Shop Amazon

Friday, April 5, 2024

‘‘የክብር ዶክትሬት ሽልማት እንጂ ለመጠሪያነት አይውልም!! ረ/ፕ ወይም ተባባሪ ፕሮፌሰር ነን የሚሉትን ሰዎች ዩንቨርሲቲው “አቶ”ነው የሚላቸው::

 ‘‘የክብር ዶክትሬት ሽልማት እንጂ ለመጠሪያነት አይውልም!! ረ/ፕ ወይም ተባባሪ ፕሮፌሰር ነን የሚሉትን ሰዎች ዩንቨርሲቲው “አቶ”ነው የሚላቸው::

====
(ይትባረክ ዋለልኝ)
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ‘‘የክብር ዶክትሬት ሽልማት እና የዶክትሬት ትምህርት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ በፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ አቅራቢነት በፕሮፌሰር ሀብታሙ ወንድሙ አወያይነት መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም በዚሁ ርዕሰ ላይ የገለጻና የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር::
በዚህ የገለፃና የውይይት መድረክ ላይ የክብር ዶክትሬት ሽልማትን በተመለከተ በፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ ባቀረቡት ሰፊ የጥናት ፅሑፍ እንደገለፁት የክብር ዶ/ር ሽልማት እንጂ ለመጠሪያነት አይውልም:: እንዲሁም ረዳት/ፕሮፌሰር ወይም ተባባሪ/ፕሮፌሰር የሚለውም ስያሜም በጋዜጠኞች ብቻ የሚሰጥ ቅፅል እንጂ ለመጠሪያነት እይውልም በማለት ተናግረዋል:: በኢትዮጵያ የክብር ሽልማት አሰጣጡ በዩንቨርስቲዎች ላይ ያለውን ችግርም በዝርዝር አንስተው ሊያስተካክሉ የሚገባቸውን ጉዳዮችንም በዝርዝር ገልጸዋል::
በተለይ ፕሮፌሰር ማስረሻ የክብር ዶክትሬትን በተመለከተ በፁሁፋቸው ላይ እንደገለፁት ከሆነ
" በየትኛውም አለም "ክቡር ዶ/ር እገሌ" ተብሎ ሲጠራ አይታወቁም :: የክብር ዶ/ር ይህ በእኛ ሐገር ብቻ በጋዜጠኞችና ከአካዳሚያዊ ክበብ ራቅ ባሉ ሰዎች የሚጠራ ሲሆን ለዚህ ክፍተት ደግሞ የክብር ዶ/ር የሚሸልሙ ዩንቨርሲቲዎቹ የክብር ዶ/ር ለመጠሪያነት እንደማይውል ለተሸላሚዎቹና ለህዝቡ አለመግለፃቸውን እንደችግር አንስተዋል:: አያይዘውም ለነገሩ ረ/ፕ እና ተባባሪ ፕሮፌሰር የሚል መጠሪያ የሚሰማው በእኛ ሐገር ጋዜጠኞች ብቻ ነው::አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ እነዚህን ሰዎች ረ/ፕ /ተባባሪ ፕሮፌሰር( እገሌ) ብሎደብዳቤ አይፅፍላቸውም:: ዩንቨርስቲዮቹ ለእነዚህ ሰዎች አቶ (እገሌ) ብሎ ነው ደብዳቤ የሚፅፍላቸው:: ጋዜጠኞች ይህን ስያሜ የሚሰጡት ዶክተር ላልሆነ ሰው ከፍ ማድረጊያ እየመሰላቸው የሚጠሩበት ስያሜ ነው:: ለነገሩ ባይገርማችሁ አሁን ደግሞ እጩ ዶክተር" እየተባለ መጠራት ትጀምሯል:: በማለት ተሰብሳቢውን ፈገግ አድርገውታል::" በማልት የገለፁ ሲሆን አያይዘውም
የክብር ዶክትሬትን በተመለከተ ብቸኛዋና በጥሩ አርአያነት የምትጠቀሰው ጋዜጠኛ ማእዛ ብሩ ናት:: ከባህርዳር ዩንቨርስቲ የክብር ዶክተር ሽልማትን ስትቀበል "በለመደ አፋችሁ ዶክተር ብላችሁ እንዳትጠሩኝ" ብላ የተናገረችውን አድንቀው ተናግረዋል:: እኔም ለፕሮፌሰር ማስረሻ ፕሮግራሙ ካለቀ በኃላ አንድ ጥያቄ አነሳሁላቸው "የዩንቨርሲቲው ሰዎች እኮ ናቸው ጋዜጠኞቹን በረዳት ፕሮፌሰር / በተባባሪ ፕሮፌሰር ስም ጥሩኝ የሚሉት እነሱ እንጂ ጋዜጠኛው አይደለም" ስላቸው በትህትና ወንድሜ "እነዚህ ሰዎች በራሳቸውና ባገኙት እውቀት የማይተማመኑ ሰዎች ናቸው:: እንዲህ የሚሉ ካሉ ያሳዝናሉ" ብለውኛል::
በዚህ ፕሮግራም ላይ የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ የኢትዮጵያ በርካታ ምሁራን ተገኝተው ነበር::
ከወዳጄ yitbarer Yetebarek Walelegen ገፅ የተገኘ።

No comments:

Post a Comment