A Yebbo Global Information Hub

EthioVibes Global

World travel, documents, money, auto, food, culture, history, sports, diaspora, business and technology.

Passport Photo Translation Notary Tax Travel ለኢትዮጵያውያን
Advertisement

በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከባለፈው ሁለት ሳምንት ወዲህ ግብፅ ውስጥ በገፍ እየታሰሩ መሆኑ ታወቀ

Published
በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከባለፈው ሁለት ሳምንት ወዲህ ግብፅ ውስጥ በገፍ እየታሰሩ መሆኑ ታወቀ Meseret Media Mar 14 (መሠረት ሚድያ)- ከሁለት ወራት በፊት ጀምሮ በግብፅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኃይል ታፍሰው ወደ ተለያዩ እስር ቤቶች ተወስደው እየታጎሩ መሆኑን በካይሮ የሚኖሩ ስደተኛ ዜጎች ለመሠረት ሚዲያ ተናገሩ። ለስራ እንደወጡ መንገድ ላይ በግብፅ የፀጥታ አካላት የተወሰዱ እናቶች ከጨቅላ ልጆቻቸው ጋር ጭምር ከተለያዩ ሁለት ወር ያለፋቸው ሲሆን የት እንደተወሰዱም ልናውቅ አልቻልንም ይላሉ። ገና እድሜያቸው ያልደረሱ ታዳጊዎች ሳይቀር ታፍነው ተወስደዋል የሚሉት ስደተኞቹ ሕጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያንም ጠፍተዋል ሲሉ ለሚዲያችን ተናግረዋል። በግብፅ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ቢሮ ስደተኛ መሆናቸውን አረጋግጦ የሰጣቸው መታወቂያ ሳይቀር በፀጥታ ኃይሎች እየተቀደደ ወደ እስር ተወስደዋል ሲሉም አክለዋል። Photo: File ቀደም ሲል በዋና ከተማዋ ካይሮ በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በንግድ ስራ እና ሰው ቤት ተቀጥረው በመስራት ይተዳደሩ እንደነበር የገለፁት እነዚሁ የመሠረት ሚዲያ ምንጮች በአሁኑ ወቅት ልጆቻቸው ሳይቀር ከትምህርት ገበታቸው ተገልለው በቤት ውስጥ ተዘግተው እንደሚውሉ ነው የተናገሩት። የኃይል አፈሳ እየተፈፀመ ያለው በኢትዮጵያውያን እና በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ብቻ መሆኑን እና ኤርትራውያን በኤምባሲያቸው አማካኝነት ወደ አገራቸው እየተሸኙ ሲሆን በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ግን ገና የታሰሩበት አድራሻ እንኳ ማወቅ አልተቻለም ብለዋል። ይህንኑ አስመልክቶ በግብፅ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲጠይቅልን በተደጋጋሚ ብናመለክትም ሰሚ አላገኘንም ሲሉ ተናግረዋል። -መሠረት ሚድያ-

Comments