የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Sunday, January 2, 2022

የባህርዳር ሀገረ ስብከት መጭውን የልደት(የገና) በዓልን ምክንያት በማድረግ የትግራይ ወራሪ ቡድን ባደረሰው ጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች ማቋቋሚያ የሚውል የ4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

የባህርዳር ሀገረ ስብከት መጭውን የልደት(የገና) በዓልን ምክንያት በማድረግ የትግራይ ወራሪ ቡድን ባደረሰው ጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች ማቋቋሚያ የሚውል የ4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።
*****
የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ዻዻስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፅዕ አቡነ አብርሃም እንደገለፁት ሰው በችግር ጊዜ መረዳዳት በጨነቀ ጊዜ ማጽናናት ከእግዚአብሔር የተሰጠን ፀጋ በመሆኑ በሀገረ ስብከቱ ስር ያሉ 40 የሚሆኑ ገዳማትና አድባራት ከነ አገልጋዮች በማስተባበር ካሁን በፊት ሲያደርግ ከቆየው ድጋፍ በተጨማሪ ከሀገረ ስብከት እስከ ታችኛው አጥቢያ ቤተክርስቲያን ድረስ የሚገኙ ምዕመናንና ምዕመናትን የተሳተፉበት ድጋፍ መሆኑን ተናግረዋል።

ቤተ ክርስቲያኗ ከጸሎት ባለፈ ለተራቡ፣ለተጠሙና ለተራዙ ወገኖቻችን መድረስ፣ ለፈረሱ የትምህርት፣ የጤና እና የኃይማኖት ተቋማት እንዲሁም የግለሰብና የመንግስት ቤቶችን መልሶ መጠገን ተገቢ በመሆኑ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

ብፅዕነታቸው አያይዘውም ሰው ለሰው መዳህኒት መሆኑን ወደ ጎን በመተው አጥፊ ከሚሆን ይልቅ የሚጠቅመው ክፉውን ጊዜ ተደጋግፎና ተከባብሮ በማሳለፍ እና ክፍውን በጋራ ሀይ በማለት ለጋራ ከሰላምና ልማት በጋራ መቆም እንደሚገባ አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ በበኩላቸው በብፅዕ አቡነ አብርሃም የሚመራው የባህርዳር ሀገረ ስብከት ከዚህ በፊት የህልውና ዘመቻው ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ ህዝቡን በጸሎት ከመጠበቅ ባሻገር እየተደረገ ያለው የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ ከሚጠበቀው በላይ መሆኑን አስታውሰዋል።

በዛሬው ዕለትም መንፈሳዊና የቁሳዊ እንዲሁም ስነ ልቦናዊ ጉዳት ለደረሰባቸውና በከፍተኛ ችግር ውስጥ ለሚገኙ የጦርነት ቀጠና ሆነው ለቆዮ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋሚያ የሚውል የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ 4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በማድረጋቸው በባህርዳር ከተማ ህዝብና መንግስት ስም የከበረ ምስጋና ያላቸው መሆኑን ገልፀዋል።

በመሆኑም ከተማ አስተዳደሩ በሚያከናውናቸው የህዝብ ልማትና ሰላም ግንባታ ተግባራት ላይ ሀገረ ስብከቱ ከጎናቸው እንደማይለይና የተጀመረውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያላቸውን የፀና እምነት ገልፀዋል ።

መረጃው የባህርዳር ከተማ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ነው።

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon