የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Tuesday, November 17, 2020

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን "ከሀገር መከላከያ ጎን እንቆማለን" በሚል ለሰራዊቱ ያላትን ድጋፍ ገለጸች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን "ከሀገር መከላከያ ጎን እንቆማለን" በሚል  ለሰራዊቱ ያላትን ድጋፍ ገለጸች
*********************
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን "ከሀገር መከላከያ ጎን እንቆማለን" በሚል  ለሰራዊቱ ያላትን ድጋፍ ገለጸች።

"ከሀገር መከላከያ ጎን እንቆማለን" በሚል  መሪ ቃል የተላለፈውን ጥሪ በመቀበል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ለመከላከያ ሰራዊቱ ያለውን ድጋፍና ክብር ገልጿል።

በመርሐ ግብሩ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በጸሎት የተከፈተ ሲሆን ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትም በመርሀ ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል።

በመርሐግብሩ የጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ከመከላከያ ጎን እንደሚቆሙ ማረጋገጣቸውንና ለሀገር ሰላምና አንድነትም የበኩላቸውን እንደሚያበረክቱ ቃል መግባታቸውን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

"ለመከላከያ ክብር እቆማለሁ" በሚል መሪ ሃሳብ በኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የተዘጋጀው ይህ መርሐ ግብር በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተካሄደ ሲሆን የአገር መከላከያ ሠራዊት እየወሰደ ላለው የሕግ ማስከበርና የአገር ህልውና የማስጠበቅ እርምጃ ድጋፍ ለመግለፅ ያለመ ነው።

Source BBC

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon