የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Monday, November 16, 2020

ዛሬ በአዲስ አበባ ፒያሳ ደጎል አደባባይ የተፈጠረው ምንድን ነው?

ህዳር 7፣2013

ዛሬ በአዲስ አበባ ፒያሳ ደጎል አደባባይ  የተፈጠረው ምንድን ነው? 

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መግለጫ ሙሉ ቃል የሚከተለው ነው፦

በአራዳ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ደጎል አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ  ፖሊስ ፈንጂ አመከነ በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተለቀቀው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሰታወቀ፡፡

ዛሬ ህዳር 7፣2013 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ፒያሳ ደጎል አደባባይ አካባቢ ከሰዓት በፊት በጎዳና ላይ ተዳዳሪ የሆነ አንድ ግለሰብ በማዕድን ውኃ መያዣ ላስቲክ ድራፍት በመግዛት ለመጠጣት ወደ አንድ ጥግ መሄዱ ያጠራጠራቸው በአካባቢው በጫማ መስዋብ ሥራ ላይ ተሰማሩ ወጣቶች ለፖሊስ ባደረሱት ጥቆማ የአካባቢው ፖሊስ እና የፌዴራል ፖሊስ ፈንጂ አምካኝ ባለሙያዎች ቦታው ላይ በመገኘት ተከሰተ የተባለውን  ማረጋገጥ መቻላቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር አካባቢያቸውን በንቃት የሚጠብቁ ወጣቶች መበራከታቸው የሚደነቅ ቢሆንም ለፖሊስ የሠጡትን መረጃ በመንተራስ ፖሊስ ባረጋገጠው መሰረት በላስቲክ የተሞላ ድራፍት ቢራ እንጂ ፈንጂ አለመሆኑን ህብረተሰቡ እዲገነዘብ ኮሚሽኑ አሳስቦ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በሚለቀቁ  ሐሰተኛ መረጃዎች እንዳይደናገጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡


No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon