የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Sunday, November 15, 2020

አዲስ የድል ዜና ከራያ አላማጣ‼️



"ኢትዮጵያ ትቀጥላለች የከሃዲው ትህነግ ቡድን ይፈርሳል።"የራያ አላማጣ ከተማ ነዋሪዎች

በጀግኖች የመከላከያ ሰራዊታችን የአማራ ልዩ ኃይልና ሌሎች የክልላችን የፀጥታ ኃይሎች በደረሰበት ሽንፈት በዛሬው እለት ከሃዲው የትህነግ ቡድን ራያ አላማጣን ለቆ ፈርጥጧል።

ደስታቸውን ሲገልፁ ያገኘናቸው የራያ አላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ለመከላከያ እና ለአማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ አክብሮትና ፍቅራቸውን በወሎ የእንግዳ አቀባበል ስርአታቸው አሳይተዋል።

የዝግጅት ክፍላችን ያነጋገራቸው የራያ አላማጣ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለፁልን ላለፉት በርካታ አመታት የከሃዲው ትህነግ ቡድን ስንሰቃይ እና በገዛ ሀገራችን እንደ ባዕድ ተቆጥረን ስንሳደድ ቆይተናል።

ዛሬ ግን ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊ፣ የአማራ ልዩ ኃይል እንዲሁም በሌሎች የፀጥታ አካላት ነፃ ወጥተናል ኢትዮጵያ ትቀጥላለች የከሃዲው ትህነግ ቡድን ይፈርሳል ብለዋል።

ነዋሪዎቹ ጨምረውም በገዛ መሬታችን እኛን እያፈናቀሉ ከሌላ አካባቢ ለመጡ የትህነግ ቡድኖች መሬታችንን ሲያሳርሱብን ቆይተዋል ሲሉ በምሬት ገልፀዋል።

የመከላከያ እና የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በበኩላቸው ህዝቡ ያደረገልን አቀባበልና ድጋፍ በዘራፊው ትህነግ ምን ያህል ተጨቁነው እንደነበር ያሳያል ብለዋል።

"ጉዟችን ከሃዲው የትህነግ ቡድን እስኪደመሰስ ይቀጥላል‼️"

አማራ ፖሊስ ኮሚሽን

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon