A Yebbo Global Information Hub

EthioVibes Global

World travel, documents, money, auto, food, culture, history, sports, diaspora, business and technology.

Passport Photo Translation Notary Tax Travel ለኢትዮጵያውያን
Advertisement

የሀዘን መግለጫ

Published
የሀዘን መግለጫ
          ____________
በምዕራብ ጎጃም ዞን የፍ/ሰላም ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ልዑል መኮንን የአማራ ክልል መንግስት በጠራው  የአማራ ልዩ ሀይል:ሚሊሻና መከላከያ ነጻ ባወጣቸው አካባቢወች ህዝብን የማረጋጋትና አመራርን ማደራጀት ተልዕኮ (ዘመቻ ማይካድራ) የክልሉን መንግስት ጥሪ ተቀብለው  የተሰጣቸውን ተልዕኮ በታማኝነትና በቁርጠኝኘት እያገለገሉ ባሉበት ትላንትናው ዕለት ማለትም ህዳር 9/2013  ስራቸውን ሲሰሩ  ውለው ሲመለሱ በወልቃይት ልዩ ስሙ አድርመጺ በሚባል አካባቢ የተሳፈሩበት መኪና ተገልብጦ ህይወታቸው አልፏል። ለአማራ ህዝብ መስዋት ሆነዋል።
 
አቶ ልዑል መኮንን በሰራባቸው ቦታወች ሁሉ ታማኝ: ቅን ውጤታማና ጠንካራ አመራር በመስጠት ህዝብን ያገለገለ ወጣት መሪ ነበር። 

በወንድማችን መሰዋት  ጥልቅ ሀዘን ቢሰማንም ለህዝብና ለሀገር  ደህንነት ሲባል የተከፈለ መስዋትነት በመሆኑ ለሌሎች የትግል ጓዶቹ ህዝብን ማገልገል እስከመስዋትነት መሆኑን አስተምሮን አልፏል ።

የምዕ/ጎጃም ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤትም በወንድማችን መስዋት መሆን የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ  ለቤተሰቦቹ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለስራ ባልደረቦቹ መፅናናትን ይመኛል።

ነፍስህን ፈጣሪ በአፀደ ገነት ያኑራት

ለሀገርና ለህዝብ መስዋት መሆን ሞት ሳይሆን ክብር ነው!!

Comments