የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Saturday, January 23, 2021

ከመተከል ተፈናቃዮች የተመለመሉ ሚሊሻዎችን በማደራጀት ማኅበረሰቡን ከጥቃት መከላከል የሚያስችል አደረጃጀት እንዲፈጠር ተወስኗል፦ አቶ ደመቀ መኮንን

ከመተከል ተፈናቃዮች የተመለመሉ ሚሊሻዎችን በማደራጀት ማኅበረሰቡን ከጥቃት መከላከል የሚያስችል አደረጃጀት እንዲፈጠር ተወስኗል፦ አቶ ደመቀ መኮንን
********************* 

ከመተከል ከተፈናቀሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተመለመሉ ሚሊሻዎችን በማደራጀት ማኅበረሰቡን በዘላቂነት ከጥቃት መከላከል የሚያስችል አደረጃጀት እንዲፈጠር መወሰኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ። 

አቶ ደመቀ ይህን የገለጹት ከመተከል የተፈናቀሉ እና በቻግኒ ራንች በተባለ መጠለያ ጣቢያ ከተጠለሉ ተጎጂዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ነው። 

የአካባቢውን ሰላም በማረጋገጥ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ እና ከማኅበረሰቡ ጋር እርቅ የማካሄድ ሥራ እንደሚሠራም ተናግረዋል። 

መንግሥት በተለያየ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች ቅድሚያ በመስጠት የማቋቋም ሥራ እየሠራ ይገኛል ያሉት አቶ ደመቀ፣ የመተከል ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም ቁርጠኛ መሆኑንም ገልጸዋል። 

በውይይቱ ላይ በቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ተስፋዬ ቤልጅጌ፣ የኮማንድ ፖስቱ ዋና አስተባባሪ ሌ/ጄ አስራት ዴኔሮ፣ አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። 

በራሔል ፍሬው
Demeke Mekonnen: It has been decided to organize militias to recruit IDPs from the plant.
 *********************

 Deputy Prime Minister and Minister of Foreign Affairs, Demeke Mekonnen, said it has decided to form a militia to protect the community in a sustainable manner by organizing militias recruited from the displaced communities.

 Demeke made the remarks in an interview with victims displaced from the plantation and sheltered at Chagni Ranch.

 He said efforts will be made to ensure peace in the area, repatriate IDPs and reconcile with the community.

 Demeke said the government is working to rehabilitate the displaced people for various reasons.

 Federal and regional officials, including Tesfaye Beljige, coordinator of the post-zone command post in Beni Shangul Gumuz, Lt. Gen. Asrat Denero, artist and activist Tamagne Beyenen, were present at the meeting.

 By Rachel Fruit

 /


/

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon