የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Tuesday, November 10, 2020

የኦነግ ታጣቂዎችን ጨምሮ የማፊያው ሕወሓት ቡድን ልዩ ኃይል አባላት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በማድረስ ተሳትፈዋል

"የኦነግ ታጣቂዎችን ጨምሮ የማፊያው ሕወሓት ቡድን ልዩ ኃይል አባላት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በማድረስ ተሳትፈዋል" - ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ 
******************** 

በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ያደረሱ አካላት የማፊያው ሕወሓት ቡድን ልዩ ኃይል፣ የአካባቢው ሚሊሺያ እና በማይታመን መልኩ ደግሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድንም ጭምር እንደነበር ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ አስታወቁ። 

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ውጊያ እየተካሄደባቸው ያሉ የጦር ቀጠናዎችን የጎበኙት ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ፣ የሕወሓት ማፊያ ቡድን በአካባቢው በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰሜን እዝ ላይ ያደረሰውን ጥቃት በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል። 

ሌ/ጄኔራሉ ከሌሎች ጓዶች ጋር በመሆን በአካባቢው ባደረጉት ጉብኝት ማፊያው የሕወሓት ቡድን እየተናገረ እንዳለው የሰሜን እዝ ከማፊያው የሕወሓት ቡድን ጋር በማበር የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እየወጋ እንዳልሆነ ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል። 

የሰሜን እዝ ፈተና ቢገጥመውም እና እንዲሸረሸር በሆዳሞች ጥረት ቢደረግበትም የዓላማ ፅናት ያላቸው የጦሩ አባላት በጀግንነት የሕይወት መሥዋዕትነት በመክፈልም ጭምር ጁንታውን ቡድን ተፋልመዋል ነው ያሉት። 

ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ በሰሜን እዝ ላይ የደረሰውን ጥቃት ሲያብራሩ፣ እዙ በመቐለ በመሸገው ጁንታ አማካይነት ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ ወደ ማጥቃት ከመግባቱ በፊት በሰሜን እዝ ውስጥ የሚገኙ ትግርኛ ተናጋሪዎችን በመጠቀም ሰሜን እዝን ለማፈራረስ አቅዶ እንደነበር ገልጸዋል። 

የወታደሩ ራሽን እና ደመወዝ መላኩን ቀድመው የማረጋገጥ ሥራ ሠርተዋል ያሉት ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ፣ ይህ ከሆነ በኋላ የሰሜን እዝ ከየትኛውም ሠራዊት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳይኖር ሬዲዮ መገናኛውን አቋርጠዋል ብለዋል። 

ለዚህ ዓላማ መሳካትም ዋና የሬዲዮ መገናኛ ኃላፊው በማፊያው ቡድን መጠለፋቸውን እና ከዚያ በኋላ ጁንታው ጥቃት መፈፀሙን ገልጸዋል። 

ግንኙነቱ ከተቋረጠ በኋላ የ20ኛው ክፍለ ጦር አዛዥን ጨምሮ የተወሰኑ የጦር አመራሮችን ማፈናቸውን፣ በተለይም ደግሞ አጋዥ ኃይል የሚባለውን ለ21 ዓመታት የሀገሩን ዳር ድንበር ሲጠብቅ የነበረውን ሠራዊት ምንም ባልተዘጋጀበት ሁኔታ ጨፍጭፈው አስከሬኑን አውሬ እንዲበላው በማድረግ ዘግናኝ ድርጊት መፈፀማቸውን ተናግረዋል። 

የጨፈጨፏቸውን ወታደሮች አስከሬን ራቁት አድርገው እስከ ትላንትናው ዕለት እንዳይቀበር አድርገዋል ያሉት ሌ/ጄኔራሉ፣ በአስከሬኑ ላይ ሲጨፍሩ እንደነበሩም ገልጸዋል። 

ከጭፍጨፋ የተረፉ የሰሜን እዝ ወታደሮችን ልብስ አስወልቀው ራቁታቸውን ወደ ኤርትራ ሠራዊት እንዲቀላቀሉ ማድረጋቸውን፣ ድንበሩን እየጠበቀ የነበረው የኤርትራ ሠራዊት ግን ራቁታቸውን ለሔዱት የሠራዊታችን አባላት ልብስ ማልበሱን መረጃው እንዳላቸው ጠቁመዋል። 

የሰሜን እዝ በርካታ ጥፋቶች ቢፈፀምበትም በተለያዩ መንገዶች ከሌሎች የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር ግንኙነት ፈጥሮ በአሁኑ ሰዓት በእልህ እና ለባንዲራው ባለው ታማኝነት የጠላት ጦርን በተለያዩ ግንባሮች እየደመሰሰ እንደሆነ እና በየቀኑ አዳዲስ ድሎችን እያስመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል። 

በአጠቃላይ የሞት ድግስ የተደገሰለት የሰሜን እዝ ሁሉንም ድል አድርጎ የሀገር ዳር ድንበረን እያስጠበቀ የትግራይን ሕዝብ ከዚህ ግፈኛ ጁንታ ነፃ ለማውጣት እየሠራ እንደሆነ እና ባንዲራውን ከፍ እያደረገ ነው ብለዋል። 

በጥላሁን ካሳ 

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon