የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Tuesday, January 4, 2022

ደቡብ አፍሪካውያን ወጣቶች ኢትዮጵያ የምታደርገውን ትግል በሁሉም መስክ ይደግፋሉ፦ ላታታ ላክስ

ደቡብ አፍሪካውያን ወጣቶች ኢትዮጵያ የምታደርገውን ትግል በሁሉም መስክ ይደግፋሉ፦ ላታታ ላክስ
**********************

ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የደቡብ አፍሪካው የማህበረሰብ መሪ ላታታ ላክስ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እና ከፐብሊክ ዲኘሎማሲ ቡድን ተወካዮች ጋር ተወያይቷል።

በውይይታቸውም አምባሳደር ዲና የኢትዮጵያን ድምፅ ለማሰማት እና ለመደገፍ ላክስ እያደረገ ላለው ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

ወጣቱ ላክስ የውጭ ሃይሎች በኢትዮጵያ ላይ የሚከተሉትን ጣልቃ ገብነት በተደጋጋሚ ሲያወግዝ የነበረ ሲሆን ደቡብ አፍሪካ ላይ በነበረው የበቃ #nomore እንቅስቃሴም ሰፊ ተሳትፎ ሲያደርግ ቆይቷል።

ወጣቱ ያለውን ተሰሚነት በመጠቀም በቀጣይም ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲቀጥል አምባሳደር ዲና ጠይቀዋል።


ወጣቱ ደቡብ አፍሪካዊ ላክስ በበኩሉ የነፃነት ምልክት በሆነችው ኢትዮጵያ መገኘቱ ልዩ ደስታ እንደፈጠረበት ተናግሯል።

ኢትዮጵያ የገጠማትን ፈተና በሁሉም መስክ እንድትወጣ ወጣቶች መሪ ሃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው ተናግሯል።

እርሱ እና ሌሎች ደቡብ አፍሪካውያን ወጣቶች ኢትዮጵያውያን የሚያደርጉትን ትግል በሁሉም መስክ እንደሚደግፍ ላታታ ላክስ ገልጿል።

ላክስ በሚኖርበት አካባቢ የሶዌቶ ማህበረሰብን በማደራጀት በሚያደርጋቸው ንቅናቄዎች ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ የሚገኝ ወጣት ነው።

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon