Wednesday, November 11, 2020

 Prime Minister Abiy Ahmed called on the people to protect the area in an active and organized manner

 Prime Minister Abiy Ahmed called on the people to protect the area in an active and organized manner.

 Prime Minister Abiy Ahmed called on the people to protect the area in an active and organized manner.

 The Prime Minister said on his social media page that the sun is setting.

 He asserted that his confession had been obtained through torture.

 "It is time for the junta to lose its grip on power," he said.

 He called on the people to be vigilant and organized in order to protect the environment.

 In this regard, he also conveyed a message to the people of Tigray to be the guardians of all his brothers so that they are not harmed in any way.

 He said the enemy of Ethiopia is the greedy Junta, adding that the people of Tigray are suffering like the other people.

 He said the people of Tigray are fighting alongside the Defense Forces to bring Junta to justice.

 I will protect my people;  I will break the yoke of the Ethiopian people;  "I will bring Junta to justice," he said.

 Subscribe to our right YouTube channel to get our video information

Tuesday, November 10, 2020

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ሕዝቡ በንቃትና በተደራጀ መንገድ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አቀረቡ።

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ሕዝቡ በንቃትና በተደራጀ መንገድ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አቀረቡ።

 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሕዝቡ በንቃትና በተደራጀ መንገድ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው  የጁንታው ፀሐይ እየጠለቀች ነው ብለዋል ።

ይሄንን መርዶ ጁንታው በቁሙ እንደተረዳው ነው የገለፁት።

ጁንታው አሁን የሚይዘውን የሚጨብጠውን የሚያጣበት ጊዜ በመሆኑ በጣዕር መንፈስ በየቦታው የመጨረሻውን የጥፋት ድግስ ይደግስ ይሆናልም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ።

በመሆኑም ሕዝቡ በንቃትና በተደራጀ መንገድ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል ።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወገኖች በየአካባቢው ምንም ዓይነት አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳይደርስባቸው ሁሉም የወንድሞቹ ጠባቂ እንዲሆንም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ጠላት ስግብግቡ ጁንታ መሆኑን በመጥቀስም የትግራይ ሕዝብ እንደሌላው ሕዝብ በጁንታው መከራ ያየ ሕዝብ መሆኑንን አስታውቀዋል።

ጁንታው ለፍርድ እንዲቀርብ የትግራይም ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር አብሮ እየተዋጋ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ህዝቡም አካባቢዬን እጠብቃለሁ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ የመከራ ቀንበር እሰብራለሁ፤ ጁንታውን ለፍርድ አቀርባለሁን ቃል ኪዳኑ ሊያደርግ እንደሚገባም ገልፀዋል ።

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
 Prime Minister Abiy Ahmed called on the people to protect the area in an active and organized manner.

 Prime Minister Abiy Ahmed called on the people to protect the area in an active and organized manner.

 The Prime Minister said on his social media page that the sun is setting.

 He asserted that his confession had been obtained through torture.

 "It is time for the junta to lose its grip on power," he said.

 He called on the people to be vigilant and organized in order to protect the environment.

 In this regard, he also conveyed a message to the people of Tigray to be the guardians of all his brothers so that they are not harmed in any way.

 He said the enemy of Ethiopia is the greedy Junta, adding that the people of Tigray are suffering like the other people.

 He said the people of Tigray are fighting alongside the Defense Forces to bring Junta to justice.

 I will protect my people;  I will break the yoke of the Ethiopian people;  "I will bring Junta to justice," he said.

ጦርነት ልሄድ ስለሆነ የጀመርኩት ክርክር ይቆይልኝ ... !

ጦርነት ልሄድ ስለሆነ የጀመርኩት ክርክር ይቆይልኝ ... !
(አምሳ አለቃ አያሌው ሙሔ)
*****
የምታዩት 50 አለቃ አያሌው ሙሄ ይባላል ። ወደ ዘመቻ ማቅናቴ ስለሆነ የጀመርኩት ክርክር ባለበት እንዲቆይ ይደረግልኝ በሚል በደቡብ ወሎ ዞን ለቦረና ሳይንት (ሳይንት አጅባርና ቦረና ሳይንት ይባላል) ወረዳ ፍርድ ቤት በችሎቱ ለተሰየሙት ዳኛ ጥያቄውን አቀረበ ።
የችሎቱ ዳኛ ጉዳዩ ከሚመለከተው የመንግሥት ጽ/ቤት ካረጋገጠ በኋላ በሠላም ይመልስህ ሲል መዝገቡን ለሌላ ጊዜ ዘግቶታል ። @Voice of Justice
አማራ ጦርነቱን ባሚገባ ወደ ራሱ ስቦ ከራሱ አልፎ ለአማራ ፖለቲከኞች የሥልጣን መደራደሪያ ዕድል ሰጥታል ። ፖለቲከኞች ዕድሉን ተጠቀሙበት ።

GMC - Gihon Media Center

የሰሜን ዕዝ የመገናኛ ሥርዓት እንዲቋረጥ እና በዕዙ ላይ ጥቃት እንዲፈፀምበት ሲያመቻቹ የነበሩ ጀነራል መኮንኖች ከነግብረ አበሮቻቸው በቁጥጥር ሥር ዋሉ

የሰሜን ዕዝ የመገናኛ ሥርዓት እንዲቋረጥ እና በዕዙ ላይ ጥቃት እንዲፈፀምበት ሲያመቻቹ የነበሩ ጀነራል መኮንኖች ከነግብረ አበሮቻቸው በቁጥጥር ሥር ዋሉ  
******************** 

የሰሜን ዕዝ ከማዕከል ጋር የሚኖረው የመገናኛ ሥርዓት እንዲቋረጥ በማድረግ በጁንታው የሕዋሓት የጥፋት ቡድን ጥቃት እንዲፈፀምበት ሲያመቻቹ የነበሩ ጀነራል መኮንኖች ከነግብረ አበሮቻቸው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። 

ኮሚሽኑ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫው በመንግሥት፣ በሕዝብ እና በሀገር መከላከያ ሠራዊት የተጣለባቸውን አደራ እና ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው የጁንታው ሕወሓት ሴራ አካል በመሆን የአገር ክህደት ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠሩ ጀነራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች እና የበታች ሹማምንቶች በድምሩ 17 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውቋል። 

በሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል ሆነው ከጁንታው ሕወሓት ጋር በመጣመር ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ በትግራይ ክልል የሚገኘው የሰሜን ዕዝ ከማዕከል ጋር የሚኖረው ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ እንዲቋረጥና የዕዙ የመገናኛ ሥርዓት ለጁንታው የሕዋሓት ወንበዴው ቡድን እንዲመቻች  በማድረግ  የተጠረጠረው  ሜጀር ጀነራል ገብረመድህን ፈቃዱ  ወይም በቅጽል  ስሙ  ወዲ ነጮ የተባለው ተጠርጣሪ በአገር ክህደት ወንጀል ከነግብረ አበሮቹ  በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን  በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ተደርጓል። 

የአገር ክህደትን በመፈጸም በዋነኝነት የተጠረጠረው ሜጀር ጀነራል ገብረመድህን ፍቃዱ ከለውጡ  በፊት በአገር መከላከያ ሠራዊት የአጋዚ ኮማንዶ እና ልዩ ኃይሎች አዛዥ የነበረ ሲሆን፣ በሠራዊቱ ውስጥም በተለያዩ የሥራ እርከኖች ያገለገለ መሆኑን ያመለከተው መግለጫው፤ ለውጡን ተከትሎም በአገር መከላከያ ሰራዊት የመገናኛ መምሪያ ኃላፊ በመሆን ሲሰራ እንደነበር አስታውሷል። 

ይሁንና ከመንግሥት፣ ከሕዝብና ከአገር መከላከያ ሰራዊት የተጣለበትን ከባድ አደራና ኃላፊነት አገር ለማፍረስ እና ለማተራመስ ከሚንቀሳቀሰው የጁንታው ሕዋሓት የሴራ አካል በመሆን የሰሜን እዝ ከማዕከል ጋር ያለው ግንኙነት እንዲቋረጥ እና በከሃዲዎች ጥቃት እንዲፈፀመበት ከማድረጉም በላይ፤ በውስጣቸው ቦምቦች እና የሚሳኤል መሳሪያዎችን የያዙ 11 ሳጥኖች የግንኙነት መሳሪዎች ናቸው በሚል ሽፋን ወደ ትግራይ የጁንታው ቡድን  ለመላክ ሲዘጋጅ ከተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ጋር እጅ ከፍንጅ መያዙን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በላከው መግለጫ አመልክቷል። 

የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ባደረጉት ጠንካራ ክትትል እና ባካሄዱት ኦፕሬሽን ተጠርጣሪው ሜጀር ጀነራል ገብረመድህን ፈቃዱን ጨምሮ ሌሎች ጀነራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች እና የበታች ሹማምንቶቻቸው በድምሩ 17 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተገልጿል። 

በቀጣይም ከጁንታው የሕዋሓት የጥፋት ቡድን አገር የማተራመስ እና የማፍረስ ሴራ እንዲሁም በአገር ክህደት ወንጀል የተሳተፉትን እና በየትኛውም የኃላፊነት ደረጃ እና መዋቅር ላይ ያሉ ተጠርጣሪዎችን ተከታትሎ በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የማድረግ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።


