በቅድሚያ የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ የአዲስ አበባ ልጅ አይደለሁም። ግን ዘመድ ወዳጆቼ፣ ጓደኞቼ ለሎች ሌሎችም የአዲስ አበባ ልጆች ናቸው። አዲስ አበባ እኔም ከተወለድሁባት ከተማ ቀጥላ የራሴ ከተማ ናት ። በተጨማሪ ደግሞ አዲስ አበባ የእማማ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ስለሆነች የሁላችንም ከተማ ናት ።
እኔን የገረመኝ ግን የአዲስ አባባ ልጅ ሁሉ መለያው ሰፈሩ ነው ። በቃ አዲስ አበባ በሰፈር በሰፈር ተከልሎ እዚ አሜሪካ እንኳ ጓደኛ የሚሆነው በሰፈር ልጅ ነው ። ሁሉም ጎጡ ጎጡን ለይቶ ነው ያለው። የፒያሳ ልጅ ፣ የቦሌ ልጅ ፣ የአራት ኪሎ፣ የአምስት ኪሎ፣ የመርካቶ፣የአዲስ ከተማ ፣የካዛንችስ፣ የቄራ፣ የፈረንሳይ ፣የጉለሌ ሌላም ሌላም። ሁሉም የየራሱን ሚና ለይቶ ያራሱን ሰፈር ሲክብ፣ሲያሽሞነሙን፣ ከኔ በላይ አራዳ፣ ጨላጣ የለም እያለ የራሱን ሲያስበልጥ ይህው ከግማሽ ምእተ አመት በላይ በዚህች ምድር ላይ ስኖር አንድም ሰው ስለ ቆሼ ተንፍሶ አያውቅም ። አንድም የአዲስ አበባ ልጅ ስለ ቆሼ ልጆች ተንፍሶ አያውቅም።
ሁሌ የምሰማው የኛ ሰፈር ፎቅ ተሰራ፣ቀለበት መንገድ በዚህ አለፈ፣በዚህ ተጠለፈ፣ጁስ ቤት፣ማሳጅ ቤት፣ ሆቴል፣ናይት ክለብ፣ ጫት ቤት፣ሁካ ቤት ወዘተ ነው።
አይ ቆሼ ሰፈር? ከብዙ አመታት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ቆሻሻ ሲጣል በጣም ብዙ ህዝብ ከቦ በቆሻሻው ሲሻማ የሚያሳይ ቪዲዮ ኢንተር ኔት ላይ አይቼ በጣም አዝኜ ነበር፣ ግን ያ ቪዲዮ የትና መቼ እንደተቀረፀ አላውቅም ። ከዚያ በቅርብ አንድ ፊልም በYoutube ተመለከትሁ ፣ የፊልሙ እርእስ “የቆሼ ልጅ ” ይላል። ያንን ቪዲዮ አይቼ በጣም አዝኘ እና ተደንቄ ለአንዱ ስነግረው “ ይገርምሃል ያንን ፊልም ልክ ቦታውን እና ሰወችን ነው ያሳዩን ” አለኝ
”እኔ እኮ ልብ ወለድ መስሎኝ ነበር?“ ስለው
“ልብ ወለድ አይለም እውነት ነው” አለኝ
ከዚያ ለሌሎች የአዲስ አበባ ልጆች ስነግራቸው ለካን ይህ የአደባባ ሚስጢር ኖሯል። ሁሉም ያውቁታል ። ለካን የቤት ጉድ የሚሉት አይነት ሆኖ ተከድኖ ይብሰል አይነት ሆኗል። ለካን ቆሼ የአዲስ አበባ የተደበቀሽ ሚስጢር ኖራለች።
ለካን ቆሼ አለም ሳያውቃት ተደብቃ የምትኖረ የአዲሰ አበባ ሚስጢር ኖራላች።
ለመሆኑ የቆሼ ልጆች ዲቪ አይደርሳቸውም? አሜሪካ ሰው አያስመጣቸውም? ወይስ እነሱም የቆሼ ልጅ ነኝ ብሎ መናገር ትንሽ ከበድ ስለሚል የሌላ ሰፈር ልጆች ነን ይላሉ?
ዛሬ ያ ሁሉ ሚስጢር ቧ ብሎ ተከፍቶ አለም ቆሼን በቴላቭዥኑ መስኮት እያያት ነው።
ቆሼና የወሎ እርሃብ ተመሳሳይነት አላቸው፣ ሁለቱም ለ አለም ህዝንእይታ ተደብቀቅ ባጋጣሚ የቴለቭዥን መስኮት ህዝብን ያሳዘና እና ያስለቀሰ እይታዎችን ይዘው ቀርበዋል።
ግን ማነው ተጠያቂው? 100% መንግስት ነው ። መጀመሪያ ደረጃ ህዝቦች ለጤናቸው ሲባል የህዝብ ቆሻሻ ከሚጣልበት አካባቢ መድረስ የለባቸውም ። ምክንያቱም በዚህ ቆሻሻ መጣያ ቦታ ከሆስፒታሎች እና ከተለያዪ ቦታዎች የሚመጡ መርዞች እና በበሽታ የተበከሉ እቃወሽ ስለሚኖሩ ከዚያ የሚመጣው በሽታ ለግለሰቡ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም ህዝብ ሊተላለፍ ስለሚችል መንግስት የሚጣለውን ቆሻሻ ማንም ሰው እንዳይደርስበት በ እጥርና በዘበኛ መጠበቅ ነበረበት። ከቆሻሻው የሚገኘውን ነገር መልሶ ለመጠቀም ወይም ሪሳይክል ለማድረግ ቢፈለግ በህግና በስነ
ስርዓት ፈቃድ ያለው ድርጀት ህዝቦችን ቀጥሮ ማሰራት ይችል ነበር።
ግን መንግስትም ዝም ህዝቡም ዝም ብሎ የቆሼን ህዝብ በሚስጢር ይዞ መንቀሳቀሱ እንደ
አማራጭ ተወስዶ ዛሬ ቆሼ የሬሳ አውድማ ሆናለች። የሚያሳዝነው በሂወተ ያሉትስ የቆሼ ነዋሪወች ስንቱ ይሆን በበሽታ የተለከፈው ?ስንቱ ይሆን የቁም ሙት የሞተው?
ቆሼ የአዲስ አባባ ሚስጢር
ያሳዝናል::
በአንድ ከተማ ሁለት ዜጎች

No comments:
Post a Comment