A Yebbo Global Information Hub

EthioVibes Global

World travel, documents, money, auto, food, culture, history, sports, diaspora, business and technology.

Passport Photo Translation Notary Tax Travel ለኢትዮጵያውያን
Advertisement

Joke ቀን ከደረሰ.....

Published




አንድ ሃብታም ጥይት የማይበሳው መኪና ይገዛና በከተማው እንደልቡ ሲሽከረከር አንድ ቀን ሌቦች ያገኙታል፣ ሰውዬውም መኪናውን ጥርቅም አደርጎ ይዘጋና አምላኩን አውጣኝ እያለ ሲፀልይ የከበቡት ሌቦች በያዙት ክላሽንኮፍ የጥይት ዝናብ ያወርዱበታል፡፡ ሰውዬውም ሞትሁ ብሎ እራሱን ይስትና ብንን ሲል መኪናው ምንም ጥይት ሳያሳልፍ አንድ እንኳ ሳያስገባ ያገኘዋል፡፡ ይህንን ያወቀው ሀብታም መኪናው ውስጥ ሆኖ ሌቦችን መሳደብ እና ማሾፍ በጣቱም ባለጌ ምልክት ያሳይ ጀመር፡፡ ከዚያ ከለቦች አንዱ ብልህ ኖሮ ጮህ ብሎ ሃብታሙን "የምትሳደበው አይሰማም " ሲለው ሃብታሙም መሰኮቱን ዝቅ አድርጎ አንገቱን አሾልኮ ሊሳደብ ሲል በጥይት ተመትቶ ጥይት የማይበሳውን መኪና ተወሰደበት እሱም ያው ከማይቀረው አለም ሄደ፡፡ ቀን ከደረሰ እንኳን ጥይት የማይበሳው ቦምብ የማይበሳው መኪና ቢይዙ ከሞት አይቀርም፡፡
http://yebbo.com/worldcup/

Comments