Call Yebbo

የቦ ኮሚኒኬሽን ኔት ወርክ ፣ ለ25 አመታት በላይ የስራ ልምድ ያካበተው የእናንተው በእናንተው። ከምሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ የውክልና አገልግሎት መስጠት የኢትዮጵያ ፓስፖርት አገልግሎት መስጠት የቢጫ ካርድ የማውጣት አገልግሎት የታክስ አገልግሎት መስጠት (የትም የኢትዮጵያ ግዛት ይኑሩ) የጉዞ ወኪል የትርጉም ስራ አገልግሎት ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 619-255-5530 ይደውሉ።

የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት በሙሉ እንዲሁም አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አናስተካክላለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment) እንችላለን። የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViberም ሆነ Whatspp ይደውሉልን። ስልክ ቁጥራችን 619 255 5530 ነው ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Wednesday, May 9, 2018

የሰው ስጋ በልቶ ለሌሎችም ያስበላው ፓስተር





ከላይ  ከእርሱ   እንደምታዪት   ይህ  ሰው  የሰው ስጋ  በልቶ  ለሌሎችም  እንዲበሉ  ይጋብዝ  የነበረ   ግለሰብ  ነው።

ታሪኩ  እንዲህ  ነው።  የላይቤራ   ዜጋ   የሆነው እና  በላይ ቤርያ  የእርስ  በርስ ጦርነት  የብዙ  ንጹሃንን  ደም  በማፍሰስ ብቻ ሳይሆን በመብላት የታወቀው  ጀኔራል እርቃን  (GENERAL  BUTT NAKED)  የሚባለው የጦር  መኮነን  ነው።
ጄኔራሉ  በራሱ አንደበት  እንዴት  አይነት ጨካኝ እና  አረመኔ   እንደነበር  በስሩ  ይዋጉ የነበሩትን  ለጋ ወጣቶች  በአደንዛዥ  እፅ  እና ፍራቻን አስለቅቆ  ድፍረት  ይሰጣል  በሚል  ሰይጣናዊ   አስተሳሰብ  ለወታደሮቹ  የለጋ  ህጻን  (ድንግል)  ልብ ከልጆች ላይ ህይወታቸው እያለ  ከሰውነታቸው ቆርጦ  በማውጣት   ልባቸውን  ቆራርጦ ለወታደሮቹ  በማብላት  እንዲሁም  ደማቸውን  በማጠጣት የሰውን  ክብር  በሚነካ  እርህራሄ  በሌለው  ጭካኔ   ህዝብ ሲፈጅ  እንደነበር  ይናገራል።

General Butt Naked

ይህ  ጄኔራል  በራሱ  አንደበት  ያደረሰውን  ግፍ  ሲያወራ  ልክ  ገሃነብ ውስጥ ያለ  ነው የሚመስለው። እንደ  ጄኔራሉ  አገላለጥ  በላይቤራ ውስጥ   ከ 40% በላይ  የሚሆነው ህዝብ  የሰው  ስጋ  በልቷል። በጄኔራሉ  አመራር   ወታደሮቹ ሲዋጉ   የጠላት  ጦር
ከገጠሙ እና ከገደሉ ስጋውን  ተካፍለው  ይበላሉ።  በተለይ  ደግሞ  አንድ  ሰው ከሞተ   ወዲያው  የግለሰቡ  የተለያዩ  የሰውነት  ክፍሎች  ወዲያ  ተቆርጠው  የሚጠፉ  ሲሆን  በተለይ  ደግሞ  የሴት  ብልት ወዲያው  ተቆርጦ  የጠፋል።  ጄኔራሉ እንደሚለው  ብዙ የላይቤራያ  ወንዶች  ቦርሳቸው ወስጥ የደረቀ  የሴት ብልት የዘው  የዞራሉ  ምክንያቱን  ሲጠየቁ  ለደፋርነት እና  ለመልካም እድል  ይሆናል  ብለው ስለሚያምኑ  ነው።

ታዲያ  ይህ  ከጭራቅ በላይ የሆነ   ዲያቢሎስ  እንደሚለው  አንድ  ቀን   ቁጭ  ብሎ የሰይጣን  ስራውን  ሲሰራ   ከጀርባው   ነጭ  ልብስ የለበሰች  ፈረንጅ   ቆማ  ስታወራው  ያያል።  መልአክ  ማለቱ  መሰለኝ ። ይህ   እንደ  ፀሃይ  የሚያበራ  ምስል  "ልጆቼን  በባርነት  አታሰቃይ  “ አለኝ  ይላል።  ያ ምስልም   ለማየት እንኳ   የሚያስቸግር  ታላቅ ነፀብራቅ  ያለው  ሲሆን  ለጄኔራሉ  ብዙ  ማስትንቀቂያ  ሰጠና  ተሰወረ።  ከዚያም በኋላ  ጄኔራል  ዲያቢሎስ  ሄወቴ   ተቀየረ  ይላል። የሽጉጥ  ቃታ/ምላጭ  መሳብ  እንኳ  አቃተኝ ይላል ይህ  ጭራቅ።

እስከ ዛሬ   ስንቱ ሌባ፣ወንጀለኛ፣ቀማኛ፣ ተደባዳቢ፣ሴት  ደፋሪ፣ሙሰኛ እና   ለሌም  ሌላም   ፓስተር  ሆንሁ  ሲል  ማየቴን  ለምጄው  ሳስበው  ፓስተር  ማለት  ”በረኪና“  ነው ወይ  እላለሁ።  ማለትም  ግለሰቡ  የሰራውን ሀጥያት  ማፅጃ  ኬሚካል። እንደፈራሁትም   ይህ  በምድር ላይ ያሉ  ሃጥያቶችን   የሰራ  የሰይጣን  አለቃ   ሁለተኛ ሂወቱን  ፓስተር ነኝ  ብሎ  ብቅ  ብሏል።

ከ20000 በላይ  የሰው  ሂወት  ያጠፋው  ይህ  አረመኔ ይባስ  ብሎ  ባሎቻቸውን፣ወድንሞቻቸውን፣ ወላጆቻቸውን  የገደለባቸውን   ግለሰቦች ሰብስቦ የናንተ  ፓስተር ነኝ  አሁን   ተቀይሪለሁ ስሜም  ተቀይሯል  ብሎ  ከተከታዮች  ጋር የጌታችንን  ስም  እያነሳ  መቀለጃ  አድርጎታል።

ጭራሽ  ይህ  ወንጀለኛ  ጭራቅ  በሰው ልጅ  ላይ  ያደረገውን  ግፍ  በአደባባይ  ልክ  እንደ  ጀብድ  ያወራል።  ላደረሰው በደል በአደባባይ  መሰቀል  ሲገባው በሃይማኖት ሽፋን ይህ  ግለሰብ  ሌላ  የሚታረድ የዋህ  ህዝብ  ያባብላል።
አልበዛም

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon