Shop Amazon

Tuesday, March 11, 2014

ጤፍን ያዩበት አይናቸው ውስጥ የጤፍ እብቅ ይግባበት (Amen)

ጤፍን ያዩበት አይናቸው ውስጥ የጤፍ እብቅ  ይግባበት
እኔ ሳድግ ጤፍ የሚሸጠው በሰሃን ተሰፍሮ  ነበር። ከገሬው ላይ። ከዚያ ጤፍ ነጋዴ መጣ,  በኪሎ የሚቸበችብ። ከዚያ ደርቅ እንጀራ መሸጥ ጀመረ፣ ከዚያ ጤፍ ከሌላ ዱቄት ጋር ተደባልቆ ጤፍ እንጀራ ተብሎ መሸጥ ጀመረ:: እንጀራ ሆነ። እንጀራ  በሸክላ ምጣድ ሳይሆን በኤሌክትሪክ መጋገር ጀመር:: ሰፋቱም አነስ::ውፍረቱም ቀነስ:: ከሳ መነመነ:: ከዚያ አሜሪካ ምድር ገባ :: በቃ እንጀራ ቅጡን አጣ፣ አይኑ ጠፋ፣ መልኩ ጠፋ፣ቅርጹ ጠፋ በቃ እንጀራ እንጀራ መሆኑ ማጠራጠር ጀመረ። ከዚያ ጤፍን አይን በላው። የፈርንጅ አይን አየው። ብለው ብለው ታላቁ ምግብ ሱፐር  ፉድ (super food)  እያሉ ይጠሩት ጀመር። ምን ያማ ጤፍ ቡና ሊሆን ነዋ። ያኔ በሰሃን ስንዝቀው የነበረው ጤፍ ዛሬ እንደ ወንጂ ስኳር በላስቲክ እየታሸገ ሊሽጥ ግን የወንጂ ስኳር ምን ነበር? ያንን በሌላ ጊዜ አሁን ግን ስለ ጤፍ። ከሁሉ ያሳሰበኝ ጤፍ ከቻይና እንዳይመጣ ነው። ምንው ፈረንጅ ሌላ ስራ አጣ? ምነው ጤፍን አዩብን? ለሁሉም ጤፍን ያዩበት አይናቸው ውስጥ የጤፍ እብቅ ይግባብት (Amen)

No comments:

Post a Comment