Post by Tes Z Shegole.
ለቴዲ አፍሮና የባንዱ አባላት ሳንድያጎ ኑ እየጠበቅናችሁ ነው::

ቴዴ አፍሮ ካባንዱ ጋር ሳንድያጎን ሲጎበኝ ለዬት ያለ ነገር ያጋጥመዋል። የተፈጥሮ ውበት፣ የኢትዮጵያውያን እንግዳ ተቀባይነት እና የማይጠገብው የሳንድያጎ አዬር ፀባይ ቴዲን በአንድ ቀን ተመልካቹን አስደስቶ መሄድ ብቻ ሳይሆን እሱም ተዝናንቶ መንፈሱን አድሶ የሙሄድባት የቫኬሽን (vacation) ከተማ ነች። ታዲያ ቴዲም ሆነ የባንዱ አባሎች መያዝ ያለባቸው የሙዚቃ መሳሪያቸውን ብቻ ሳይሆን ፓስፖርታቸውን ጭምር ነው። እደግመዋለሁ ፓስፖርታቸውን :: ምክንያቱም ሳንድያጎ የምትገኘው 15 ደቂቃ ከሜክሲኮ ድንበር ላይ ስለሆነች ወጣ ብሎ መዝናናት ያው የተለመደ ስለሆነ ሜክሲኮ ደግሞ ካለ ፓስፖርት መመለስ አሁንም እደግመዋለሁ መውጣት ሳይሆን መመለስ ስለማይቻል ከዚሁ መጠንቀቅ ነው።
ሳንድያጎን ፈጣሪ ሲሰራት ለሰው ዘና ብሎ ተፈጥሮን እያጣጣመ እንዲኖር አድርጎ የሰራት ስለሆነ አሜሪካ ውስጥ አሉ የተባሉ ሃብታሞች ወይ ይኖራሉ ወይም ደግሞ ሁለተኛ ቤት ሳንድያጎ አላቸው። ሎስ አንጀለስ ያው የደቡብ ካሊፎርንያ ክፍልና የአሜሪካ የትይንት ማእከል ቢሆንም ትፍግፍግ ያለ አየሩም ትንሽ ጠቆር ያለ ሲሆን ሳንድያጎ ደግሞ ፀዳ ያለ ምቹ ቦታ ነው። ለመዝናናት ለፈለገ ሰው ሁሉም ነገር አለ። ከተፈጥሮ መዝናኛ አንስቶ እስከ ሰው ሰራሽ መዝናኛ ድረስ ሁሉም በአይነት በአይነቱ ስላለ ሳንድያጎን በአንድ ወይም በሁለት ቀን አይቼ እመለሳለሁ ማለት በራስ መቀለድ ነው። የሳንድያጎ አራቱም ማእዘኖቿ በተፈሮ የታደለች ናት:: ወደ ሰሜን የውቅያኖስ ዳርቻ፣ ወደ ደቡብ ሜክሲኮ ወደ ምስራቅ ስላማዊ ውቅያኖስ ወደ ምእራብ ደግሞ ለአይን የሚማርኩ ተራሮችና ኮረብቶች አሏት። አንዳንዴ ልክ እማማ ኢትዮጵያ ያሉ እስከሚመስል ድረስ ልብ ይማርካሉ። ክበበው ገዳ እንዳለው ሌሎች ከተሞች እንዳለው ህዝብ ሁሌ በጃኬት ተሸፍኖ አይኖርም:: ሁሉም ዘና ብሎ ብዙው በከናቲራ እና በቁምታ ሱሪ ነው። ታዲያ ማንም ስለ አየር ፀባይ አይጨነቅም። ሁሌም ብርሃን ሁሌም ፀሐይ ነው። አንዳንዴ አንዳንድ የኢትዮጵያ አርቲስቶች ስለ ማእበል የጻፉት ዘፈን ልክ ሳንድያጎ ላይ ሆነው የጻፉት ይመስላል። የውቅያኖሱን ማእበል እንደ አክምባሎ ደፋ ቀና ሲል መመልከት መንፋስን ያረካል:: ከተማዋን ፈጣሪ እጁን ታጥቦ የሰራት ይመስላል። የኛ ፍራቻ ቴዲ አልመለስም ብሎ አምልሰትን ካልመጣሽ ብሎ ማሳመኑ ላይ ነው። ሁለቱም ከመጡ መቅረታቸው የማያጠራጥር ነው። ባይቀርሩም በሆዳቸው ማሰባቸው የማይቀር ነው። ታዲያ ከእንዲህ ያለ ከተማ መምጣት በአንድ ደንጋይ ሁለት ወፍ አይሆን? አዝናንቶም፣ ተዝናንቶም። ታዲያ ይህ የት ይገኛል? ለሁሉም የዛሬ ሳምንት መልሱን ከራሱ ከቴዲ እንስማው።
No comments:
Post a Comment