የሽሮና ወጥ እና የወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ተመሳሳይነት
ሽሮ ከኢትዮጵያ ምግቦች ሁሉ የመጀመሪያው እና የክፉ
ቀን ደራሽ የሆነው፣
ካልሰለቹ በስተቀር አመቱ ሙሉ ቢባላ በዶክተርም ሆነ
በሀይማኖት ያልተከለከለ ታላቅ ምግብ ነው ። የሚገርመው ግን
ሽሮወች ሁሉ እኩል አልተፈጠሩም። ለስም ሁሉም ሽሮወች ተመሳሳይ
ቢሆኑም ነገር ግን በጣም
ብዙ የተለያዩ የሽሮ ወጦች አሉ።
ለምሳሌ አንዱ አንዱ ቀጭን፣ አንዱ
በቅቤ አብዶ የተሰራ፣ አልጫ ሽሮ፣ ምጥን ሽሮ፣ ወፍራም ወይም ቀጭን ሽሮ፣ የፈላ ሽሮ፣
ያልፈላ ሽሮ፣ እና የሁሉም የሽሮ ወጦች አለቃ ቦዘና ሽሮ ለአብነት ያክል የሚጠቀሱ ናቸው።
ግን ይህን ሁሉ የተለያየ ሽሮ አይነትን ያመጣው የሽሮው ዱቄት ሳይሆን
የባለሙያው የአሰራር ችሎታ እና የጥበብ ልዩነት ነው።
ታዲያ
መንግስትም ልክ እንደ ሽሮ አሰራር ነው። ጥሩ አስተዳደር ጥሩ ሽሮ ወጥን ይፈጥራል ። መጥፎ አስተዳደር ደግሞ ቢበሉት የሚያቅር፣ ውሃ ውሃ
ወይም የሚያቃጥል ሽሮ ይሆናል
።
በጣም የሚገርመው ግን ይህ አሁን በአገራችን የማየው ነገር ከሽሮ ወጥ ጋር መመሳሰሉ ነው። ለምን? በሉኝ ነገሩ እንዲህ
ነው።
በሽሮ ወጥ አሰራር ላይ ያሉትን ንጥረ ነገሮች እስኪ አብረን እንቃኛቸው
እና እያንዳንዱን ሂደት ደግሞ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ
ጋ አቻ
ስያሜ እንስጠ።
አንድን
ሽሮ ወጥ ለመስራት የሚያስፈልጉ ነገሮች ለምሳሌ ውሃ፣ በርበሬ፣ ሽሮ፣ ጨው፣ ድስት፣ እሳት፣ ቅቤ ወይም ዘይት፣ ሽንኩርት እና የወጥ ማማሳያው ለአብነት ያክል የሚጠቀሱ ነገሮች ናቸው። ታዲያ እነዚህን ነገሮች ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታዎች
ጋር እናመሳስላቸው። ድስትብ ከነክዳኑ እንደ አገር እንደ
እማማ ኢትዮጵያ ፣ ሽሮን ልክ እነደ ህዝብ፣ እሳትን ደግሞ ልክ
እነደ መንግስት ወይም አስተዳደር እና ሌሎች የቀሩት ደግሞ ልክ እነደ ህግ እና ድንጋጌ ሲሆኑ ማንኪያውን ደግሞ ልክ እንደ ፖለቲካ እንያቸው።
ታዲያ
አንድ ሽሮ ጥሩ ሽሮ እንዲሆን በጥሩን ሁኔታ መዘጋጀት አለበት። በአይነ ሂሊናችሁ እስኪ አንድ እሳት ላይ የተጣደ ገና በመብሰል
ላይ ያለ ሽሮ ይታያችሁ። ይህ ሽሮ ጥሩ ሽሮ ወጥ እንዲሆን ከፈለግን
ከታች እሳቱን (መንግስትን) እየተቆጣጠርን
፣ ድስቱን (አገርን) አንዴ
ከፈት አንዴ ዘጋ እያደረግን በማማሰያ (በፖለቲካ) ቀስ እያልን ሸሮውን (ህዝቡን)
እናስተዳድራለን። ነገር ግን ከታች ያለው እሳት (መንግስት) ከሚገባው በላይ ከነደደ ሽሮ (ህዝብ) ይፈላና ቶሎ ብለን መላ ካልሰጠነው ቱግ ብሎ የደፋል። ታዲያ በንዴት የወጣው ሽሮ ቶሎ ብለን እሳቱን ካልቀነስነው የድስቱ (አገር) ክዳን እንኳብ ሳይቀር ገልብጦት
የደፋል።
ታዲያ አሁን
ያለው የሀገራችን እሳት ልክ እንደ ሽሮ ወጡ ማብሰያ እሳት ነው። ዝም ብሎ ጫናውንና እንግልቱን ከጨመሩበት (እሳቱን)
ማለት ነው። ህዝብ ከገነፈለ ማቆሚያው ከባድ ነው። አንዳንድ ሽሮ ከገነፈለ እራሱ እሳቱን ያጠፋዋል ።
ጎበዝ የሆነች የወጥ ሰራተኛ ግን ሽሮውን ቀስ እያለች እሳቱን (የመንግስትን ) እየቀነሰች፣
በማማሰያው እያማሰለች ቀስ ብላ ቆንጆ ያበደ ሽሮ ትሰራለች። ታዲያ ከሽሮ የምንረዳው ታላቅ ነገር፣
ሽሮ ቆንጆ የሽሮ ወጥ የሚሆነው ጎበዝ የሽሮ
ሰሪ (መሪ) ሲኖር ነው።
ነገር ግን ዝም ብሎ ሽሮውን በድስቱ (አገር ) አፍኖ እሳቱን(መንግስትን) ቢጨምሩበት
ሽሮ ጭንቅ ስለማይወድ የድስቱን ክዳን ከፍቶ ይገነፍል እና እራሱ ሽሮውን የሚያበስለውን እሳት (መንግስትን) ያጠፋዋል። ታዲያ ጥሩ
ሽሮ ለመብላት እሳቱን ቀነስ፣ ዘናና
ለቀቅ ማድረጉ ለሁሉም ይበጅል ።
አለበዚያ ሽሮውን በእሳት ካጋዩት
ትርፉ ሽሮው ገንፍሎ
እራሱን መንግስቱን (እሳቱን) ያጠፋዋል። ሽሮው ገንፍሎ እሳቱ አልጠፋ
ካለ ሽሮው ይጎረና እና ሳይበላ ይቀራል
ጠንቀቅ ነው። ሽሮን ቆንጆ ሽሮ የሚያደርገው ጎበዝ ባላሙያ ነው። ሀገርንም ጥሩ አገር የሚያደርገው
መልካም መሪ
ነው ::
አመሰግናለሁ
ለኢትዮጵያ አስተዋይ
መሪ ይስጣት
No comments:
Post a Comment