የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Friday, November 6, 2020

ስግብግቡ ጁንታ በህወሓት ውስጥ የመሸገው ኃይል ላይ የተወሰደው የመጀመሪያው ዙር ኦፕሬሽን በስኬት እንደተጠናቀቀ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ

ስግብግቡ ጁንታ በህወሓት ውስጥ የመሸገው ኃይል ላይ የተወሰደው የመጀመሪያው ዙር ኦፕሬሽን በስኬት እንደተጠናቀቀ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ
*************

ባለፉት ሁለት ቀናት ስግብግቡ ጁንታ በህወሓት ውስጥ የመሸገው ኃይል፣ ለስልጣን የሚስገበገበው፣ ለገንዘብ የሚስገበገበው፣ ለሀገር ሉዐላዊነት ለሕዝቦች ደህንነት ደንታ የሌለው ኃይል በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመከላከያ ሰራዊት እንዲሁም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፖሊስ ሰራዊት ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ይታወሳል።

ይህ ጥቃት ድንገተኛ ቢሆንም የመጀመሪያው የመከላከል እቅድ ሙሉ ለሙሉ በስኬት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል።

የእቅዱ ዋነኛ አላማዎች 1ኛ ጥቃቱን መግታት- የመጀመሪያው ዓላማ ጠላት በሁሉም አቅጣጫ ጥቃት እየሰነዘረ በህዝብ፣ በሰራዊቱ፣ በፖሊስ ላይ እና በአንዳንድ ወሳኝ የመሰረተ ልማቶች ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት መግታት ነበር። 

ከዚህ አንፃር በተለያየ አካባቢ ይገኝ የነበረ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ወደ ስፍራው በማንቀሳቀስ የጠላትን ጉዞን ሙሉ ለሙሉ በማስቆም ተጨማሪ ጥቃት መሰንዘር ወደማይችልበት ደረጃ ማድረስ ተችሏል ብለዋል።

ሁለተኛው አላማ የመከላከያ እና የፖሊስ ሰራዊት የደረሰበትን ጥቃት ተከትሎ ይህንን ኃይል የመታደግ እና ወሳኝ ሀገራዊ ሀብቶች አና ትጥቆች የመታደግ ስራ እንደነበር ተገልጿል።

ከዚህ አንፃርም በባድመ ግንባር፣ በፆረና እና በዛላንበሳ በዋና ዋና ስፍራ ተሰልፈው ያሉ የሰራዊት አባላት እና ትጥቆች ሙሉ ለሙሉ ከጠላት ፍላጎት ውጭ ለማድረግ ተችሏል።

 
3ኛው አላማ የጠላትን የማድረግ አቅም ማዳከም ነው። የጠላት ኃይል የኢትዮጵያ ህዝብ ከሌለው ሀብት ላይ ቀንሶ ሀገሩን ለመከላከል የገዛቸውን ዋና ዋና ትጥቆች፣ ሚሳኤሎች፣ ሮኬቶች በመጠቀም ጥፋት ማካሄድ እንዳይችል አቅሙን ማዳከም ነበር።

በዚህም ሦስቱ ዓላማዎች መቶ በመቶ መሳካታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም በዳንሻ ግንባር ያለውን ጠላት ሙሉ ለሙሉ በመደምሰስ አካባቢውን መቆጣጠር መቻሉንም አስታውቀዋል።

በቀጣይም ስግብግቡ ጁንታ ሙሉ ለሙሉ ለሕግ እስከሚቀርብ ድረስ የሚደረገው እራስን እና ሀገርን የመከላከል ዘመቻ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አረጋግጠዋል። 

የአየር ሀይሉ በወሰደው እርምጃም በተለያዩ ስፍራዎች ላይ የነበሩ ሮኬቶችን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ለማውደም መቻሉንም ገልፀዋል።

እነዚህ ሮኬቶች እስከ 300 ኪሎ ሜትሮች መወንጨፍ የሚችሉ በመሆናቸው እና በወንጀለኛው ቡድን ሮኬቶቹን የመጠቀም ፍላጎት በመኖሩ በመቀሌ እና አካባቢዋ በነበረው የከባድ መሳሪያ ማስቀመጫ ላይ የአየር ኃይሉ እርምጃ እንዲወስድ መደረጉ ተገልጿል።

በአስማማው አየነው 

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon