Shop Amazon

Tuesday, September 15, 2015

የሰብለ ገዳይ ማን ነው?

የሰብለ ገዳይ ማን ነው?
የሁላችንም መልስ የተለያየ ቢሆንም ሞት የሚመጣው ያው ቀናችን ሲደርስ ስለሚሆን  በፈጣሪ ለምታምኑ መወለድም ሆነ መሞት የፈጣሪ ስራ ነው።ነገር ግን ለስብለ ሞት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ንክኪ ይኖራቸዋል ብዬ ስላሰብሁ ባለኝ አቅሜ የሰብለ  መሞት ተጥያቂም ሆነ  ለመኪናዋ ግጭት ምክንያት የሆኑትን ነጥቦችን ጣል ጣል ላድርግ ብዬ ነው።  ስብለን የማውቃት በቤቶች ድራማ ነው። ያው የዘሩ ቀለጠ ዘመድ እና ሰራተኛ ሆና ስትሰራ በነበራት ገፀ ሃህሪ  ላይ ትርፌን ሆና ስተ ሰራ ነበር። በዚያ በትርፌ ገፀ ባህሪዋ ላይ ሰብለ በሆድ ተመስላለች፣ ሆድ ማለት ቻይ ማለት ነው። ተስድባም ፣ተጣልታም ሆነ ተንገላታ ሁሉንም ችላ ኑሮዋ ለቤቷ ነበር። ታማኝ፣ ለዘምድ ሟችነቷ ለእውነት ያላት ክብር በዚያ በትርፌ ገፀ ሃህሪዋ ላይ እውነትም የተትረፈረፈች ሆና ስታዝናናን ኖራለች። ታዲያ ስብለን ያ ለእይታ  በቅቶ እኛን ሳቅ በሳቅ ሆነን የደስታ ፀጋና የተትረፈረፈ ሳቅና ጨዋታዋ ሲለየኝ/ን በጣም ከልብ እያዘንሁ ነው።





የትርፌን እውነተኛ ስም ሰብለ መሆኑን ያወቅሁት የእንቁጣጣሽ እለት ነው። ገና በጠዋቱ መከረኛ ፌስ ቡኬን ስከፍተው ፎቶዋና ስሟ ብቅ ብሎ አየሁት። በአካል ተገናኝተን ባልውቃትም እንኳ ለኔ ግን የራሴን እህት ያጣሁ ሆኖ ነው የተሰማኝ። በጣም ነበር ያዘንሁ።  አሁንም እያዘንሁ ነው ያለሁ።  ለቤተሰቦቿ እና ለአድናቂዎቿ እግዚያብሄር ያጥናችሁ እላለሁ።  ታዲይ የኔ ጥታቄ የሰብለ ገዳይ ማን ነው? ከሚለው ላይ ነው።

ታዲያ የኔን ትንተናን አብረን እንከታተል። ያስታውሱ ይህ የኔ የራሴ ትንታኔ በምንም አይነት መረጃ ላይ የተመሰረተ ስላልሆነ እንደ መረጃ መወሰድ የለበትም  ግን የመሰለኝን እና በሆዴ ያለውን ለንባብ ላብቃው ብዬ ነው።

የኢትዮጵያ የመኪና መንገዶች ማለት በሰለጠነው አለም የተሰሩ መኪኖች የመኪና መንዳት ህጉን ለማያከብረው ላልሰለጠነው አሽከርካሪ እንካ ሰው ግደል ተብሎ የስው ማጥፊያ  ፈቃድ (የመግደያ ፈቃድ ) ወይም የመንጃ ፈቃድ የሚሰጥባት ሀገር ናት። ታዲያ ስብለን ማን ገደላት ተጥያቂውስ ማነው? በኔ አስተያየት ለሰብለ ሂዎት መጥፋት  እና ለብዙ ኢትዮጵያውያን ሂዎት መጥፋት ተጠያቂዎች የሚከተሉት ናቸው። ዛሬ በሀገራችን የመኪና እራት የሚሆኑት ዜጎች ቤት ይቁጠረው ነው።  ታዲያ ለብዙሺህ ህዝብ እልቂት ተጠያቂዎች እነማናቸው? 


የመንጃ ፍቃድ ሰጪ ባለስልጣናት። አንድ ሰው መኪና መንጃ ፈቃድ ካለምንም እውቀት በገንዘብ ብቻ ካገኘ ያ ሰው ታንክ ወይም መትረዬስ ከተሰጥው ሰው አይተናነስም። ያ  በገንዘቡ መንጃ ፈቃድ ያገኘ ሰው ውሎ አድሮ ሰው መግደሉ ስለማይቀር የኢትዮጵያ የመንጃ ፈቃድ ፈተናና ፈቃድ በመስጥት የተስማሩ ግለስቦችና የመንግስት አካላት ተጥያቂዎች ናቸው።

የመንገድ ስራ ባለስልጣን። አንድ አገር ያላት የተሽከርካርሪ ብዛትና ባደገ ቁጥራ ያንን እድገት በቅርቡ እየተከታተለ መንገዶችን መስራት፣ መጠገን፣ ተገቢ የትራፊክ ምልክቶችን እና የፍጥነት መከላከያዎችን፣ መኪና ማቆምም ሆነ እግራኛ መራምድ የሚችልበትን፣ የመኪናዎች አይነት እና ብቃት በተመደበው መመሪያ መሰርት መሄዳቸውን መቆጣጥር ባለመቻሉ::

የትራፊክ ፖሊስ። በጉቦ የሚንቀሳቀስ የትራፊክ ፖሊስ ማለት ለአሽከርካሪዎች ሰው ግደሉ ብሎ ሽጉጥ የሚያቀብል ዲያቢሎስ ማለት ነው። አሽከርካሪውች ጥፋት ሲያጠፉ ጥፋተቸውን አምነው እና ሌላ ጥፋት እንዳይሰሩ ተገቢ መቀጫ እና ስልጠና እንዲያገኙ ማስገደድ ሲኖርበት ዛሬ በአብዛኛው የትራፊክ ፖሊስ ስልጣኑን የሚጠቀምበት ያስጀመረው ቤት  ማስጨረሻ ወይም ላለበት ሱስ ማብረጃ የሚሆን ገንዝብ ማግኛ ባንክ ነው ያደረገው። ትራፊኩ ህጉን ከማስከበር ይልቅ ለእሱ ገንዝብ ያስገኛሉ ብሎ የሚጠረጥራቸውን አሽከርካሪዎችን አስቁሞ ካለ ጥፋታቸው መቅጣት እና ገንዝብ መቀበል ስራው ነው። ታዲያ የትራፊክ ፖሊስም እጁ አለበት::






የባለ ጭነት መኪናው። የሰብለ ባል መኪናውን ሲነዳ ሄዶ ከቆም መኪና ጋር ተላተመ ነው የተባለው። ግን ለምን? የቆመው መኪና መቆም በማይገባበት ቦታ ላይ ነው ያቆመው? የቆመው መኪና የቆመው ለአይን አስችጋሪ በሆነ ኩርባ ቦታ ላይ ነው ወይስ በጣም ጠባብ እና ለትራፊክ መጨናነቅ መንስኤ በሆነበት ቦታ ላይ? ለምሳሌ ይህ መኪና ሲቆም ሌሎች መኪኖች እንዳይጋጩ ሪፍሌክተር  (reflector or hazard sign)ወይም ሌላ ምልክት አድርጎ ነበር?ተበላሽቶ የቆም ነበር? ወጣ ብሎ የቆም ነበር?መንገድ ዘግቶ ነበር ? ይህ ሁሉ መጠየቅ ያለብት  ነው።

እግረኛው።
የኢትዮጵያ እግረኛ መኪና ይንቃልመኪናን የሚያክል ተንቀሳቃሽ ብረት  ከመሸሽ ይልቅ በአንድ እጁ የሚያቆመው ይመስል  ከመኪናው ጋር ይጋጫልመኪናው በተጋጨ ጊዜ በቦታው እግረኛ ነበር? ያ እግረኛ በተመደበለት ቦታ  ነበር የሚያቋርጠው (cross walk)? እግረኛው ሳይታሰብ ወደ መኪናው ዘሎ ገባ ምን ሆነ?

መኪናዋ ስብለ ተሳፍራባት የነበረችዋ መኪና ምን ችግር ነበረባት፣ የፍሬን? የዲዛይን? የእይታ? ሬዲወው ከሽፌሩ በምን ያክል እርቆ ይገኛል? በጣም አስችጋሪ ዲዛይን?የመኪናዋ ጥንካሬ፣ በምን ያክል ግጭት ነው መኪናዋ ተሳፋሪውን ለአደጋ የምታጋልጠው (impact)? የመኪናዋ ጥንካሬ ባለው ደረጃ መሰረት ተሰርታለች

ሾፌሩ:   እኔ ስልጣን ቢኖረኝ የኢትዮጵያን አጠቃላይ ሾፌር መንጃ ፈቃዱን ቀምቼ ሁሉም ሙሉ ስልጠና ወስዶ ተገቢውን ፈተና ካለፉ በኋላ ለመንዳት እንዲችሉ ማድረግ ነው። ይህንን የምለው ካለ ምክንያት አይደለም። እኔ ከምኖርበት ከተማ ወይም ግዛት በጣም ብዙ መኪና አለ። መኪና ማለት እግር ነው። የመኪናው ብዛት ለአይን ማመን ያስቸግራል። በሚሊዮን የሚቆጠር መኪና (በቀን) ልክ እንደ ውሃ ሲፈስ መመልከት በጣም ያስገርማል። ግን ያ ሁሉ መኪና በዚያ ፍጥነት ሸው ሽው ሲል እንዲያው ዝም ብሎ በትአምር የተገኘ አይደለም። ይህንን ሁሉ ሾፌር ብቃቱን እና ጥራቱን የሚጠብቁ በስራው ብቁ የሆኑ የመንጃ ፈቃድ ፈታኞች፣ ፖሊሶች የመንገድ ስራ ባለስልጣናት እጅና ጓንት ሆነው ስለሚሰሩ ነው። አዎ የትራፊክ አደጋ የለም አይደለም ግን የመኪናውን ቁጥር እና የአደጋውን ብዛት ስናይ የኢትዮጵያው ለጆሮ ይከብዳል። ታዲያ ይህ ለምን ሆነ? ነው። የመጀመሪያው የአስከርካሪዎች ስልጠና ነው። ማንም ስው ብቃት ከሌለው ፈተና ማለፍ አይችልም። ጉቦ የለም። ሁሉም ሰው በስራው ያልፋል። ሌላው ህጉን የማያከብሩ አሽከርካሪዎች ዋጋቸውን ያገኛሉ። ቅጣቱ እንደ ጥፋቱ የተለያየ ሲሆን አንዳንዱ በገንዘብ በጣም ህጉን ከጣሰ ደግሞ በእስራት ያስቀጣል። ለምሳሌ አልኮል ጠጥቶ ሲነዳ የተያዘ አሽከርካሪ  ቅጣቱ አይጣል ነው። ዋጋውን ያገኛል። አደንዛዥ እፅ ይዞ የተገኘ የዘላለም ቤቱ እስር ቤት ነው። ጉቦ በጣም ከስቶ የመነመነበት ህብረተሰብ ነው። አንዳንድ ባለጌ ፖሊሶች ያልሆነ ህገ ወጥ ስራ ከመስራታቸው በስተቀር አሽከርካሪው ጥፋት ካጠፋ የእንጀራ ገመዱ ስለሚበጥስ ተጥንቅቆ ህግ አክብሮ ይነዳል። ያም ለሌላውም ሰላም ለእርሱም ሰላም ይሰጣል። ግን ይህ ሁሉ ህግና ስነ ስርአት እያለ አደጋ አለ ሞትም አለ ግን እንደ አገራችን የገነነ አይደለም



ቴክኖሎጂ ካለቦታው። ሌላው ለስብለ ሞት ተጠያቂው ቴክኖሎጂ ነው። በምራቡ አገር አነጋገር እነዚህ ነገሮች በእጅጉ እየተከለከሉ ሲሆን እነሱን መጠቀም ቅጣት አለበት። እነዚህ ሾፌሩን የሚያደናግሩ ዳንቂራዎች (Distracted driving is the act of driving while engaged in other activities—such as looking after children, texting, talking on the phone or to a passenger, watching videos, eating, or reading. These activities take the driver's attention away from the road. devices ) ለብዙ ሰው ሂዎት መጥፋት አስተዋፆ አድርገዋል። እነዚህም የመኪና ቴፕ፣ ራዲዮ፣ ሲዲ ሲሆኑ እየነዱ ስልክ ማውራት በጣም ትልቁ የዘመናችን የሰው ሂዎት አጥፊ ቴክኖሎጂ ነው። በብዛት ሾፌሮች  ሌሎች እጅን ከስልክ ነፃ የሚያደርጉ የስልክ መነጋገሪያ መሳሪያዎችን  (hands free) ከመጠቀም ይልቅ በአንድ እጅ እያዎሩ በአንድ እጅ እየነዱ ህዝብን መጨረስ የተለመደ ሆኗል። እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ከጥቅማቸው ጉዳታቸው የበለጠ ሲሆን የሚገርመው ግን ሾፌሩ የሰውን ነፍስ ይዞ እየበረረ በቴክኖሎጂ ሲጫዎት የዶሮ ነፍስ እንኳ ለማዳን ከሚያደርገው ጥንቃቄ ያነሰ ነው። ግን ሰው ከሞተ በኋላ እየየ ነው

ስካር። ኢትዮጵያ ውስጥ ሾፌርና ስካር የቅርብ ጓደኞች ናቸው። መጋበዝ መገባበዝ ያው ባህላችን ሲሆን ሾፌርን ካልጠጣህ በሞቴ እያሉ መጋበዝ ካልሞትህ ወይም ካልገደልክ ብሎ ሾፌሩን መለመን ነው። የአሁኑን አላውቅም ድሮ ግን ትራፊኩና ሾፌሩ አብረው አረቄ፣ ጠላ፣ ድራፍት ወይም ጠጃቸውን ሲለበልቡ ውለው የትራፊክ ፖሊስ ሌላ ሾፌር ፍልጋ (ጉቦ ለመብላት) ሾፌሩ ደግሞ ተደግፎም ሆነ ተንገዳግዶ መኪናውን ይዞ ይከንፋል። እንዲያውም አንዳንዱ ሲጠጣ ጥሩ ሆኖ ይነዳል ይባልና እንደ ጀግንነት ይቆጠርለታል። ያ ድንቁርና ነው። አልኮል እራሳችንን እንዳንቆጣጠር (Impaired judgement:Impaired judgement is a medical condition that results in a person not being able to make good decisions because of an underlying medical problem, environmental factors, diet or drugs/alcohol,)  ያደርጋል። ወይም ደግሞ ግምታችን እንዲዛባ ስለሚያደርግ ለ አደጋ ይዳርጋል። ግን ሾፌሩ እና ትራፊኩ አብረው ከጠጡ ምንም ዋጋ የለውም። ሁሉም ታጥቦ ጭቃ ነው። አንድ የትራፊክ ፖሊስ በስራ ላይ እያለ ምንም አይነት አልኮል መቅመስ የለበትም ግን በብዛት አብረውት የሚጠጡ ሾፌሮች ሰክረው ሲሄዱ እያዬ  አንድ ሰው ትርፍ ጭንሃል ብሎ ጎቦ ለመብላት የሚያሰቃዬው የታክሲ ወይም የሌላ ሾፌር  አይጣል ነው። ይህ ነገር ጋባዥንም ያስጠይቃል። ለምሳሌ እኔ እሲህ ባለሁበት አገር አንድ ቡና ቤት ግለሰቡ መስከሩን እያወቀ ከመጠን በላይ አልኮል ሽጦለት ሾፌሩ ጉዳት ቢያደርስ የቡና ቤቱ ሰራተኛም ተጠያቂ ነው። ይህም ማለት ለድግስ የጠራነው ሰው መኪና መንዳቱን ካወቅን ግለሰቡ በስውና በንብርት ላይ አደጋ ሊያደርስ ስለሚችል የሾፌሩን ቁልፍ ቀምቶ በታክሲ ወይም በእግሩ መላክ ነው። ያ ብልሃት የሰውን ሂዎት ያድናል።

የእውቀት ማነስ፣ ንቀት እና ስግብግብነት፥ እነዚህን 3 ነገሮች በአንድ ላይ ያደረግሗቸው የአንባብያንን ጊዜ ለመቆጥብ ብየ ነው። ሾፌር መኪናውን በትክክል አይረዳም። ይህም ማለት መኪናዋ ውስጥ ያሉት ለሾፌሩ ደህንነት እና መኪናዋ የምትሰጠውን የማስጠንቀቂያ ምልክት ችላ ማለት ናቸው። ለምሳሌ የመኪና ቀበቶ የሚታሰረው በ አደጋ ጊዘ ተሳፋሪም ሆነ ሾፌር ተፈንጥረው በመውጣት ሌላ የባሰ አደጋ  እንዳያጋጥማቸው ታስቦ ነው። እነዚህ መኪኖች ይህንን አይነት ነገር እና የመሳሰሉትን የደህንነት እቃዎችን ሲጨመርባቸው በብዛት ከብዙ ምርምር እና ጥናት ጋር ተያይዞ ሲሆን በተለይ በምራቡ አለም ያሉ አገሮች መኪኖች እነዚህን ነገሮች ከሌላቸው መሽጥም አይችሉም። ለምሳሴ እኔ ባለሁበት ግዛት ቀበቶ ሳያስሩ መንዳት ያስቀጣል። ለስብለ መሞት አንዱ ምክንያት የሆነው እሷ በወቅቱ ቀብቶ አላሰረችም ነበር አሉ። ስለዚህ ከሰብለ እንማር። ሌላው የመኪናን ልክ አለማወቅ ነው። በ አብዛኛው መኪኖች ሲሰሩ ምን ያክል ሰው እንደሚይዙና ምን ያክል ጭነት እንደሚሽከሙ ይታወቃል ነገር ግን አንዳንድ ሾፌች ከስግብግብነትም ወይም ከእውቀት ማነስ ጋር በተያያዘ መንገድ መኪናዋን ከ አቅም በላይ ጭነው በስውና በንብረት ላይ ጉዳት ያስከትላሉ። ሌላው ትልቁ የህዝቡ ጠላት ካለ መጥን በፍጥነት የሚነዱ ሾፌሮች  ናቸው። በሰለጠንው አገር የመኪና ፍጥነት እንደ አካባቢው ይለያያል። ለምሳሌ ትምህርት ቤት እና እግረኛ በሚበዛበት ወይም ከተማ ውስጥ የመኪናው ፍጥነት በጣም ትንሽ ሲሆን  በ አውራ መንገዶ እና አገር አቋራች መንገዶች ድግሞ በብዚ ፍጥነት መንዳት ሲቻል ግን ህጉ ከሚፍቅደው በላይ መንዳት አይቻልም። ሌላው በጣም በሚያሰቅቅ ሁኔታ የትራፊክ አደጋ የሚያስከትለው መኪናን መቅደም ወይም ማለፍ ነው። ይህም ማለት መኪናውን  ለመቅደም ሲታሰብ መንገዱ አንድ መኪና ብቻ ስለምያሳልፈ ፊት ለፊት በሚመጣው መኪና መስመር ላይ አድርጎ መኪናን መቅደም ክፊት የሚመጣው መኪና በድንገት ከመጣ ፊት ለፊት መላተም ያለው አደጋ አይጣል ነው። በህጉ የት መቅደም እና አለመቅደም ምልክት ያለ ቢሆንም ፎፌሮች ችላ በማለት በተለይም ደግሞ ብዙ ህዝብ የጫኑ አውቶቡሶች ከነተሳፋሪያቸው ሲላተሙ ሙሉ በሙሉ ከውስጥ ያለው ህዝብ ያልቃል። ሌላው የሾፌሮች ስግብግብነት ነው። እንደሰማሁት አንዳንድ ሾፌሮች መኪና ተቀጥረው ስለሚሳሩ እና የመኪናው ባለቤት ከሰጣቸው የቀን ፍጆታ በላይ ለራሳቸው ለመስራት ብለው በደከመና በጫት በደነዘዘ አእምሯቸው  ሲከንፉ በህዝብ እና በንብረት ላይ የሚያደርሱት ጥፋት የትዬለሌ ነው
To be continued

No comments:

Post a Comment