ዛሬ ምሽት 5:00 ሰዓት ገደማ በባህር ዳር መኮድ እና በጎንደር አዘዞ አካባቢ በተቀራራቢ ሰአት መለስተኛ ፍንዳታ መፈፀሙን የክልሉ መንግስት አስታውቋል፡፡
በአሁኑ ሰአት ሁሉም ነገር ሰላም መሆኑንም እንዲሁ ።
የጠላት ኃይል ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ የሽብር ስራ እየሰራ ስለሆነ ጦርነት ውስጥ ያለን መሆኑ ታውቆ ህብረተሰቡ ተረጋግቶ እራሱንና አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ የክልሉ መንግስት አሳስቧል ሲል የአማራ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል ፡፡
Comments