A Yebbo Global Information Hub

EthioVibes Global

World travel, documents, money, auto, food, culture, history, sports, diaspora, business and technology.

Advertisement

በራያ አላማጣ ግንባር ጀግናው መከላከያ ሰራዊት በዛሬው እለት ከፍተኛ ድልን ተቀዳጀ።

Published
ሕዳር 8 ቀን 2013

በራያ አላማጣ ግንባር ጀግናው መከላከያ ሰራዊት በዛሬው እለት ከፍተኛ ድልን ተቀዳጀ።

ጠላት ለህብረተሰቡ ልማት መዋል ሲገባቸው ለምሽግ መስሪያ ሲጠቀምባቸው የነበረውን አንድ ዶዘር ፣ አንድ እስካቫተር ፣  አንድ ሎደር እና አንድ ፒካፖችን ጥሎ ፈርጥጧል ።

አንድ ዙ23 አየር መቃወሚያም በቁጥጥር ስር መዋሉን ፣ የደቡብ እዝ የሰው ሀብትና ሚዲያ ስራዎች አስተባባሪ ኮ/ል ደጀኔ ፀጋዬ ገልፀዋል።
በተጨማሪም ብዙ የጥፋት ቡድኑ ታጣቂ የተደመሠሠ ሲሆን ፣ በርካታ ቁስለኞችን ይዞ ሊሸሽ ቢሞክርም ጀግናው አየር ሀይላችን ተከታትሎ መደምሰሱን ተናግረዋል።

የሰራዊት አባላቱ በሰጡት አስተያየት ፣ እየተመዘገበ ባለው ድል መደሰታቸውንና ወደፊትም ጁንታውን በመደምሰስና ህግን ለማስከበር ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ንጉሴ ውብሊቀር  ( ከግዳጅ  ቀጣና )
ፎቶግራፍ  ንጉሴ ውብሊቀር

Comments