Shop Amazon

Sunday, March 25, 2018

በመጽሐፍ ቅዱስ እንዳንበላ የተከለከልነው። Clean and Unclean Food

Clean and Unclean Food



ኦሪት ዘሌዋውያን ምዕራፍ ፲፩

እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው።
ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በሉአቸው። ከምድር እንስሶች ሁሉ የምትበሉአቸው እነዚህ ናቸው።
የተሰነጠቀ ሰኮና ያለውንና የሚያመሰኳውን እንስሳ ሁሉ ብሉ።
ነገር ግን ከሚያመሰኩት፥ ሰኮናቸው ስንጥቅ ከሆነው ከእነዚህ አትበሉም፤ ግመል ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።
ሽኮኮ ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።
ጥንቸልም ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።
እርያም ሰኮናው ተሰንጥቋል፥ ነገር ግን ስለማያመሰኳ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።
የእነዚህን ሥጋ አትበሉም፥ በድናቸውንም አትነኩም፤ በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው።
በውኃ ውስጥ ከሚኖሩት ሁሉ እነዚህን ትበላላችሁ በውኆች በባሕሮችም በወንዞችም ውስጥ ከሚኖሩት ሁሉ ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ትበላላችሁ።
በውኆቹ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ፥ በውኆች ውስጥ የሕይወት ነፍስ ካላቸው ሁሉ፥ በባሕሮችና በወንዞች ውስጥ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው።
፲፩ በእናንተም ዘንድ የተጸየፉ ይሆናሉ፤ ሥጋቸውንም አትበሉም፥ በድናቸውንም ትጸየፋላችሁ።
፲፪ ክንፍና ቅርፊትም የሌላቸው በውኃ ውስጥ የሚኖሩት ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው።
፲፫ ከወፎችም ወገን የምትጸየፉአቸው እነዚህ ናቸው፤ አይበሉም፤ የተጸየፉ ናቸው፤
፲፬ ንስር፥ ገዲ፥ ዓሣ አውጭ፥ ጭላት፥ ጭልፊት በየወገኑ፥
፲፭ ቁራ ሁሉ በየወገኑ፥
፲፮ ሰጎን፥ ጠላቋ፥ ዝዪ፥ በቋል በየወገኑ፥
፲፯፤፲፰ ጕጕት፥ እርኩም፥ ጋጋኖ፥ የውኀ ዶሮ፥
፲፱ ይብራ፥ ጥምብ አንሣ አሞራ፥ ሽመላ፥ ሳቢሳ በየወገኑ፥ ጅንጁላቴ ወፍ፥ የሌሊት ወፍ።
የሚበርርም፥ በአራት እግሮችም የሚሔድ ተንቀሳቃሽ ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፈ ነው።
፳፩ ነገር ግን ከሚበርሩት፥ አራትም እግሮች ካሉአቸው፥ ከእግሮቻቸውም በላይ በምድር ላይ የሚዘልሉባቸው ጭኖች ካሉአቸው ተንቀሳቃሾች እነዚህን ትበላላችሁ።
፳፪ ከእነርሱም እነዚህን ትበላላችሁ፤ አራቱን ዓይነት አንበጣዎች በየወገናቸው።
፳፫ ነገር ግን የሚበርር፥ አራትም እግሮች ያሉት ተንቀሳቃሽ ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፈ ነው።
፳፬ በእነዚህም ርኩስ ትሆናላችሁ፤ የእነርሱንም በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።
፳፭ ከእነርሱም በድን የሚያነሣ ሁሉ ልብሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።
፳፮ ሰኮናም ያለው፥ ነገር ግን ሰኮናው ያልተሰነጠቀ፥ የማያመሰኳም እንሰሳ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው፤ እርሱን የሚነካ ሁሉ ርኩስ ነው።
፳፯ በአራት እግሮቹ ከሚሄድ እንስሳ ሁሉ በመዳፎቹ ላይ የሚሄድ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው፤ የእርሱን በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።
፳፰ በድናቸውንም የሚያነሣ ልብሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው። እነርሱም በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው።
፳፱ በምድር ላይም ከሚንቀሳቀስ ተንቀሳቅሳሽ እነዚህ በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው፤ ሙጭልጭላ፥ አይጥ፥ እንሽላሊት በየወገኑ፥
ኤሊ፥ አዞ፥ ገበሎ፥ አርጃኖ፥ እስስት።
፴፩ ከሚንቀሳቀሱት ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩሶች የሚሆኑ እነዚህ ናቸው። ከእነርሱም የሞተውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።
፴፪ ከእነርሱም የሞተውን የሚነካ በምንም ላይ ቢወድቅ እርሱ ርኩስ ነው፤ የእንጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቁርበት ወይም ከረጢት ቢሆን የሚሠራበት ዕቃ ሁሉ እርሱ በውኃ ውስጥ ይደረግ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።
፴፫ ከእነርሱም አንዳች በውስጡ የወደቀበትን የሸክላውን ዕቃ ሁሉ ስበሩት፥ በውስጡም ያለው ሁሉ ርኩስ ነው።
፴፬ በእርሱ ውስጥ ያለው፥ ውኃም የሚፈስስበት የሚበላ መብል ሁሉ ርኩስ ነው፤ በዚህም ዕቃ ሁሉ ያለው የሚጠጣ መጠጥ ሁሉ ርኩስ ነው።
፴፭ ከእነዚህም በድን የሚወድቅበት ሁሉ ርኩስ ነው፤ እቶን ወይም ምድጃ ቢሆን ይሰባበራል፤ ርኩሶች ናቸው፤ በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ይሆናሉ።
፴፮ ነገር ግን ምንጩ፥ ጕድጓዱም፥ የውኃውም ኵሬ ንጹሐን ናቸው፤ በድናቸውን ግን የሚነካ ርኩስ ነው።
፴፯ ከበድናቸውም በሚዘራ ዘር ላይ አንዳች ቢወድቅ እርሱ ንጹሕ ነው።
፴፰ ነገር ግን በዘሩ ላይ ውኃ ቢፈስስበት፥ ከዚህ በኋላ ከበድናቸው አንዳች ቢወድቅበት፥ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።
፴፱ ለመብል ከሚሆኑላችሁ እንስሶች የሞተ ቢኖር፥ በድኑን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።
ከበድኑም የሚበላ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ርኩስ ይሆናል፤ በድኑንም የሚያነሣ ልብሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።
፵፩ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀስ ተንቀሳቃሽ ሁሉ የተጸየፈ ነው፥ አትብሉትም።
፵፪ በሆዱ የሚሳብ፥ በአራትም እግሮች የሚሳብ፥ ብዙ እግሮችም ያሉት፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ የተጸየፉ ናቸውና አትብሉአቸው።
፵፫ በሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ ሰውነታችሁን አታስጸይፉ፤ በእነርሱም እንዳትረክሱ ሰውነታችሁን አታርክሱባቸው።
፵፬ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና፤ ሰውነታችሁን ቀድሱ፥ ቅዱሳንም ሁኑ፥ እኔ ቅዱስ ነኝና፤ በምድርም ላይ በሚሳብ ተንቀሳቃሽ ሁሉ ሰውነታችሁን አታርክሱ።
፵፭ እኔ አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር ነኝ፤ እንግዲህ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ።
፵፮ የእንስሳና የወፍ፥ በውኃም ውስጥ የሚንቀሳቀስ የፍጥረት ሁሉ፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀስ የፍጥረት ሁሉ ሕግ ይህ ነው።
፵፯ በርኩስና በንጹሕ መካከል፥ የሕይወት ነፍስ ካላቸውም በምትበሉትና በማትበሉት መካከል እንድትለዩ ነው።
11 The Lord said to Moses and Aaron, “Say to the Israelites: ‘Of all the animals that live on land, these are the ones you may eat: You may eat any animal that has a divided hoof and that chews the cud.
“‘There are some that only chew the cud or only have a divided hoof, but you must not eat them. The camel, though it chews the cud, does not have a divided hoof; it is ceremonially unclean for you. The hyrax, though it chews the cud, does not have a divided hoof; it is unclean for you. The rabbit, though it chews the cud, does not have a divided hoof; it is unclean for you. And the pig, though it has a divided hoof, does not chew the cud; it is unclean for you. You must not eat their meat or touch their carcasses; they are unclean for you.
“‘Of all the creatures living in the water of the seas and the streams you may eat any that have fins and scales. 10 But all creatures in the seas or streams that do not have fins and scales—whether among all the swarming things or among all the other living creatures in the water—you are to regard as unclean. 11 And since you are to regard them as unclean, you must not eat their meat; you must regard their carcasses as unclean. 12 Anything living in the water that does not have fins and scales is to be regarded as unclean by you.
13 “‘These are the birds you are to regard as unclean and not eat because they are unclean: the eagle,[a] the vulture, the black vulture, 14 the red kite, any kind of black kite, 15 any kind of raven, 16 the horned owl, the screech owl, the gull, any kind of hawk, 17 the little owl, the cormorant, the great owl, 18 the white owl, the desert owl, the osprey, 19 the stork, any kind of heron, the hoopoe and the bat.
20 “‘All flying insects that walk on all fours are to be regarded as unclean by you. 21 There are, however, some flying insects that walk on all fours that you may eat: those that have jointed legs for hopping on the ground. 22 Of these you may eat any kind of locust, katydid, cricket or grasshopper. 23 But all other flying insects that have four legs you are to regard as unclean.
24 “‘You will make yourselves unclean by these; whoever touches their carcasses will be unclean till evening. 25 Whoever picks up one of their carcasses must wash their clothes, and they will be unclean till evening.
26 “‘Every animal that does not have a divided hoof or that does not chew the cud is unclean for you; whoever touches the carcass of any of them will be unclean. 27 Of all the animals that walk on all fours, those that walk on their paws are unclean for you; whoever touches their carcasses will be unclean till evening. 28 Anyone who picks up their carcasses must wash their clothes, and they will be unclean till evening. These animals are unclean for you.
29 “‘Of the animals that move along the ground, these are unclean for you: the weasel, the rat, any kind of great lizard, 30 the gecko, the monitor lizard, the wall lizard, the skink and the chameleon. 31 Of all those that move along the ground, these are unclean for you. Whoever touches them when they are dead will be unclean till evening. 32 When one of them dies and falls on something, that article, whatever its use, will be unclean, whether it is made of wood, cloth, hide or sackcloth. Put it in water; it will be unclean till evening, and then it will be clean. 33 If one of them falls into a clay pot, everything in it will be unclean, and you must break the pot. 34 Any food you are allowed to eat that has come into contact with water from any such pot is unclean, and any liquid that is drunk from such a pot is unclean. 35 Anything that one of their carcasses falls on becomes unclean; an oven or cooking pot must be broken up. They are unclean, and you are to regard them as unclean. 36 A spring, however, or a cistern for collecting water remains clean, but anyone who touches one of these carcasses is unclean. 37 If a carcass falls on any seeds that are to be planted, they remain clean. 38 But if water has been put on the seed and a carcass falls on it, it is unclean for you.
39 “‘If an animal that you are allowed to eat dies, anyone who touches its carcass will be unclean till evening. 40 Anyone who eats some of its carcass must wash their clothes, and they will be unclean till evening. Anyone who picks up the carcass must wash their clothes, and they will be unclean till evening.
41 “‘Every creature that moves along the ground is to be regarded as unclean; it is not to be eaten. 42 You are not to eat any creature that moves along the ground, whether it moves on its belly or walks on all fours or on many feet; it is unclean. 43 Do not defile yourselves by any of these creatures. Do not make yourselves unclean by means of them or be made unclean by them. 44 I am the Lord your God; consecrate yourselves and be holy, because I am holy. Do not make yourselves unclean by any creature that moves along the ground. 45 I am the Lord, who brought you up out of Egypt to be your God; therefore be holy, because I am holy.
46 “‘These are the regulations concerning animals, birds, every living thing that moves about in the water and every creature that moves along the ground. 47 You must distinguish between the unclean and the clean, between living creatures that may be eaten and those that may not be eaten.’”

 

No comments:

Post a Comment