Shop Amazon

Monday, August 25, 2014

ሳንድያጎ የኢትዮጵያ ቀን እና የቡሄ በአል በደማቅ ስነ ስርዓት ተከበረ






ሳንድያጎ የኢትዮጵያ ቀን እና  የቡሄ በአል በደማቅ ስነ ስርዓት ተከበረ
Ethiopian Day Celebration. Photo Credit Yedidaya

(Yebbo.com San Diego Aug 8 25, 2014)  በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሳንድያጎ አስተባባሪነት የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ቀን ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ ኢትዮጵያውያን በተገኘበት በታዋቂው የሰላማዊ ውቅያኖስ ዳርቻ ላይ ትናንት እሁድ ነሃሴ 24፣2006 ዓም በታላቅ ድምቀት ተከበረ። በዚህ ዝግጅት ላይ  የእግር ኳስ ጨዋታ ግጥሚያ፣ ጭውውት፣ ሙዚቃ፣ ነፃ የምግና መጠጥ፣ ባህላዊ የኢትዮጵያ ቡና፣ የበቆሎ እሽት ጥብስና የተለያዩ ባህላዊ ጭፈራዎች የተደረጉ ሲሆን በእለቱም የክብር እንግዳ  የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ተጫዋች አቶ ሽዋንግዛው አጎናፍር የማበረታቻ ንግግር ሲያደርጉ የማህበረሰቡ ፕሬዘዳንት አቶ ተረፈ መኮንንም በቦታው ለተገኙት የበአሉ ተሳታፊዎች ታላቅ ምስጋና አቅርበው ይህ በሀል የጋራችን የሆነ አንድ የሚያደርገን የኢትዮጵያውያን መመኪችን በመሆኑ ለወደፊቱ ከዚህ በበለጠ ለማክበር የማንኝውም ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አስታውቀው ምሽቱ የቡሄ ችቦ በማብራት ተጥናቋል።
Attn: Did you take some pictures of video and would like to share it with others, tag us #yebbo from your facebook or email it to info@yebbo.com

No comments:

Post a Comment