናቸው ልክ እንደ ታክሲ ሰው እንዲያመላልሱ መፍቀዱ ነበር ። የLYFT ን አመጣጥ እና ተቀናቃኝነት ያየው UBER አገልግሎቱን በማስፋት የመኪናዎችን አይነት በአራት ከፈላቸው ። እነዚህም ፥ UBER SUV፣UBER BLACK፣ UBER XL እና UBERX ናቸው። በዚህ ጊዜ የUBER ሾፌሮች ቁጥር በብዙ እጥፍ ሲጨምር ከዚህ በፊት በህልማቸው እንኳ አስበውት የማያውቁት አሜሪካኖች ወደ ገበያው ገቡ። UBERም የገበያን እና የተጠቃሚውን ብዛት ሲመለከት አርጀት ያሉ መኪናዎችን ከስራ አባረረ ። በተለይ ደግሞ የ UBER BLACK እና UBER SUV የተባሉትን አገልግሎቶች ለመስጠት ብዙ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በጣም በብዙ ዶላር መኪና ገዝተው ትንሽ አመት እንሰራለን ሲሉ ወሽመጣቸው በመቆረጡ ግማሹ መኪናውን ሽጦ (በርካሽ) ሌላ አዲስ መኪና ለመግዛት ተገዷል ሌላው ደግሞ ኡበርን እርም ብሎ ትቷል። የሹፌሮች ብዛት በበዛ ቁጥር ገበያ እየሞተ በዚያው ልክ ደግሞ የሾፌሩ ቁጥር እየጨመር መጥቷል ። ለአብነት ያክል ይህንን ሪፖርት ስናደርግ UBER ከመምጣቱ በፊት በሳንድያጎ ከተማ ከ3000 የማይበልጡ የታክሲ ሾፌሮች የነበሩ ሲሆን ዛሬ ግን ከ 20 000 በላይ የ UBER ሾፌሮች አሉ ማለት ነው። አብዛኛው አበሻ ታክሲም ሆነ UBER ወይም LYFT የሚነዳው እንደ ቋሚ ሳራ አድርጎ እራሱንም ሆነ ቤተሰቡን እየረዳ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የUBER እና የLYFTን ስራ አጨናንቀውት ያሉት ግን ሌላ ስራ እያላቸው መኪና የሚነዱት እንዲያው ለመደበሪያ እና ያለባቸውን ሱስ ማስታገሻ የሚሆን ተጨማሪ ገንዘብ ለማግኘት የሚነዱት ናቸው የሚባል ወሬ አለ ። ሌላው የኡቡር እና የሊፍትን የሾፌሮችን ብዛት ከዚህ ያደረሰው ሁለቱም ድርጅቶች ባላቸው ገንዘብ ህግን መቆልመም ስለሚችሉ ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው የታክሲ ነጂ ለመሆን ያለበት እዳ አይጣል ነው። የታክሲው ሾፌር የጣት አሻራ ተነስቶ፣ የወንጀል ታሪኩ(CRIMINAL RECORD) ተጠንቶ ትምህርት ወስዶ ሌላም ሌላም ውጣ ውረድ ወጥቶ እና ወርዶ ነው። የ UBER እና የLYFT ነጂ ግን መኪናው ደህና ትሁን እንጂ ኢንሹራንስ እስካለው ድረስ ማሽከርከር ስለሆነ ሁሉም ዘው ብሎ የሚገባበት ስራ ሆኗል። ግን አንድ ቀን UBER እና LYFT የሚቀጥሩትን ሰው የወንጀል ታሪክ (CRIMINAL RECORD) መመርመር ቢጀምሩ ብዙ ነጂዎች ከስራ ስለሚባረሩ ጥቅሙ ለታክሲም ሆነ ለኡበር ነጂ ነው።
ታዲያ ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ አሁን ደግሞ የታክሲ ስራን የሚፈታተን ቴክኖሎጂ እያኮበኮበ ነው:: በ GENERAL MOTORS የሚሰራው ROBOTXI በስራ ላይ ለማዋል ሙከራው በ SAN FRANCISCO እና ሌሎችም ከተሞች እየተሞከረ ነው ። ታዲያ የህ ሊታመን የማይችል ቴክኖሎጂ እውን ከሆነ የታክሲም ሆነ የዑበር ነጂወች ምን እያደረጉ ነው?
እንደ ዜናው ከሆነ በቅርብ አመታት ውስጥ እውን የሚሆን ይመስላል።
በኔ ግምት የ ታክሲ ሾፌርም ሆነ የኡበር ሾፌር እጁን አጣምሮ መጠበቅ የለበትም ። ሰው በማሽን እየተተካ መሆኑን ለማየት እስኪ ወደ WALMART ሱቅ በሉና SELF SERVICE የሚባለውን ገንዘብ ተቀባይ ማሽን እዪ፣ቀስ በቀስ የሰውን ስራ እየወሰደ ሰው በማሽን እየተተካ ነው። ታዲያ መድሀኒቱ ምንድን ነው?
መድሃኒቱ ከባድም ቀላልም ነው። መድሀኒቱ እንደ እድሜያችሁ እና እንዳላችሁ የትምህርት ደረጃ እንዲሁም እንደ ቤተሰባችሁ ብዛት ይለያያል ። እንደ አሜሪካው የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይም (DEPARTMENT OF LABOR) በአሜሪካ ውስጥ ከ 65ሺ በላይ የስራ አይነቶች አሉ (የስራ ብዛቶች አላልሁም) ነገር ግን አብዛኛው አበሻ ያተኮረው በጣም በጣት በሚቆጠሩ የስራ አይነቶች ላይ ብቻ ነው ። ሌሎች ላይስ?
ከላይ እንደገለጽሁት መድሃኒቱ እንደ እድሜያችሁ እና እንዳላችሁ የትምህርት ደረጃ እንዲሁም እንደ ቤተሰባቸሁ ብዛት ይለያያል ብያለሁ። ለዚህም ምክንያት አለኝ ። ለምሳሌ እድሚያቸው ከ 50 አመት በላይ ለሆኑ ከአሁን በኋላ ወደ ትምህርት ቤት ሄዳችሁ ተመርቃችሁ ስራ ፈልጋችሁ ከዚያ ከታክሲ ስራ ውጡ ለማለት በጣም ይከብዳል ምክንያቱም ግለሰቦች ብዙ የቤተሰብ ሃላፊነት ስላለባቸው ስራቸውን ማቆም ያዳግታቸዋል በሚል ነው። ግን ወኔው ካለ እንኳን 50 90 ቢሆኑ የትምህርት ገደብ የለውም።
ወጣቶች እና የኮሌጅ ዲግሪም ሆነ ዲፕሎማ ይዘው የእለት ገቢያቸን ሮቦት ሊወስድባቸው ሲል በዝምታ ከንፈራቸውን እየመጠጡ ለሚቀመጡ በጣም አዝናለሁ። ያላቸው እድል እራሳቸውን ወደ ትምህርት ቤት አዙረው ጥሩ ስራ የሚያስገኝ ትምህርት ተምረው የትራንስፖርቴሽን ባሪያ ከመሆን መፋታት ነው። ታዲያ በተለይም ወጣት የታክሲ ሾፌሮች ነገ ዛሬ ሳትሉ ፊታችሁን ወደ ትምህርት አዙሩ።
ወጣቶች እና የኮሌጅ ዲግሪም ሆነ ዲፕሎማ ይዘው የእለት ገቢያቸን ሮቦት ሊወስድባቸው ሲል በዝምታ ከንፈራቸውን እየመጠጡ ለሚቀመጡ በጣም አዝናለሁ። ያላቸው እድል እራሳቸውን ወደ ትምህርት ቤት አዙረው ጥሩ ስራ የሚያስገኝ ትምህርት ተምረው የትራንስፖርቴሽን ባሪያ ከመሆን መፋታት ነው። ታዲያ በተለይም ወጣት የታክሲ ሾፌሮች ነገ ዛሬ ሳትሉ ፊታችሁን ወደ ትምህርት አዙሩ።
ታዲያ ይህ ምክር ለሁሉም ነው;። እድሚያቸሁ ትንሽ ገፋ ካለም የአጭር ጊዜ ኮርስ ወስዳችሁ እራሳችሁን በትምህርት ማደስ ነው። አለበዚያ በኡበር ላይ የታየው የገበያ ግሽበት በሮፖት ደግሞ የከፋ እንዳይሆን። ሮቦት ከመጣ ታክሲንም የኡበርም ሆነ የሊፍት ሾፌርን አይምረውም።
በነገራችን ላይ አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል እንደሚባለው የአሜሪካው የታክሲ ቢዝነስ መዳከም ለኢትዮጵያም ጉዳት አለው፣ ምክንያቱም የታክሲ ነጂ ብዙ ከሰራ ለቤተሰቡ እና ለዘመዶች ብዙ ማድረግ ይችላል ማለት ነው። ያ ማለት ተጠቃሚወ ሆነ ተጎጂው በግለሰቡ ዙሪያ ያለው ሰው ሁሉ ነው እና መታሰብ አለበት
አምዴ ነኝ ችር ይግጠመን
በነገራችን ላይ አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል እንደሚባለው የአሜሪካው የታክሲ ቢዝነስ መዳከም ለኢትዮጵያም ጉዳት አለው፣ ምክንያቱም የታክሲ ነጂ ብዙ ከሰራ ለቤተሰቡ እና ለዘመዶች ብዙ ማድረግ ይችላል ማለት ነው። ያ ማለት ተጠቃሚወ ሆነ ተጎጂው በግለሰቡ ዙሪያ ያለው ሰው ሁሉ ነው እና መታሰብ አለበት
አምዴ ነኝ ችር ይግጠመን
I heard about Bitcoin several years ago, I thought it was a scam and illegal. Back then it was less than a dollar per share. Now after few years the value of 1 bit coin is more than $11,000.00. Last month it was more than $15,000. Now the price is swinging but not that much. A week a go I bought very small amount of bit coin to test the market and several of you are asking me how I did it. Well, someone (Habesha) who is already investing on the market told me how to do it and I did it. Now I am sharing my piece of knowledge to you. Share it!
ማሳሰቢያ : ይህ አዲስ ገበያ ወዴት እንደሚያመራ በውል መረጃ ስለሌለ አደራ ያለ የሌለ ወረታችሁን ከዚሁ እንዳትጨምሩት። ረጋ ብላችሁ እያስተዋላችሁ
These are simple steps I took.
Step One : I created an account at Coinbase.com
Step Two: Coinbase.com Verified my identity
Step Three: Coinbase.com asked my Credit Card /bank info
Step Four: Coinbase.com deposited very small amount of money in my bank Like $1.60
Step Five: I put the exact amount in my profile to verify my bank
Step Six: I logged in to the Coinbase.com web site and clicked on Dashboard and then to Buy/Sell button.
Since my Credit Card was approved I just put how much money I want to add and I clicked on "Buy Bitcoin Instantly"
Once you are in the Coingbase dashboard you can buy four crypto currencies . These are:
- Bitcoin
- Bitcoin Cash
- Ethereum
- Litecoin
Also you can down load the Coinbase.com app from ap store for Apple or Android devices and can watch, buy and sell bitcoins
No comments:
Post a Comment