Shop Amazon

Friday, September 19, 2014

መገንጠል የሞኝ ነው።





መገንጠል የሞኝ ነው። ለምን በሉኝ?  አሜሪካ ስትጀመር ጀመሮ  አስራ  ሶስት ግዛቶች ነበሯት በእድሜም ሆን በስፋት ከኛ ታንስ የነበረችው አሜርካ ተዋግታም ሆን ገዝታ ዛሬ ታላቋ አሜርካ ሆና የድሮ እናቷን እንግሊዝን በልጣ ትገኛልች።  ለምሳሌ ቴክሳስ፣ ሉዚያና፣ ካሊፎርንያ፣ አላስካ፣ እና ሌሎችም ግዛቶች በገንዘብ ተገዝተው ነው። ታዲያ ከአሜሪካ የምንማረው አገርን ጠንካራ የሚያደርጋት/ገው አብሮ መኖር እንጂ መገንጠል አይደለም። ሌላው ምሳሌ ደግሞ የእንግሊዙ እና የስኮትላንዱ ፍቺ ነበር። ስኮትላንድ በቃኝ መረረኝ እሄዳለው ስትል የእንግሊዝ ፕለቲክኞች መጀመሪያ ቀልድ ከዚያ ነገሩን ሲያዩት መረር፣ ጠንክር እና ሃያል ሲሆንባቸው ምን አደረጉ መስላችሁ ሁሉም የእንግሊዝ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ልዩነታቸውን ወደ ሗላ ጣል አድርገው ስኮትላንድን ከእናቷ እንዳትለይ ብዙ ማባበያ ሰጡ። ለምሳሌ የታክስን ሌላ ሌላም መሽንገያ። ልክ እንደ ጥሩ ወላጅ አባብለው ከቤት ጥዬ እጠፋለሁ ያለችውን እስኮትላንድን አስቀሩ ማለት ነው። እስኮትላንድም ቤቴን ለቅቄ ብወጣ ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል ብላ አስባ አስላስላ  ይቅርብኝ ብላ ቁጭ አለች። መተሳስብ ይሉታል ይህን ነው። እንግሊዞች የአለምን ካርታ ያሰመሩት እነሱ ይመስሉኛል።  ሆን ብለው እርስ በእርሱ አለም ዘላለሙን እንዲናኮር አሚኬላ እሾህ ተክለው የሄዱ ሴረኞች። ዛሬ ግን ያ መርዝ ቤታቸው ብቅ ሲል ያሁሉ ወኔ ሜዳ ገባና የመገንጠልን ችግር ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ለምነውም ሆነ ተለማምጠው ስኮትላንድን አስቀሩ።  አይ ሆፕ (I hope) ይህን ትምህርታቸውንም ለሌላው ቢያስተምሩ መልካም ነው። ነገሩማ ምን መማር ያስፈልገዋል ሁሉም ግልጥ ነው። አንድ ሰው ሙሉ አካላት አለው፣ ለምሳሌ የግለስቡ እጅ በጣም ጥንካራ እና ቦክስኛ እግሩ ድግሞ ለኳስ ምቹ የሆነ ግለሰቡን ኮክብ ያደረገ ነው እንበል። ታዲያ ይህ ግለሰብ አይ እጄ  ወይም እግሬ ይገንጠሉ ይላል? አይልም!  ምክንያቱም የእጁም ሆነ የእግሩ ጥንካሬ የመላው አካሉ  በአንድነት  መስራት ነው። አገርም እንዲህ ናት። በደርልና ግፍ ሊኖር ይችላል ግን በቃ በትንሽ በትልቁ ካልተገነጠልሁ ማልቱ በብዛት ለሚገነጠልው አገር አይበጅም። ምክንያቱም ትልቁ አካል ካለ ትንሹ ሊኖር ይችላልና። ለምሳሌ አንድ ሰው በአንድ እግር ወይም በአንድ እጅ ሊኖር ይችላል ግን አንድ እጅ ወይም እግር ካለ ዋናው ሰውነት አይኖርም። ታዲያ መገንጥል ለማንም አይበጅም። የተገነጣላች ሁም ወይም እንገነጠላለን ብላችሁ ያሰባችሁ ካላችሁ ያው ከፈረንጅ መማር ስለሚቀናን ከዋናዎቹ ከእንግሊዞች ተማሩ። አንድነት ሃይል ነው።

No comments:

Post a Comment