ከኅዳር 22 በኋላ በአሮጌ ብር ግብይት መፈጸም እንደማይቻል ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ
******************************
ብሔራዊ ባንክ ለኢቲቪ በላከው መግለጫ ከኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም በኋላ በአሮጌ ብር ግብይት መፈጸም እንደማይቻል ገልጾ፣ አሮጌውን ብር በአዲስ ብር የመቀየሪያ የመጨረሻ ቀን ግን ታኅሣሥ 6 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን አስታውቋል፡፡
የባንኩ መግለጫ እንደሚያስረዳው፣ እስከ አሁን ያልተቀየረ ብር እንዲቀየር እና ሂደቱን ለማፋጠን ከኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ታኅሣሥ 6 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት 15 ቀናት በአሮጌ ብር ግብይት መፈጸም አይቻልም፤ ግብይት መፈጸም የሚቻለው በአዲሱ ብር ብቻ ነው፤ በእነዚህ የመጨረሻዎቹ 15 ቀናት ማንኛውም ሰው አሮጌውን ብር ወደ ባንክ ሄዶ መቀየር ግን ይችላል፡፡
ታኅሣሥ 6 ቀን 2013 ዓ.ም የመጨረሻ ብር የመቀየሪያ ቀን መሆኑ ታውቆ ህብረተሰቡ በእጁ ያለውን አሮጌ ብር እንዲቀይር ባንኩ አሳስቧል፡፡
No comments:
Post a Comment