Shop Amazon

Showing posts with label ቤቶች. Show all posts
Showing posts with label ቤቶች. Show all posts

Friday, December 31, 2021

19 separate and mass graves found by terrorist group at Robit Secondary and Preparatory School in Raya Kobo Woreda

በራያ ቆቦ ወረዳ በሚገኘው የሮቢት 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት በሽብር ቡድኑ የተፈጸሙ 19 የተናጠልና የጅምላ መቃብሮች ተገኙ
*********************

የራያ ቆቦ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መንገሻ በላይነጋ እንደገለጹት በሮቢት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ከተገኙት 19 መቃብሮች 3ቱ በእያንዳንዳቸው እስከ 30 ሰዎች የተቀበሩባቸው የጅምላ መቃብሮች ናቸው። 

ወራሪው ቡድን የወረዳውን ትምህርት ጽሕፈት ቤት እና በወረዳው የሚገኙ 7 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ 129 ትምህርት ቤቶችን በመውረር ዘረፋ መፈጸሙንና ንብረቶችን ማውደሙን ተናግረዋል። 

የሽብር ቡድኑ ከዘረፋቸውና ካወደማቸው ንብረቶችና ቁሳቁሶች መካከልም የቤተ ሙከራ ቁሳቁሶች፣ ኮምፒውተሮች፣ ፕላዝማዎች፣ የተማሪ ሰነዶችና ሌሎችም የትምህርት ቤቱ ንብረቶች ይገኙበታል። 

የሮቢት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጥበቃ ሠራተኞች አቶ ይመር አየለ እና ዝናቡ ሰማው ወራሪው ቡድን ትምህርት ቤቱን የመቃብር ስፍራ እንዳደረገው ገልጸዋል። 

የሮቢት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለፈው ዓመት መጨረሻ ከ1ሺ 800 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምር እንደነበር መገለጹን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል። 
19 separate and mass graves found by terrorist group at Robit Secondary and Preparatory School in Raya Kobo Woreda
 *********************

 Raya Kobo Woreda Education Office Head, Mengesha Belaynega, said three of the 19 graves found on the grounds of Robit High School are mass graves of up to 30 people each.

 The invading group reportedly looted 129 schools, including the Woreda Education Office and seven secondary schools in the woreda, and looted property.

 Among the items looted and destroyed by the terrorist group were lab equipment, computers, plasma, student documents, and other school supplies.

 Robit High School security guards Yimer Ayele and Zinabu Semaw said the invading group had turned the school into a graveyard.

 According to the Ministry of Education, Robit High School enrolled more than 1,800 students at the end of last year.