Friday, December 31, 2021

Ethiopian Airlines will start flying to Berbera from February 8 ********************

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከየካቲት 8 ጀምሮ ወደ በርበራ መብረር ይጀምራል
********************

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ የሶማሌላንድ የወደብ ከተማ በርበራ ከየካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ።

አየር መንገዱ ወደ በርበራ በሳምንት ሶስት ጊዜ በረራ ለማድረግ እቅድ እንዳለውና ወደፊት የበረራ ቁጥሩን እንደሚጨምር ለኢዜአ በላከው መግለጫ አመልክቷል።

የበርበራ ከተማን እንደ መዳረሻ መጨመሩ በምስራቅ አፍሪካ አገራት መካከል ያለውን የንግድ ትስስር እንዲጠናከር ከማድረግ ባለፈ በአውሮፓ፣ እስያ፣ አፍሪካ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካና መካከለኛው ምስራቅ ያሉት ዓለም አቀፍ ተጓዦቹ በቀጠናው ያላቸውን ተደራሽነት ቀላልና ምቹ የማድረግ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጿል።

በኤደን ባህረ ሰላጤ ምዕራባዊ አቅጣጫ የምትገኘው የሶማሌላንድ የወደብ ከተማ በርበራ ለምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የባህር ንግድ በር አማራጭ በመሆን ወሳኝ አስተዋጽኦ እንደምታበረክት ይገለጻል።

ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብ 19 በመቶ ድርሻ ያላት ሲሆን በወደቡ ላይ መርከቦቿን ከወራት በፊት ማሰማራት መጀመሯ ይታወቃል።


No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon