Saturday, December 5, 2020

የወታደሯ የ3 ቀናት የመቃብር ውስጥ ቆይታ።

የወታደሯ የ3 ቀናት የመቃብር ውስጥ ቆይታ። 
የወታደሯ የ3 ቀናት የመቃብር ውስጥ ቆይታ። 
የወታደሯ የ3 ቀናት የመቃብር ውስጥ ቆይታ

****************** 

መ/ወ/ር ተስፋነሽ ጋቢሳ ትባላለች። የመከላከያ ሠራዊቱ ልዩ ኃይል አባል ናት፡፡ ጁንታው በከፈተው ውጊያ ለመፋለም በራያ ግንባር ከክፍሏ አባላት ጋር ተሰልፋ በርካታ ግዳጆችን በድል ተወጥታለች።

ጠላት ለዓመታት ያዋጋኛል ብሎ እንዳዘጋጀው በወታደራዊ ጠበብቶቹ በግንባሩ መሪ ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ እና ሌሎች አመራሮች የተመሰከረለት ልዩ ቦታው አዲ ቀይህ የተባለው ቦታ ላይ ለ3 ቀናት በተደረገው ፍልሚያ በጀግንነት እየተዋጋች ሳለ ያልጠበቀችው ሁኔታ ገጠማት። 

በዚህ ቦታ ላይ ጠላት ሙሉ ኃይሉን ተጠቅሞ መዋጋት በመጀመሩ እንደ ሌሎች ምሽጎች በቀላሉ መስበር ካለመቻሉም ባሻገር፣ ጠላትን ለመደምሰስ የገባውን የወገን ጦር ለመቁረጥ መልሶ ማጥቃት በማድረጉ ወገን የኃይል ሚዛኑን ለማመጣጠን እና ሌሎች ወታደራዊ ጥበቦችን ለመጠቀም ሲባል ከጠላት ከበባ ሰብረው እንዲወጡ ሲደረግ መ/ወ/ር ተስፋነሽ በጠላት ቀጣና ተቆርጣ ትቀራለች። 

ወ/ር ተስፋነሽ ወገን አሸንፎ ሞሽጉን እንደሚሰብር ሙሉ እምነት ስለነበራት፣ የታጠቀችውን ስናይፐር ጨምሮ መሬቱን ቆፍራ ራሷን ጉድጓድ ውስጥ ትቀብራለች።  አፈሩን በእጆቿ በላይዋ ላይ በመመለስ ከመሬቱ ጋር በሚገባ ትመሳሰላለች። 

በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች ብዙ የጁንታው ታጣቂዎች በላይዋ ላይ እየተረማመዱ ከወዲያ ወዲህ ይመላለሱባታል። 

መማረክን ከሞት በላይ የምትፈራው እና ድሉን ሳታይ መሞት የማትፈልገው ጀግናዋ መ/ወ/ር ተስፋነሽ ያላት አማራጭ ሁሉንም ችላ ዝም ማለት ብቻ ነበር።

ነገር ግን ጁንታው ከአጠገቧ ላይ ዲሽቃውን ሲጠምደው፣ አንዱ የዲሽቃው መቋሚያ እግር ከተቀበረችበት አቅራቢያ ላይ አረፈ።  ዲሽቃውም ቦታውን ሳይለቅ ከአቅራቢያዋ እየተኮሰ 3 ቀናት ተቆጠሩ።

በእነዚህ ቀናት ራሷን እንደ ሙት ያለ ምንም እንቅስቃሴ ትንፋሿን አምቃ ምድር ውስጥ ሳለች ከፍተኛ ውጊያ ከተካሄደ በኋላ ሠራዊቱ ምሽጉን ሰብሮ ድል ማድረጉን የዲሽቃው መቋሚያ እግርም እሷ ካለችበት ጉድጓድ አካባቢ መነሣቱን አወቀች፡፡

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ራሷን ከቀበረችበት በማስነሣት አካባቢውን ስትመለከት ጀግኖች ጓዶቿ ጁንታውን አባርረው ቦታውን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረውታል። 

እሷ ብታውቃቸውም እነሱ ግን ሙሉ ሰውነቷ ከአፈር ስለተመሳሰለ አላወቋትም ነበርና 'እጅ ወደ ላይ' የሚል ድምፅ ሰማች።

እሷም እጆቿን አንሥታ 'ወገን ነኝ ' የሚል ድምፅ በደስታ ብዛት ተውጣ አሰማች። እነሱም ወደ ኋላ በመውሰድ ከ3 ቀናት በኋላ እህል እና ውኃ እንድትቀምስ አድርገዋታል።
መ/ወ/ር ተስፋነሽ ጋቢሳ በአሁኑ ወቅት በሙሉ ጤንነት ወደ መደበኛ ተግባሯ ተመልሳ ጁንታውን ለደምሰስ እየተፋለመች ትገኛለች ሲል ከመከላከያ ሠራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት በሙሉ እንዲሁም አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አናስተካክላለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment) እንችላለን። የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViberም ሆነ Whatspp ይደውሉልን። ስልክ ቁጥራችን 619 255 5530 ነው ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Translate

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon

Call Yebbo

የቦ ኮሚኒኬሽን ኔት ወርክ ፣ ለ25 አመታት በላይ የስራ ልምድ ያካበተው የእናንተው በእናንተው። ከምሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ የውክልና አገልግሎት መስጠት የኢትዮጵያ ፓስፖርት አገልግሎት መስጠት የቢጫ ካርድ የማውጣት አገልግሎት የታክስ አገልግሎት መስጠት (የትም የኢትዮጵያ ግዛት ይኑሩ) የጉዞ ወኪል የትርጉም ስራ አገልግሎት ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 619-255-5530 ይደውሉ።