የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Friday, November 13, 2020

በምዕራብ ሸዋ ዞን በተደረገው ኦፕሬሽን የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ

በምዕራብ ሸዋ ዞን በተደረገው ኦፕሬሽን  የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ
*******************************

በምዕራብ ሸዋ ዞን በቅርቡ በተደረገው ኦፕሬሽን 5 የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፣ 7 ደግሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ለእነዚህ አካላት መረጃ አቀብለዋል የተባሉ 45 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገልጿል፡፡

በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ በቅርቡ በተደረገው ኦፕሬሽን በቡድኑ የህዝቡን ሰላም ለማወክ የተዘጋጁ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በጸጥታ ኃይሎችና በህዝቡ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በምዕራብ ሸዋ ዞን የፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራና ፍትሕ አሰጣጥ ኃላፊ ኮማንደር ኑረሳ አከና ገልጸዋል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉ የጦር መሳሪያዎች  4 ክላሽ ጠመንጃዎች፣ 5020 የክላሽ ጥይቶች፣ 5 ኋላቀር የጦር መሳሪያዎች፣  9 ሽጉጦች፣ 16 ቦምቦች እና 2 ፈንጂዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡ 

ከተያዙት ፈንጂዎች ውስጥ አንዱ ድልድዮችና መኪኖች ላይ ጥቃት ለመፈጸም የሚውል ነው ተብሏል፡፡ 

የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊትና የኦሮሚያ ፖሊስ አልባሳትና የተለያዩ ስለት ያላቸው እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon