A Yebbo Global Information Hub

EthioVibes Global

World travel, documents, money, auto, food, culture, history, sports, diaspora, business and technology.

Passport Photo Translation Notary Tax Travel ለኢትዮጵያውያን
Advertisement

ክበበው ገዳ የሳንድያጎን ህዝብ በሳቅ ጥርሱን ሊያረግፍ ተዘጋጅቷል:: በቦክስ ሳይሆን በቀልድ

Published




ክበበው ገዳ የሳንድያጎን ህዝብ በሳቅ ጥርሱን ሊያረግፍ  ተዘጋጅቷል:: በቦክስ ሳይሆን በቀልድ::
በቅርቡ በኢንተርኔት ላይ የተለቀቀውን የክበበው ገዳን ስራዎች ያዬ ሰው  የክበበው ገዳን በሳልና ጠጠር ያሉ የላቁ ስራዎችን እንዴት አድርገው ከቀልድነት አልፈው አዝናኝና በውስጣቸው ክኒን የያዙ ስራዎች ከያኒ ክበበውን አሉ ከሚባሉ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ከያንያን ተርታ አድርጎታል። ይህንን ታላቅ ስራዎን ይዞ ክበበው አድናቂዎችን ከአጥናፍ አጥናፍ እያስደነቀ ነው። በተለይም ደግሞ "አንተ ሳቅ እኔ ልሳቀቅ !" እንዲሁም  "ማይ ጎድ"  የሚሉት አባባሎቹ በንግግር ውስጥ ጣልቃ እየገቡ እለት ከእለት የሚዘወተሩ የቋንቋችን ክፍሎች ሆነዋል። ለዚሁም ነው ክበበው ለመጀመሪያ ጊዜም ሳይሆን ለሁለተኛ ጊዜ ሳንድያጎን ሊጎበኝ ሲመጣ ህዝቡ በሳቅ ጥርሱ እንዳይረግፍ ካሁኑ የሳቅ ልምምድ ላይ ያለው። በክበበው ሳንድይጎን በመጪው  October 11, 2014 ላይ ስራውን ያሳያል::

Comments