Call Yebbo

YebboTax Ethiopian Banner
ለአሜሪካ ታክስ ከፋዮች፣ አመታዊ ታክሳችሁን፣ ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Backtax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amdment) ካላችሁ የትም ሆናችሁ ማሰራት ትችላለችሁ።የኢትዮጵያ ፓስፖርት፣ የቢጫ ካርድ፣ ውክልና፣ የትርጉም ስራ ይፈልጋሉ? በViber/WhatsApp በ619 255 5530 ደውሉልን። info@yebbo.com Yebbo.com

Sunday, November 15, 2020

የህወሓት ጽንፈኛ ቡድን የመከላከያ ሰራዊትና የኤርትራ ሰራዊት የደንብ ልብስን እያመረተ በማጭበርበር ስራ ውስጥ መግባቱ ተገለጸ

የህወሓት ጽንፈኛ ቡድን የመከላከያ ሰራዊትና የኤርትራ ሰራዊት የደንብ ልብስን እያመረተ በማጭበርበር ስራ ውስጥ መግባቱ ተገለጸ
------------------------------------------------
የህወሓት ጽንፈኛ ቡድን የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊትና የኤርትራ ሰራዊት የደንብ ልብስን እያመረተ የማጭበርበር ስራ ውስጥ መግባቱ ተገለጸ፡፡

ከዋልታ ጋር ቆይታ ያደረጉት በሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢንዶክተርነሽን ዳይሬክተር ተወካይ ብርጋዴል ጄነራል ኩማ ሚዴቅሳ ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን እየደረሰበት ያለውን ሽንፍት ተከትሎ የኤርትራ ሰራዊት የደንብ ልብስ አመሳስሎ በማምረትና ቅጥረኞችን በማልበስ በቁጥጥር ስር አዋልኩ የሚል ድራማ እየተወነ ነው ብለዋል፡፡

በትግራይ ክልል በሚገኘው አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ በህወሓት ውስጥ የሚገኘው ጽንፈኛ ቡድን የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊትና የኤርትራ ሰራዊት የደንብ ልብስን አመሳስሎ እያመረተ እንደነበረ ይታወቃል ያሉት ብርጋዴል ጄነራል ኩማ፣ የጽንፈኛ ቡድኑ ገና ብዙ ማጭበርበሪያ ስራዎችን እየሰራ በመገናኛ ብዙኃን ሊያስተላልፍ ስለሚችል ህዝቡ ይህን ሊረዳ ይገባል ብለዋል፡፡

ጽንፈኛው ቡድኑ እርስ በእርስ የሚጋጩ የሀሰት ወሬዎችን መንዛቱን እንደቀጠለ እና ለሚሰራቸው ወንጀሎች ሌላን አካል ተጠያቂ ለማድረግ እንደሚጥር ተናግረዋል፡፡

ጽንፈኛ ቡድኑ በኤርትራ መንግስት እንደተመታ አድርጎ የሀሰት ወሬ እየነዛ ነው የተባለ ሲሆን፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከኢትዮጵያም አልፎ ሰላምንና ደህንነትን በማስጠበቅ በኩል ይታወቃል፤ የማንንም የውጪ ጣልቃ ገብነት አይፈልግም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ሀገር መከላከያ ሰራዊት በደረሰበት ጥቃት ቁጭት ውስጥ ገብቶ ይህን ጽንፈኛ ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰራ ነው ያሉት ብርጋዴል ጄነራል ኩማ ህዝቡ የከሃዲው ቡድን የሚነዛውን የሀሰት ወሬ ወደ ጎን በመተው ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ይህ ጽንፈኛ ቡድን የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብስንም አመሳስሎ በማምረት ለጥፋት ስራው ተጠያቂ ለማድረግ እየጣረ በመሆኑ ህብረተሰቡ በንቃትና በጥንቃቄ አካባቢውን እንዲቃኝ ብርጋዴር ጄነራሉ አሳስበዋል፡፡

(በመስከረም ቸርነት)

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon