Call Yebbo

የቦ ኮሚኒኬሽን ኔት ወርክ ፣ ለ25 አመታት በላይ የስራ ልምድ ያካበተው የእናንተው በእናንተው። ከምሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ የውክልና አገልግሎት መስጠት የኢትዮጵያ ፓስፖርት አገልግሎት መስጠት የቢጫ ካርድ የማውጣት አገልግሎት የታክስ አገልግሎት መስጠት (የትም የኢትዮጵያ ግዛት ይኑሩ) የጉዞ ወኪል የትርጉም ስራ አገልግሎት ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 619-255-5530 ይደውሉ።

Call Yebbo

YebboTax Ethiopian Banner
ለአሜሪካ ታክስ ከፋዮች፣ አመታዊ ታክሳችሁን፣ ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Backtax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amdment) ካላችሁ የትም ሆናችሁ ማሰራት ትችላለችሁ።የኢትዮጵያ ፓስፖርት፣ የቢጫ ካርድ፣ ውክልና፣ የትርጉም ስራ ይፈልጋሉ? በViber/WhatsApp በ619 255 5530 ደውሉልን። info@yebbo.com Yebbo.com

Thursday, November 13, 2025

አባታችን ሆይ

አባታችን ሆይ – ካራኦኪ መልክ

አባታችን ሆይ – ካራኦኪ ጸሎት

▶ እያንዳንዱን ጽሑፍ ለመጫወት በክፍሉ ውስጥ ያለውን “Play” ይጫኑ።

✝️
ግርማ
ስመ እግዚአብሔር
✝️

1. አባታችን ሆይ (በአማርኛ)

በአብያተ ክርስቲያናት በጋራ በአማርኛ ሲጸለይ ከጥቃቅን ልዩነቶች ጋራ እንዲህ ነው፦ አባታችን ሆይ! በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግስትህ ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ በደላችንንም ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ መንግሥት ያንተ ናትና ኅይል ክብር ምስጋና ለዘለዓለሙ አሜን!

✝️
ሕሊና
ዮሐንስ
✝️

2. አቡነ ዘበሰማያት (ግእዝ)

አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ፣ ትምጻእ መንግሥትከ፣ ወይኩን ፈቃድከ ፣ በከመ በሰማይ፣ ከማሁ በምድር። ሲሳየነ ዘለለ ዕለትነ ሃበነ ዮም። ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ፣ ከመ ንሕነኒ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ። ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት፣ ኣላ አድኅነነ ወባልሐነ እምኩሉ እኩይ። እስመ ዚኣከ ይእቲ መንግሥት፣ ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም፣ አሜን።

✝️
ገብርኤል
ማርያም
✝️

3. በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል (ግእዝ)

በሰላመ፣ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ፣ ኦ እግዝእትየ ማርያም ሰላም ለኪ፣ ድንግል ብኅሊናኪ ፣ ወድንግል በሥጋኪ። እመ እግዚአብሔር ጸባዖት ሰላም ለኪ። ቡርክት አንቲ እምአንስት፣ ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ። ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልእተ ጸጋ፣ እግዚአብሔር ምስሌኪ። ሰአሊ ወጸልዪ ምሕረት በእንቲኣነ፣ ኀበ ፍቁር ወልድኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ይሥረይ ለነ ኃጣውኢነ።

✝️
ሰላም
ቅድስት
✝️

4. በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል (በአማርኛ)

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ፣ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ። በሀሳብሽ ድንግል ነሽ ፤ በሥጋሽም ድንግል ነሽ። አሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል። ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ። የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ ልዑል እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና። ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን እና ምሕረትን ለምኝልን ኃጢአታችን ይቅር ይለን። ለዘለዓለሙ አሜን።

✝️
አብ • ወልድ • መንፈስ
ቅዱስ
✝️

5. የ፫ እግዚአብሔር ጸጋ

የእግዚአብሔር አብ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ቸርነት፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችን ጋር ይሁን ለዘለዓለሙ። አሜን።

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon