Pages

Friday, May 9, 2025

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የማንኛውም ተሽከርካሪ ወይም ቤት ስም ከመዞሩ በፊት የታክስ እዳ ነፃ (clearance) ማስረጃ ማቅረብ አስገዳጅ ማድረጉ ታውቋል።

 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የማንኛውም ተሽከርካሪ ወይም ቤት ስም ከመዞሩ በፊት የታክስ እዳ ነፃ (clearance) ማስረጃ ማቅረብ አስገዳጅ ማድረጉ ታውቋል።

መሠረት ሚድያ የተመለከተው እና ሚያዝያ 20/2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የታክስ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ በሆኑት ወ/ሮ ወርቅነሽ ሰቦቃ የተፃፈው መመርያ ለከተማው የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፣ ለመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ፣ እንዲሁም ለአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የተፃፈ ነው።

መመርያው 'የታክስ እዳ ነፃ (clearance) ሳይጠየቅ የስም ንብረት ዝውውር እንዳይከናወን' የሚል ሲሆን አስፈላጊነቱን ሲገልፅም "ከተማ ውስጥ በርካታ መሰረተ ልማት ስራዎች እና ዘርፈ ብዙ ሰው ተኮር ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ" በማለት ገቢው የእነዚህም ወጪ ለመሸፈን እንደሚውል ይጠቁማል።

"የታክስ ባለእዳ እዳውን እስካልከፈለ ድረስ ማናቸውም ተሽከርካሪ (ኮድ 2ን ጨምሮ) እና ለማናቸውም አገልግሎት የሚውል (ለመኖርያ ቤት ጭምር) እና ያልተጠናቀቁ ቤቶች ለታክስ እዳ ማካካሻነት የሚሆኑ ሀብቶች እንደሆኑ" የሚገልፀው ደብዳቤው አፈፃፀሙ አሁኑኑ እንደሚጀምር ያሳያል።

No comments:

Post a Comment