Call Yebbo

YebboTax Ethiopian Banner
ለአሜሪካ ታክስ ከፋዮች፣ አመታዊ ታክሳችሁን፣ ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Backtax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amdment) ካላችሁ የትም ሆናችሁ ማሰራት ትችላለችሁ።የኢትዮጵያ ፓስፖርት፣ የቢጫ ካርድ፣ ውክልና፣ የትርጉም ስራ ይፈልጋሉ? በViber/WhatsApp በ619 255 5530 ደውሉልን። info@yebbo.com Yebbo.com

Sunday, November 15, 2020

በአዲስ አበባ ከተማ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተሰበሰበ

በአዲስ አበባ ከተማ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተሰበሰበ
***************
ባለፉት ሁለት ቀናት ከአዲስ አበባ ለመከላከያ ሠራዊቱ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የከተማ አስተዳደሩ ምክት  ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

የቦሌ እና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች እና አርሶ አደሮች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ143 በላይ በሬዎች፣ በግ እና ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን ጨምሮ ከ95 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደርገዋል።

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የቦሌ እና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች እና አርሶ አደሮች እንዲሁም ባለፉት ጥቂት ቀናት ደግሞ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ የመንግሥት ሠራተኞች እና መላው ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰጡት ሞራል እና ድጋፍ እንደሚያኮራ ገልጸዋል።

ለመከላከያ ሠራዊቱ ለተሰጠውም ድጋፍ ምክትል ከንቲባዋ አመስግነዋል።

ክፍለ ከተሞቹ ያደረጉትን የገንዘብ፣ የሰንጋ በሬ እና ሌሎች ድጋፎችን ወ/ሮ አዳነች ለኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሚንስትር ደኤታ ወ/ሮ ማርታ ሉጂ እና ለከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች አስረክበዋል።

በይድነቃቸው ሰማው    

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon