Call Yebbo

የቦ ኮሚኒኬሽን ኔት ወርክ ፣ ለ25 አመታት በላይ የስራ ልምድ ያካበተው የእናንተው በእናንተው። ከምሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ የውክልና አገልግሎት መስጠት የኢትዮጵያ ፓስፖርት አገልግሎት መስጠት የቢጫ ካርድ የማውጣት አገልግሎት የታክስ አገልግሎት መስጠት (የትም የኢትዮጵያ ግዛት ይኑሩ) የጉዞ ወኪል የትርጉም ስራ አገልግሎት ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 619-255-5530 ይደውሉ።

የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት በሙሉ እንዲሁም አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አናስተካክላለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment) እንችላለን። የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViberም ሆነ Whatspp ይደውሉልን። ስልክ ቁጥራችን 619 255 5530 ነው ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Sunday, June 22, 2014

ያበሻ ቀጠሮ and World Cup

ያበሻ ቀጠሮ and World Cup




ያበሻ ቀጠሮ ማለት ሁለት ወይም ሶስት ሰዓት ከቀጠሮው መዝግየት ነው። ግን ማን እና መቼ ተጀመረ ?  እኔ እንደሚመስለኝ የተጀመረው ድሮ ሰዎች ሰዓትን በፀሃይ ጥላ ሲቆጥሩ ነው ።የናንተን አላውቅም እንጂ የገሬ ሰው ሰዓትን የሚቆጥረው በፀሐይና በዶሮ ነው። በውድቅት ማለት ለምሳሌ በጣም በሌሊት ሲሆን ዶሮ ሳይጮህ ደግሞ ሳይጋ ሲሆን ጀንበር ስትጠልቅ ማለት ወደ ማታ ሊሆን ሲል ሲሆን ጅብ ሳይጮህ ደግሞ ያው በጣም ሲመሽ ነው። ያም እንደየ ዋራቱ እና ወቅቱ ሊቀያየር እንደሚችል ዘንግተን ነው። ለምሳሌ የክረምት እና የበጋ ፀሐይ አንድ አይሆኑም እና። በሳይንሱ መሰረት ነው። የክንድ ሰዓት መጥቶ ሃብታሞች ወይም ትልልቆች/ ባላ ስራዎች ሲጠቀሙ ደግሞ ሰዓትን ለጌጥ እንጂ ለሰራ የሚጠቀመው ብዙም አይደል። በድሮ ጊዜ ኑሮ በጣም ይጣፍጥ ነበር። ሁሌ እረፍት ሁሌ ጨዋታ ስለነበር ለስዓር ብዙም ግድ አልነበረውም ። ዛሬ ግን ያው ኑሮ ባከና ስለሆን ሁሉም በሰዓት ሳይሆን በደቂቃ,  በደቂቃ ሳይሆን በሰከንድ መባከን ሆኗል። ልብ ብላችሁ ብታዩ እኛ ለምሳሌ በአለም አቀፍ ደረጃም ቢሆን የምናሸንፈው ሰፋ ያለ ጊዜ የሚጠይቀውን ማራቶንን (Marathon)ነው። ጊዜን በጣም መጠቀም በጣም እንፈራለን። ምክንያቱም መጣደፍ ወይም ችኩል ነው ብለን ስለምናምን ነው። አንድ ሰው ለምሳሌ ቶሎ ቶሎ ከተናገረ ለፍላፊ,  በጣም ሮጥ እሮጥ ካለ ደግሞ  ከውካዋ ብለን ስንጠራው ቀርፋፋውን ደግሞ እረጋ ያለ እያልን እናሞክሸዋለን። ግን አለማችን ዝግምተኛ ሳይሆን ከውካዋ እዬሆነች፣ እኛንም ነፍሳችንን ከውካዋ  እያደረገችው ነው። ለምሳሌ የእትዮጵያ ቡና ተጠጥቶ እስክሚያከትም ፫  ሰዓት ሲወስድ የአሜሪካው ኩባንያ Starbucks  (ባይኔ ያዬሁትን ነው) በሶስት ደቂቃ ሶስት ሰው ያስተናግዳል። ይህም ማለት በአንድ ሰዓት ከ60 ሰው በላይ ማለት ነው። ይገርማል። ሌላው የሰዓት ጥቅም የታወቀው በዚህ በስፖርት አለም ነው። ሰከንድም ሰው ሆና ሰውን ታራውጠው ጀመር። ዛረ የአሜሪካ (Team USA) ቡድን እኩል ለኩል የወጣው  ባለቀ ጊዜ ነው። ታዲያ ያች ደቂቃ ታሪክ ሰራች።  ጥያቄው እኛስ መቼ ነው? የአበሻ ቀጠሮ አቁመን የዘመኑን ቀጠሮ የምንጀመረው? እስኪ ዛሬውኑ ቀጠሮ ይያዙና ያሰው የሚድርስበትን ጊዜ ይመዝግቡ። በሰዓቱ ከደረሰ ሽልማት ስጡት።የሽልማቱን ነገር እራሳችሁ አሰላስሉት ግን የፈረንጅ ቀጠሮ አትበሉት።ለፈረንጅ ማን ሰጠው? ኤዲያ...

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon