Shop Amazon

Friday, November 13, 2020

የተከዜ ግድብ በቦምብ ተደብድቧል የሚለው ሀሰተኛ መረጃ መሆኑ ተገለፀ

የተከዜ ግድብ በቦምብ ተደብድቧል የሚለው ሀሰተኛ መረጃ መሆኑ ተገለፀ
***************************

የተከዜ ግድብ በቦምብ ተደብድቧል በማለት በጽንፈኛው የህወሃት ቡድን  የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል፡፡

ተከዜ ሀይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ ልክ እንደ ሌሎቹ የኃይል ማመንጫ ግድቦች ሁሉ በፌደራል መንግሥት የተገነባና የሚያስተዳድረውም የፌደራል መንግሥት ነው።

እሁድ ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዕለት የህወሓት ሚሊሻ ግድቡን ለመጠበቅ የተሠማራውን የፌደራል ፖሊስ ኃይል ከሥራው ለማደናቀፍ ጥቃት  መፈጸሙ ተገልጿል። 

የተጎዱት እና የተገደሉት ቁጥር ያልተረጋገጠ ቢሆንም፣ በሕይወት የተረፉት 11 የፌደራል ፖሊስ አባላት ለ14 ሰዓት ያህል በእግር ተጉዘው፣ ተራራዎችን አቆራርጠው ወደ ጎንደር መግባታቸው ተገልጿል፡፡

በቀጣዮቹ ቀናት የህወሓት አክቲቪስቶች በማኅበራዊ ሚዲያ አማካኝነት "ግድቡን ተቆጣጥረናል" የሚል መረጃ ማሰራጨታቸው ተገልጿል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የህወሓት ሚልሻዎች በማይካድራ በንጹሀን ዜጎች ላይ የፈፀሙትን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ሪፖርት ባወጣበት በህዳር 3፣ 2013 ዕለት፣ የህዝብን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር የተከዜ ግድብ በቦንብ እንደተመታ የሚያትት ሆን ተብሎ የተቀናበረ፣ የሀሰት መረጃን ህወሓት በቴሌቪዥን አሰራጭቷል።

ባለሁለት ክበብ ቅስት ያለው እና በውሀ የተሞላ ግድብ በቦንብ ቢመታ ሊያስከትል የሚችለው መጥለቅለቅ እና ጥፋት ማንም ሊገምተው የሚችለው መሆኑ የመረጃውን ሀሰተኛነት በቀላሉ ለማረጋገጥ ይቻላል ተብሏል።

ተፈጥሯዊ ባህሪው ነውና፣ በህወሓት ውስጥ የሚገኘው የጽንፈኞች ቡድን በሀሰት ለማሳመን ጥረት ማድረጉን ይቀጥላል የተባለ ሲሆን፣ህወሓት የሀሰት መረጃ የማሠራጨት ዘመቻውን በትጋት መቀጠሉን ሁሉም ሰው እንዲገነዘብ ተጠይቋል፡፡

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን
 It was revealed that the Tekeze Dam was bombed
 ***************************

 The state of emergency is under investigation by the extremist TPLF for claiming that the Tekeze Dam was bombed.

 The Tekeze Hydroelectric Power Project, like other hydroelectric dams, is built and operated by the federal government.

 On Sunday, October 29, 2013, the TPLF militia reportedly attacked a federal police force guarding the dam.

 Although the number of casualties is unknown, the 11 surviving federal police officers walked for 14 hours, crossed mountains and entered Gondar.

 In the following days, TPLF activists reportedly spread information on social media that they had "taken control of the dam."

 On November 3, 2013, Amnesty International reported on the TPLF militia's massacre of innocent civilians in Maikadra.

 It is said that the flooding and destruction of a two-circle arch and a dam filled with water can be easily verified.

 It is inherent that the TPLF extremists will continue to try to persuade them, and everyone is asked to realize that the TPLF has continued its efforts to spread false information.


No comments:

Post a Comment