የአሳ ደም አለው ?


የአሳ ደም አለው ?
የሞኝ ጥያቄ እንደምትሉ አልጠራጠርም። በዚህ በአብይ ጾም የአሳ ነገር የኦርቶዶክ ተዋህዶ ተከታዮችን ለሁለት የከፈለ ጉዳይ ነው። እንደሚታወቀው በዚህ አብይ ጾም  ስጋ፣ እንቁላል፣ ወተትና የመሳስሉት አይበሉም/አይጠጡም። በዚህ ጉዳይ ላይ ሁሉም አንድ ሲሆን የአሳ ጉዳይ ግን ትንሸ ግራ ያጋባል። እኔ በበኩሌ የአሳ የመብላት ፍላጎቴ የሚያይለው አሁን ስለሆን በቃ ደስ ብሎኝ ነው የምበላው። ግን ማን ብላ እንዳለኝ ስለማላውቅ ያው የወረስሁት ልምድ ስለሆነ ለማቆም ሃሳቡም የለኝም። ግን ድሮ ልጅ ሳለሁ የተነገረኝ አሳ ደም የለውም ነበር። ዛሬ ውሎየ አሳ ገበያ ስለነበር ያየሁት አሳ ደም ሳይሆን በቃ ለዚያውም ደማቅ ቀይ ደም ነው ያለው። መብላቴን ባላቆምም እስኪ አሳ የምትበሉ አሳ ደም የለውም ከሚለው ውጭ የተፈቀደበትን ሌላ ምክንያት ለንባብ አብቁት::


Comments