የሶስቱ ቀናት ፈታኝ ተጋድሎ በጀኔራሉ አንደበት

የሶስቱ ቀናት ፈታኝ ተጋድሎ በጀኔራሉ አንደበት
.
ዳንሻ ከተማ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ አምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር ካምፕ ጊቢ ውስጥ የመከላከያ መኪናዎች በጥይት ተበሳስተው ይታያሉ፡፡ መስታወታቸው ረግፏል፤ ዛፎቹም የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል፤ መጥረቢያ እንጂ የጥይት ውርጅብኝ የቆረጣቸው አይመስሉም። የግንብና ቆርቆሮ ቤቶች እንደ ወንፊት ተበሳስተዋል፡፡ የጥይቶች ቀላሃ እንደ ጠጠር ተበትኗል፡፡

ዕለተ ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2013ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት አካባቢ በዳንሻ ከተማ ያልተጠበቀ፣ አሳዛኝ፣ አስደጋጭ ድርጊት ነው የተፈጸመው፡፡ በከተማዋ የሚገኘው የሰሜን ዕዝ የአምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር የተደገሰለትን ጥቃት አያውቅም። በመካናይዝድ ክፍለ ጦሩ ስታፍ ውስጥ የሚሰሩት መደበኛ ስራቸውን ከውነው እንቅልፍ ላይ ናቸው፡፡

በዚህ ምሽት ግን የትግራይ ልዩ ሀይል አባላት ወደ ካምፑ ዘለቁ፤ ብርጋዴር ጀነራል ሙሉዓለም አድማሱን እንደሚፈልጉትና እንዲጠራላችሁ የበር ጥበቃዎችን ይጠይቃሉ። ጀኔራሉም እንደማይመጡ ሲነገራቸው ተመልሰው ይሄዱና ተጨማሪ ሀይል ይዘው መጥተው በካምፑ ላይ የጥይት መአት ማውረድ ይጀምራሉ፡፡ ውስጥ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላትም በጽናት የመመከት ስራ ውስጥ ገቡ፤ለሶስት ቀንና ሌሊት በጽናት ታገሉ፡፡

አንድ የመከላከያ ሰራዊት የመረጃ ሰራተኛ ወደ ጀነራሉ ጆሮ ተጠግቶ "አካባቢውን የትግራይ ልዩ ሀይሎች ከቦታል፡፡ ፍላጎት ካለህ ሽማግሌዎቹ ከአካባቢው እናስወጣው ብለው ነግረውኛል፤ ውሳኔህ ምንድነው?" ሲል ጠየቀኝ ያሉት ብርጋዴር ጀነራሉ፣ የእነሱ ፍላጎት እኔም ወኔዬን ተሰልቤ የሲቪል ልብስ ለብሼ ተደብቄ ወደ አማራ ክልል እንድወጣ አልያም እኔን አታለው እንድያዝ በማድረግ ካምፕ ውስጥና በአቅራቢያው ባለው የመከላከያ ሰራዊት ላይ ለመሰንዘር ያቀዱትን ጥቃት የመከላከልና የመመከት ስራ ለማሰናከል ነው፡፡በዚህም በቀላሉ ሰራዊቱንና መሳሪያውን በቁጥጥር ስር ለማዋል አስበው መሆኑን ገለጹልን፡፡

እኔም ምላሼ ሽምግልናውን አለመቀበል ብቻ ሳይሆን የመረጃ ሰራተኛው ከሽማግሌዎቹ ጋር ለጥሩም ይሁን ለመጥፎ መገናኘት እንደሌለበት አስጠንቅቄ ነገርኩት። አሁን ይህን ያለኝ ልጅ ቆስሎ ለህክምና ወደ ጎንደር ሄዷል። ሲመጣ ጠይቄ ዓላማቸው ምን እንደነበር የምረዳው ይሆናል፡፡ተመትቶ ስለነበረ እኔም እንዳልሞት አስቦ ይሆናል የሚል ግምት አለኝ ብለውናል።

"የሶስት ቀን ከበባው በጣም አስቸጋሪ ነበር። 24 ሰዓት ተኩስ ነው፡፡ ያጠቃሉ እኛ እንከላከላለን፤ ይሄዱና ምግብ በልተው ሀይል ጨምረው ያጠቃሉ፤ ሲታኩሱ የነበሩት ልዩ ሀይሎች ወደ ካምፓቸው ሄደው አርፈውና ጥይት ጭነው ይመጣሉ፡፡እኛ ካለንበት ቦታ ውጭ መፈናፈኛ ስፍራ የለንም፡፡ እንደ ቀለበት ዙሪያውን ከበውና ውሃ ፣ ምግብ፣ ጥይት የለም፡፡ ያለችንን ነው በቁጠባ የምንጠቀመው" ሲሉ ያብራሩት ጀነራሉ፣ 
"እኔም አልፎ አልፎ እንደ ምሽግ ከተጠቀምኩበት ግንብ ቤት እየወጣሁ ለወታደሮቼ ጥይት በቁጠባ ተጠቀሙ እያልኩ አሳስብ ነበር" ሲሉ ይገልጻሉ፡፡ "እነሱም አላሳፈሩኝም በጽናት ተዋደቁ። የሰራዊታችን በጽናት የመከላከል ሞራል የሚገርም፣ የሚደነቅና ታምር የሚያስብል ነው" ይላሉ፡፡

"አርቢጂ፣ ቦንብ፣ መትረየስ ፤ ክላሽ እንደ ዝናብ ቢያርከፈክፉብንም ለሶስት ቀናት ቀንና ሌሊት መክተናል፡፡በፍጹም እንተርፋለን ብለን አላሰብነም ፤ ከቻልን እስከ መጨረሻው እንከላከላለን ፤ካልቻልን ደግሞ በመጨረሻ ላይ ራሳችንን እናጠፋለን የሚል አቋም ነበርን፡፡ ግን በእግዜአብሄር ቸርነት፤ በመከላከያ ሰራዊት ፈጥኖ ደራሽነት ቀለበቱ ተሰብሮ ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግረናል" ብለውናል ብርጋዴር ጀኔራል ሙሉዓለም፡፡

"ድርጊቱ የሚያሳዝን ነው፤ በህወሓት ከሀዲ ቡድን እንዲህ አይነት ጥቃት ይፈጸምብናል ብለን አስበን፤ አልመንም አናውቅም" የሚሉት በሰሜን ዕዝ የአምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ሙሉዓለም አድማሱ፤ "ምክንያቱም ከኢትዮ-ኢርትራ ጦርነት ጀምሮ ትግራይ መሬት ነው እየኖርን ያለው። ህዝቡን መሪዎቹንም በደንብ እናውቃቸዋለን" ብለዋል፡፡

“አብረህ እየበላህ እየጠጣህ፣ ተዋልደህ ተጋምደህ፤ ትዳር መስርተህ ፣ልጆች ወልደህ፤ ቤተሰብ ሆነህ በፍጹም ጥቃት ሊሰነዝርብኝ ይችላሉ ብለህ አታስብም፤ ሆኖም ያልታሰበው ተፈጸመ፤ ያልተጠበቀው ሆነ" ሲሉ በትግራይ ክልል ልዩ ሀይል የተሰነዘረባቸውን ጥቃት አሳዛኝ ሲሉ ይገልጹታል።

"ኩርፊያና የተለያዩ መገለጫዎች ይታያሉ ፡፡ ይህን ተከትሎ ጥርጣሬዎች ቢኖሩም ደፍረው መከላከያ ሰራዊት ካምፕ ውስጥ ገብተው ያጠቃሉ ብለን አላሰብንም። ምክንያቱም ወንድምህ ሊያኮርፍ ይችላል እንጂ ያጠቃኛል፤ ይገለኛል ብለህ ፈጸሞ አትገምትም" የሚሉት ብርጋዴር ጀኔራሉ፤ "ግን የትግራይ ልዩ ሀይሎች ዕለተ ማክሰኞ 25ቀን 2013ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ያለምንም ርህራሄ ዙሪያውን እንደ ቀለበት ከበውን አጠቁን ፣ አጠቁን እኛም በጽናት ተከላከልን፤ መከትን" ብለዋል፡፡

"የህወሓት ቡድን ዓላማ የመከላከያ ሰራዊትን መድፎች፣ ታንኮች፣ ብረት ለበሶችን መንጠቅና መከላከያን ማፍረስ ነው፡፡ በዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም ፤ በራሳችን መሳሪያ ተመልሰው እኛን ለመውጋት ነበር ዕቅዳቸው፡፡ ይህ አልተሳካላቸውም፡፡ እኛም በያለንበት በጽናት ተዋግተን መክተናል፡፡ አሁን እነሱ ባሰቡት ሳይሆን እኛ ባሰብነው መንገድ እየሄደ ነው፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጦርነቱ ይቋጫል ብለን እናስባለን" ሲሉ ገልጸውልናል።

ብረጋዴር ጀኔራል ሙሉዓለም አንድ የሚገርማቸው የሚደንቃቸው ነገር አለ፡፡
"እኔ አንድ ተራ ኢትዮጵያዊና ተራ ጄነራል ነኝ። በአንድ ክላሽ ጥይት ግፋ ቢል ደግሞ በስናይፐር መግደል ይችላሉ፤ ግን የጭካኔያቸው ጭካኔ አርቢጂ ነው የተኮሱብን ። አርቢጂ የሚባለው መሳሪያ ደግሞ ለታንክ ወይም ለጠንካራ ምሽግ ነው የሚተኮሰው፤ የእኔን ቤት ለማፍረስ ግን አርቢጂ ነው የተኮሱት" ሲሉ የከሀዲው ቡድን የጭካኔ ጥግ ምን ያህል እንደሆነ ይናገራሉ ፡፡
"እኔ ብሞትም ቤቱ የእነሱና የህዝቡ ንብረት ነው። ለትግራይ ህዝብ ሰላምና ጸጥታ ለቆምኩ፣ ለአገር ሉዋላዊነትና ለህዝብ ሰላም ውድ ህይወቴን ለመስጠት በተሰለፍኩ የክህደታቸው፣ የክፋታቸው ጥልቀት እኔን በአርቢጂና በቦንብ ነው ያጠቁት" ሲሉ የድርጊቱን ክፋት ገልጸውታል።

"የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ህዝብ ጋር አብሮ እየኖረ ያለ፣ ለህዝቡ የልማት ስራዎች ወደ ኋላ የማይል፣ በማህበራዊ ድጋፎች የሚሳተፍ፣ ሁልጊዜ በየዓመቱ ለአቅመ ደካሞች የሚያርስ፣ የሚያርም፣ የሚያጭድና አንበጣ የሚከላከል ነው። በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ጣቢያዎች፣ በመንገድ ግንባታዎች በሚሳተፍ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈጸም የህወሓት ቡድን እወክለዋለሁ ቆሜለታለሁ ለሚለው ህዝብ ደንታ እንደሌለው ያሳያል" ይላሉ፡፡
"የአገሩን ዳር ድንበር የሚጠብቀውን፤ የኢትዮጵያ ብሄሮችና ብሄረሰቦች ስብስብ የሆነውን የመከላከያ ሰራዊት ለማውድምና ለማጥፋት ነው ጥቃቱን የሰነዘሩት ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከዚህ በኋላ ስለኢትዮጵያዊነት፣ብሄሮች ፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቢሰብኩ፣ ቢለፈልፉ፣ ቢቀሰቅሱ ማን ጀሮ ይሰጣቸዋል ፡፡ ምክንያቱም ጥቃቱን በጽናት ለመመከት የተዋደቁት ከኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች የተወጣጡ ወታደሮች ናቸው" ብለዋል፡፡

ጀኔራሉ በ1980ዓ.ም በወቅቱ ኢህዲን ተብሎ የሚጠራውን ትግል የተቀላቀሉ ናቸው፡፡ ከዚሁ ዓመት ጀምሮ ደርግ እስኪደመሰስ ድረስ በተደረጉ ውጊያዎች ተሳትፈዋል። ቆቦ አካባቢ በተካሄደው ሰላም በትግል ኦፕሬሽን፤ ሰሜን ሸዋ መራኛ፣ ጁሁርና መራቤቴ አውድ ውጊያዎች ተሳትፈዋል፡፡በጎጃም ደጀን፣ አምቦ፣ ነቀምት፣ ጅማ፣ ቡሌሆራ(አገረ ማርያም) ሞያሌ ድረስ በዘለቀው አውድ ውጊያ ተሳትፈዋል፡፡በሀረርም ጸረ ሰላም ሀይሎችን በመከላከልና በማጥቃት ዘመቻ ተሳትፈዋል፡፡
በሩዋንዳ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ በ1986ዓ.ም ግድጃቸውን በስኬት አጠናቀው ተመልሰዋል፡፡
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሲቋቋምም 20ኛ ክፍለ ጦር መድፈኛ ብርጌድ አንደኛ ሻለቃ አዛዥ ሆነው አገልግለዋል፡፡በኢትዮ-ኢርትራ ጦርነትም ትምህርታቸውን አቋርጠው በመሄድ ብርጌድ አዛዥ በመሆን በጾረና፣በባድመ፣በሽራሮ አዲኋላ ግንባር ተሳትፈዋል፡፡
አሁንም በዳንሻ ከተማ በትግራይ ልዩ ሀይል የተካሄደውን ከበባና ሶስት ቀናት የዘለቀ ጥቃት ወስን ወታደሮችን መርተውና አዋግተው በተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት ዕገዛ መከላከሉን በድል አጠናቀው የማጥቃቱን ተልዕኮ በድል እየተወጡ ይገኛሉ።
ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

አይን ያወጣ ሙስና። የበለሳ ሊቀመንበር ዘመዶቹን መርጦ ወደ ዘመቻ በመላክ ህዝባዊ ክስ ቀረበበት!



"#የበለሳ ወረዳ # ሊቀመንበር ዘመዶቹን መርጦ ወደ ዘመቻ በመላክ ህዝባዊ ክስ ቀረበበት!

የጋይንት ህዝብ ደግሞ ከኮታ በላይ የዘመች ቁጥር ከአቅም በላይ በመብዛቱ የዘመቻው አስተባባሪዎች ቁጥሩን ለመቀነስ የተጠቀሙበት፣የዕድሜ ጣራ፣የአካል ብቃት ና መሰል የምልመላ ስልት ሁሉ ውድቅ ሁኖባቸው መቸገራቸው ከቅርብ ምንጮች ባረጋገጥኩ ጊዜ...!

#እውነትም #"ጦርነት ሰርግና ምላሹ የሆነ ህዝብ ነው" አልኩ

//////////ይኸው ነው!///////////

በትግራይ የሕግ የበላይነት የማስከበር ስራ በታቀደው መሰረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ

በትግራይ የሕግ የበላይነት የማስከበር ስራ በታቀደው መሰረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ
*************************

በትግራይ የሕግ የበላይነት የማስከበር ስራ በታቀደው መሰረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገልጸዋል፡፡

በትግራይ ክልል የተጀመረው ኦፕሬሽን  ወንጀለኛው ጁንታ የሕወሃት ቡድን  ትጥቅ እንዲፈታ ከተደረገ በኋላ፣ ችግር ፈጣሪዎች ለፍርድ ሲቀርቡ እንዲሁም  በክልሉ ሕጋዊ ተቀባይነት ያለው አስተዳደር ሲመሰረት እንደሚቆም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

ሁሉም ስራዎች በተገቢው ፍጥነት እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትዊተር ገጻቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል፡፡

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን 

 Prime Minister Abiy Ahmed said the rule of law is being implemented in Tigray as planned
 ***************************

 Prime Minister Abiy Ahmed said the rule of law is being implemented in Tigray as planned.

 The operation, which began in Tigray State, will end after the disarmament of the criminal Junta TPLF, the perpetrators will be brought to justice and a legitimate administration will be established in the state, he said.

 In a message posted on his Twitter account, Prime Minister Abiy Ahmed said that all the work is being carried out at the proper pace.

 The right way to get our video information

የኦነግ ታጣቂዎችን ጨምሮ የማፊያው ሕወሓት ቡድን ልዩ ኃይል አባላት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በማድረስ ተሳትፈዋል

"የኦነግ ታጣቂዎችን ጨምሮ የማፊያው ሕወሓት ቡድን ልዩ ኃይል አባላት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በማድረስ ተሳትፈዋል" - ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ 
******************** 

በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ያደረሱ አካላት የማፊያው ሕወሓት ቡድን ልዩ ኃይል፣ የአካባቢው ሚሊሺያ እና በማይታመን መልኩ ደግሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድንም ጭምር እንደነበር ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ አስታወቁ። 

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ውጊያ እየተካሄደባቸው ያሉ የጦር ቀጠናዎችን የጎበኙት ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ፣ የሕወሓት ማፊያ ቡድን በአካባቢው በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰሜን እዝ ላይ ያደረሰውን ጥቃት በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል። 

ሌ/ጄኔራሉ ከሌሎች ጓዶች ጋር በመሆን በአካባቢው ባደረጉት ጉብኝት ማፊያው የሕወሓት ቡድን እየተናገረ እንዳለው የሰሜን እዝ ከማፊያው የሕወሓት ቡድን ጋር በማበር የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እየወጋ እንዳልሆነ ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል። 

የሰሜን እዝ ፈተና ቢገጥመውም እና እንዲሸረሸር በሆዳሞች ጥረት ቢደረግበትም የዓላማ ፅናት ያላቸው የጦሩ አባላት በጀግንነት የሕይወት መሥዋዕትነት በመክፈልም ጭምር ጁንታውን ቡድን ተፋልመዋል ነው ያሉት። 

ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ በሰሜን እዝ ላይ የደረሰውን ጥቃት ሲያብራሩ፣ እዙ በመቐለ በመሸገው ጁንታ አማካይነት ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ ወደ ማጥቃት ከመግባቱ በፊት በሰሜን እዝ ውስጥ የሚገኙ ትግርኛ ተናጋሪዎችን በመጠቀም ሰሜን እዝን ለማፈራረስ አቅዶ እንደነበር ገልጸዋል። 

የወታደሩ ራሽን እና ደመወዝ መላኩን ቀድመው የማረጋገጥ ሥራ ሠርተዋል ያሉት ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ፣ ይህ ከሆነ በኋላ የሰሜን እዝ ከየትኛውም ሠራዊት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳይኖር ሬዲዮ መገናኛውን አቋርጠዋል ብለዋል። 

ለዚህ ዓላማ መሳካትም ዋና የሬዲዮ መገናኛ ኃላፊው በማፊያው ቡድን መጠለፋቸውን እና ከዚያ በኋላ ጁንታው ጥቃት መፈፀሙን ገልጸዋል። 

ግንኙነቱ ከተቋረጠ በኋላ የ20ኛው ክፍለ ጦር አዛዥን ጨምሮ የተወሰኑ የጦር አመራሮችን ማፈናቸውን፣ በተለይም ደግሞ አጋዥ ኃይል የሚባለውን ለ21 ዓመታት የሀገሩን ዳር ድንበር ሲጠብቅ የነበረውን ሠራዊት ምንም ባልተዘጋጀበት ሁኔታ ጨፍጭፈው አስከሬኑን አውሬ እንዲበላው በማድረግ ዘግናኝ ድርጊት መፈፀማቸውን ተናግረዋል። 

የጨፈጨፏቸውን ወታደሮች አስከሬን ራቁት አድርገው እስከ ትላንትናው ዕለት እንዳይቀበር አድርገዋል ያሉት ሌ/ጄኔራሉ፣ በአስከሬኑ ላይ ሲጨፍሩ እንደነበሩም ገልጸዋል። 

ከጭፍጨፋ የተረፉ የሰሜን እዝ ወታደሮችን ልብስ አስወልቀው ራቁታቸውን ወደ ኤርትራ ሠራዊት እንዲቀላቀሉ ማድረጋቸውን፣ ድንበሩን እየጠበቀ የነበረው የኤርትራ ሠራዊት ግን ራቁታቸውን ለሔዱት የሠራዊታችን አባላት ልብስ ማልበሱን መረጃው እንዳላቸው ጠቁመዋል። 

የሰሜን እዝ በርካታ ጥፋቶች ቢፈፀምበትም በተለያዩ መንገዶች ከሌሎች የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር ግንኙነት ፈጥሮ በአሁኑ ሰዓት በእልህ እና ለባንዲራው ባለው ታማኝነት የጠላት ጦርን በተለያዩ ግንባሮች እየደመሰሰ እንደሆነ እና በየቀኑ አዳዲስ ድሎችን እያስመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል። 

በአጠቃላይ የሞት ድግስ የተደገሰለት የሰሜን እዝ ሁሉንም ድል አድርጎ የሀገር ዳር ድንበረን እያስጠበቀ የትግራይን ሕዝብ ከዚህ ግፈኛ ጁንታ ነፃ ለማውጣት እየሠራ እንደሆነ እና ባንዲራውን ከፍ እያደረገ ነው ብለዋል። 

በጥላሁን ካሳ 

Monday, November 9, 2020

በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ዙሪያ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ገለጻ እየተደረገ ነው

በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ዙሪያ  በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ገለጻ እየተደረገ ነው
************************

በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ዙሪያ  በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ገለጻ እየተደረገ ይገኛል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እየተሰጠ ባለው በዚህ ገለጻ፣  ዘራፊው የህወሃት ቡድን በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመው ክህደትና በአገራዊ አንድነት ላይ ያተኮረ ነው፡፡

በመድረኩ የኪነጥበብ ባለሙያዎችና  ታዋቂ ሰዎች እየተሳተፉ ነው፡፡

በአስማማው አየነው

የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሁመራ ኤርፖርትን ተቆጣጣረ

የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሁመራ ኤርፖርትን ተቆጣጣረ
**********************

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዘራፊው የህውሓት ቡድን ከጠላት ጋር ጥምረት በመፍጠር ለእኩይ አላማ ሊጠቀምበት የነበረውን የሁመራ ኤርፖርት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።

በርካታ ህውሓት ያደራጃቸው የልዩ ኃይል፣ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት ለመከላከያ ሰራዊት እጃቸውን እየሰጡ ነው።

ሰራዊቱ ዘራፊው የህውሓት ቡድን ያደረሰበትን ድንገተኛ ጥቃት በመመከት የመልሶ ማጥቃት ስራ እየሰራ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ከዳንሻ ጀምሮ በርካታ ቦታዎችን እየተቆጣጠረ እንደሚገኝ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያሳያል። 


Prime Minister Abhiy Ahmed has made new appointments

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዳዲስ ሹመቶችን ሰጡ
********************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የተሰጡት ሹመቶች የሚከተሉት ናቸው።

- አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
- ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም

- ሌ/ጄኔራል አበባው ታደሰ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም

- አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብሔራዊ መርጃና ድህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር

- ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር

አዳዲሶቹ ሹመቶች የሀገሪቱን የጸጥታና የደኅንነት ብሎም የውጭ ግንኙነት አካላትን በማጠናከር የተጀመረውን ሕግ የማስከበር ዘመቻ በአጭር ጊዜ በብቃት ለመወጣት የተደረገ የአመራር ሽግሽግ እንደሆነም ተገልጿል።
Prime Minister Abhisit Vejjajiva has made new appointments

 ********************


 The following are the appointments made by Prime Minister Abiy Ahmed since October 25, 2013.


 - Demeke Mekonnen Deputy Prime Minister and Minister of Foreign Affairs

 - General Berhanu Jula, Chief of Staff of the Armed Forces


 - Lt. Gen. Ababaw Tadesse, Deputy Chief of Staff of the Armed Forces


 - Ato Temesgen Tiruneh Director General of the National Relief and Security Service


 - Commissioner Demelash G. Michael, Federal Police Commissioner


 The new appointments are part of a leadership transition to strengthen the country's law enforcement and foreign relations.


Saturday, November 7, 2020

The Federal Government is working to uphold the rule of law in accordance with the country's constitution, the Prime Minister's Office said

የፌዴራል መንግስት በአገሪቱ ሕገ መንግስት መሰረት የሕግ የበላይነት የማስከበር ስራ እየሰራ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ገለጸ
********************************

 ህወሃት የአገሪቱን ሕገ መንግስት በመጣስ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የፌዴራል መንግስት በአገሪቱ ሕገ መንግስት መሰረት የሕግ የበላይነት የማስከበር ስራን እየሰራ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ገልጿል፡፡

አሁን ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ከሁለት ዓመታት በፊት ወደ ስልጣን መምጣቱን ተከትሎ አገሪቱን በሕግ ሳይሆን በጭቆና ለ27 ዓመታት ሲገዛ የነበረው ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራት /ህወሃት/ ሰላማዊ ዜጎችን እንደ ጋሻ በመጠቀም በመቐለ ከተማ ከፍትሕ ሸሽተው መቆየቱን ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡

ቡድኑ  ባለፉት ሁለት ዓመታት ለተለያዩ ቡድኖች ድጋፍ በማድረግ አገርን የማተራመስ ተግባር ላይ ተጠምዶ የነበረው ቢሆንም፣ የፌዴራል መንግስት ሁኔታውን በትዕግስት ሲከታተል መቆየቱ ተገልጿል፡፡

የፌዴራል መንግስቱ ህወሃት በአገሪቱ ውስጥ የተፈጠረው የሪፎርም አካል እንዲሆን የውይይት፣ የድርድርና የጋራ መግባባት እድሎች ተከፍተው ሁሉም የሰላም አማራጮች የተጠቀመ ቢሆንም ቡድኑ ባሳማራቸው የጥፋት ኃይሎች  አማካኝነት በምዕራብ ጎንደር፣ ሻሸመኔ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ቤኒሻንጉል፣ ጉራ ፈርዳ፣ እንዲሁም በቅርቡ በምዕራብ ወለጋ ጥቃት መፈጸሙን ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡

መንግስት በገለልተኛ አካላት በኩል ድርድር እንዲደረግ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም ህወሃት ሕገ ወጥ ምርጫ በማድረግና የፌዴራል መንግስቱን እንደ ሕገ ወጥ አካል በመቁጠር ለፌዴራል መንግስቱ እውቅና እንደማይሰጥ ገልጸ ነበር ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም ቡድኑ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መሰነዘሩን ተከትሎ የፌዴራል መንግስት የመከላከያ ሰራዊት ራሱን እንዲከላከል እንዲሁም በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ትእዛዝ ማስተላለፉ ተገልጿል፡፡

 በትግራይ ለ6 ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅም በኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሰብሳቢነት የሚመራና አግባብነት ካላቸው አካላት የተውጣጡ አባላት ያሉት ግብረ ኃይል በዚህ አዋጅ መቋቋሙ የተገለጸ ሲሆን፣ ግብረ ሀይሉ አስፈላጊ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ፦
• ፖሊስን ጨምሮ ማንኛውንም የፀጥታ ሃይል ትጥቅ እንዲፈቱ ማድረግ፣ 
• የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ጨምሮ አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸው ሌሎች እንቅስቃሴዎች 
ላይ ገደብ መጣል፣ 
• የሰአት እላፊ ገደብ የማውጣት፣ 
• የጦር መሳሪያ እንቅስቃሴዎችን የማስቆም፣
• የመገናኛ ዘዴዎች እንዲቋረጡ የማድረግ፣ እንዲሁም 
• ህገ ወጥ በሆነ ተግባር ላይ ተሳትፈዋል ብሎ የጠረጠራቸውን ግለሰቦችና ቡድኖች የመያዝና የማቆየት ኃላፊነት ይኖረዋል መባሉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡።

24 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተደመሰሱ

24 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተደመሰሱ

****************

በህወሃት ደጋፊነት በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ አካባቢ በነዋሪዎች ላይ ጭቃኔ የተሞላበት ግድያና ጥቃት ያደረሱ 24 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መደምሰሳቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡

ሰሞኑን የኦነግ ሸኔ ቡድን በፈጠረው የሽብር ተግባር የዜጎች ህይወት ማለፉና ንብረት መውደሙ የሚታወስ ነው።

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ዘግናኝ የግድያ ጥቃትና የንብረት ማውደም ባደረሱ የኦነግ ሸኔ ቡድን አባላት ላይ የክልሉ ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን እርምጃ መውሰዱን ገልጸዋል።

በተለይ በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ አካባቢ በነዋሪዎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት በኦነግ ሸኔና በህወሃት ደጋፊነት የተወሰደው እርምጃ በጣም አሳዛኝ እንደነበር ይታወቃል ብለዋል።

የክልሉ ፖሊስ ድርጊቱ በተፈጸመበት አካባቢ ባደረገው ክትትል በምዕራብ ኦሮሚያ እና በደቡብ ኦሮሚያ በኦነግ ሸኔ ላይ በተደረገ ክትትልና በተወሰደው እርምጃ እስካሁን 24  የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መደምሰሳቸውን አስታውቀዋል።

26 የሚሆኑ የኦነግ ሸኔ አባላት መማረካቸውን እና 23 የሚሆኑት ደግሞ በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ለጸጥታ ኃይሉ መስጠታቸውን ኮሚሽነሩ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን