Tuesday, January 4, 2022

.ለጠላት የእሳት ነበልባል የሆኑት አባት እና ልጅ

ለጠላት የእሳት ነበልባል የሆኑት አባት እና ልጅ

አቶ ጋሻዉ ሹምዬ ይባላሉ፤ በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ወረዳ የድብ ባሕር ቀበሌ ነዋሪ እና የስምንት ልጆች አባት ናቸዉ። አብሮ ዘማች የበኩር ልጃቸው ደግሞ ደረጀ ጋሻው ይባላል፡፡ አባት እና ልጅ ሀገር ለማፍረስ ወደ አካባቢያቸው የመጣዉን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በምን መልኩ መደምሰስ እና መቀበሪያውን እዚያዉ ማድረግ እንደሚችሉ ተማከሩ፤ አደረጉትም። አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ነሐሴ እና ጳጉሜን ወራት በአካባቢያቸው የፈጸመውን ወረራ ለመመከት ከወገን ጦር ጋር አብረው ተፋልመዋል፡፡ 

አባት እና ልጅ በወገን ጦር በደረሰበት ከባድ ምት የተፍረከረከውን አሸባሪ የትግራይ ወራሪ ቡድን እየተከታተሉ በመልቀም እና ዋሻ ውስጥ ተቆርጠዉ የቀሩትን የቡድኑን አባላት በመፋለም ሦስቱን አቁስለዉ አምስቱን ማርከዉ በአጠቃላይ ስምንቱን ለመከላከያ ሠራዊት አስረክበዋል፡፡ 

ጀግናው አቶ ጋሻዉ “አባቴ አርበኛ ነዉ፤ የአባቴን መሳሪያ ይዤ ነዉ የዘመትኩት፤ የእርሱ ልጅ በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል፤ ይህም ጠንክሬ ሀገሬን ከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እንድታደግ አድርጎኛል” ነው ያሉን፡፡ ጀግናው አቶ ጋሻው አሁንም ስሜታቸዉ እንደጋለ፤ ደማቸዉ እንደሞቀ ነዉ፤ ሀገራቸውን ለማፍረስ የመጣውን ጠላት ደምስሰውታል። 

የበኩር ልጃቸዉ ደረጀ ጋሻዉ በሰኔ ወር 2013 ዓ.ም ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም ነበር የተመረቀዉ፤ ገና ሥራ ይዞ አዲስ ሕይወት ሳይጀምር ነበር ሀገር አፈርሳለሁ ብሎ የመጣን አሸባሪ የትግራይ ወራሪ ቡድን ለመደምሰስ ሀገራዊ ጥሪዉን ተቀብሎ ከአባቱ ጋር የዘመተዉ። 

“ሀገራችን ወረራ ሲፈፀምባት ቆሞ የሚያይ በዝምታ የሚያልፍ ወጣት የለም፤ እኔም እስከመጨረሻዉ ጠላቷን ልደመስስላት ነዉ ወደ ትግሉ የተቀላቀልኩት” ያለዉ ወጣት ደረጀ እጁ ላይ የተወሰነ ጉዳት ደርሶበት ሕክምና አድርጎ ወደ ግንባር መዝመቱን ተናግሯል።

“ታላቅ ሀገር ለሆነችው ኢትዮጵያ የሚከፈልላት ዋጋ ከመቁሰልም በላይ ነዉ” ሲል ነው ወጣቱ የገለጸው፡፡ 

“የአባቶቻችን ልጆች በመሆናችን እጅጉን ልንኮራ ይገባል፤ ሁላችንም የእነርሱን የጀግንነት ታሪክ በመድገም አሻራችንን እናሳርፍ” ብሏል። 

ዛሬም አዳዲስ ጀግኖች ተፈጥረዋል፤ እኛም የሠሩትን ገድል መግለጣችንን እንቀጥላለን።
Source Amhara Communications

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት በሙሉ እንዲሁም አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አናስተካክላለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment) እንችላለን። የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViberም ሆነ Whatspp ይደውሉልን። ስልክ ቁጥራችን 619 255 5530 ነው ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Translate

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon

Call Yebbo

የቦ ኮሚኒኬሽን ኔት ወርክ ፣ ለ25 አመታት በላይ የስራ ልምድ ያካበተው የእናንተው በእናንተው። ከምሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ የውክልና አገልግሎት መስጠት የኢትዮጵያ ፓስፖርት አገልግሎት መስጠት የቢጫ ካርድ የማውጣት አገልግሎት የታክስ አገልግሎት መስጠት (የትም የኢትዮጵያ ግዛት ይኑሩ) የጉዞ ወኪል የትርጉም ስራ አገልግሎት ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 619-255-5530 ይደውሉ።