የጃኪ ጎሲን ፊያሜታ ቪዲዮ ዩቱብ ላንቃውን ዘጋው::
ከ 5,117,220 በላይ ተመልካቾችን ያስመዘገበው የጃኪ ጎሲ ፊያሜታ ቪዲዮ ዩቱብ ላንቃውን ዘግቶታል። ምክንያቱም የ መሳሪያው አጃቢ ድምፁ የሌላ ሰው ነው በሚል የእኔነት ይገባኛል በሚል ክስ ይመስላል። "This video previously contained a copyrighted audio track. Due to a claim by a copyright holder, the audio track has been muted" አቶ ጎሱ ዩቱብን ይህንን ክስ ለማሸነፍ ማሳዬት ያለበት ብዙ ነገር አለ። ከነዚህም ውስጥ ህጋዊ ሰነድ ማለትም ኮንትራት የተፈራረመበትን ማሳየት ሲሆን በሃገራችን ይህን አይነት ውል መዋዋል ያልተለመደ አሰራር ሰለሆን አቶ ጎሲ ማድረግ ያለበት ምን እንደሆን ባለሙያዎችን (ጠበቃ ) ማነጋገሩ ተገቢ ነው። ሌሎች የኢትዮጵያ አርቲስቶችም በጎሲ ላይ የደረሰውን እንደ ምሳሌ ወስደው ጠንቀቅ ነው። እነሱ ሰው ካለ አግባብ ቀዳብን ብለው ሲጨነቁ የእነሱ ሰራ ውስጥ አግባብ የሌለው ስራ ካለበት ሁሉንም ይዞት ገደል ይገባል። አታድርስ ነው::
No comments:
Post a Comment