Monday, March 24, 2014

ከሰው ለሰው ድራማ የሚገኘው ገቢ ለማንም እንዳይከፈል በፍርድ ቤት እግድ ተጣለበት

በየሳምንቱ ረቡዕ ማታና በድጋሚ ቅዳሜ ላለፉት 127 ሳምንታት በመተላለፍ ላይ ካለው ‹‹ሰው ለሰው›› ድራማ የሚገኘው ማንኛውም ዓይነት ገቢ ለማንም እንደይከፈል፣ መጋቢት 2 ቀን 2006 ዓ.ም. በፍርድ ቤት ዕግድ ተጣለበት፡፡

ክፍያው እንዳይፈጸም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግልግል ዳኞች ክልከላ የተጣለባቸው፣ አቶ መስፍን ጌታቸው (በአሁኑ ጊዜ የድራማው ፕሮዲዩሰርና ዳይሬክተር) አቶ ሰለሞን ዓለሙ (ስክሪፕት ጸሐፊ ተዋናይ)፣ አቶ ነብዩ ተካልኝ (የኢትዮ ኢንተር ኤጁኬት ፕሮሞሽን ባለቤት)፣ የአቶ ዳንኤል ኃይሌና የአቶ ሰለሞን ዓለሙ ስፓርክ ፊልም ፕሮዳክሽን የሚባለው ድርጅት ናቸው፡፡

የግልግል ዳኞቹ የዕግድ ትዕዛዙን ያስተላለፉበት ምክንያት፣ የሰው ለሰው ድራማ ፕሮዲዩሰርና በድራማው ‹‹ናርዶስ›› የምትባለውን ገጸ ባህሪ ወክላ የምትተውንና በፋይናንስና አድሚኒስትሬሽን ኃላፊነት ትሠራ ከነበረችው ወ/ሮ ብሥራት ገመቹ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ክስ በመመሥረቱ መሆኑን የዕግድ ትዕዛዙ ያስረዳል፡፡

ወ/ሮ ብሥራት ገመቹ፣ አቶ ነብዩ ተካልኝ፣ አቶ መስፍን ጌታቸው፣ አቶ ሰለሞን ዓለሙና አቶ ዳንኤል ኃይሌ ታኅሣሥ 22 ቀን 2003 ዓ.ም. በሰነዶችና ማረጋገጫና ምዝገባ ጽሕፈት ቤት ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ለማዘጋጀት ተስማምተው የሽርክና ውል መፈራረማቸውን የክስ ማመልከቻው ያስረዳል፡፡


ቀድሞ ‹‹የመጨረሻው ሰሞን›› የሚል ስያሜ ሰጥተውት የነበረውን ድራማ ‹‹ሰው ለሰው›› በማለት ሰይመው ለመሥራት ሲስማሙ፣ ወ/ሮ ብሥራትና ሦስቱ ተከሳሾች የትርፍ ክፍፍላቸውን በመቶኛ እንደየተሳትፏቸው ለመከፋፈል ተስማምተው መፈራረማቸው በሰነዶቹ ላይ ተጠቅሷል፡፡

ኢትዮ ኢንተር ኤጁኬት ፕሮሞሽን በተባለው የአቶ ነብዩ ተካልኝ የንግድ ድርጅት ፈቃድ፣ ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጋር ውል ተፈራርመው ‹‹ሰው ለሰው›› ድራማን በመሥራት ላይ እያሉ፣ ንግድ ፈቃዳቸውን ሲያድሱ የአቶ ሰለሞን ዓለሙ ድርጅት መሆኑ በተጠቀሰው ስፓርክ ፊልም ፕሮዳክሽን በሚል ድርጅት ስም በማደስ፣ ከሳሽ ወ/ሮ ብሥራት የትርፍ ተካፋይ የማትሆንበት አሠራር መጀመሩን ክሱ ይገልጻል፡፡  22 ማዞሪያ አካባቢ በሚገኘው ቡና ባንክ ቅርንጫፍ አቶ ሰለሞን ዓለሙና አቶ መስፍን ጌታቸው በጋራ ሒሳብ ሲያንቀሳቅሱ እንደነበርም የክሱ አቤቱታ ይጠቁማል፡፡

ለድራማው ቀረፃ ቤቷንና መኪናዋን በማቅረብ ተባብራ ስትሠራ የነበረችው ከሳሽ ወ/ሮ ብሥራት ድራማው ከተጀመረ ጀምሮ በፕሮዲዩሰርነት፣ በፋይናንስ አድሚኒስትሬሽን በወር አምስት ሺሕ ብር ተከፍሏትና ‹‹ናርዶስ›› የተባለችውን ገጸ ባሕሪ ወክላ ትሠራ እንደነበርም ለፍርድ ቤት ያቀረበችው ሰነድ ያብራራል፡፡

በመሆኑም በኃላፊነትም ሆነ በተዋናይነት እንዲሁም ከትርፍ ሊከፈላት የሚገባው ክፍያ ሳይፈጸምላት፣ ለጊዜው በግልጽ መግለጽ በማትፈልገው ምክንያት ከአንዱ ተከሳሽ ጋር አለመግባባት በመፈጠሩ፣ ከድራማው 54ኛ ክፍል ጀምሮ ‹‹ናርዶስ››ን ሆና ትተውንበት የነበረውን ገጸ ባህሪ መነጠቋን፣ ከ90ኛው ክፍል ጀምሮ ደግሞ ከፕሮዲዩሰርነቷ መሰረዟን በክሷ ለፍርድ ቤቱ አስረድታለች፡፡ ከድራማው 26ኛ ክፍል ጀምሮም የገቢ ክፍፍል እንዳልተፈጸመላት አክላለች፡፡

አቶ መስፍንና አቶ ሰለሞን ከተለያዩ ስፖንሰሮችና ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት መጠኑን ያላወቀችው ክፍያ እያሰባሰቡ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት መሆኑን፣ አቶ ዳንኤል የተባሉት ተከሳሽም የጥቅም ተጋሪ መሆናቸውን አስረድታ፣ 100 ሺሕ ብር በካሽ አዋጥታ ካቋቋመችው የድራማ መድረክ በዕውቀትና በዓይነት ከሰጠችው አገልግሎት በላይ ሞራል የሚነካ (ለኢትዮጵያ ሕዝብ ክብር ሲባል የማይገለጽ) ተግባር እንደተፈጸመባት በክሷ ዘርዝራ አቅርባለች፡፡

ከሳሽ ወ/ሮ ብሥራት ከቴሌቪዥን፣ ከማስታወቂያና ከስፖንሰሮች ከተሰበሰበውና የአገር ውስጥ ገቢ ተቀንሶ የሚደርሳት 16.25 በመቶ ድርሻዋ በወራት ተባዝቶ ከነወለዱ እንዲከፈላት፣ በፋይናንስና አድሚኒስትሬሽን ለሠራችበት በወር የሚከፈላትን አምስት ሺሕ ብር በ35 ወራት ተባዝቶ እንዲከፈላት፣ ‹‹ናርዶስ›› የምትባለውን ገጸ ባህሪ ወክላ ለተወነችበት 56 ክፍሎች በ500 ብር ታስቦ በድምሩ 163 ሺሕ ብር እንዲከፈላት ዳኝነት ጠይቃለች፡፡

የከሳሽን አቤቱታ ዝርዝር ማብራሪያ የተመለከተው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ ሁለተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት በሰጠው ብይን፣ ከሳሽና ተጠሪዎች እያንዳንዳቸው አንድ ዳኛ እንዲመርጡ፣ የግራ ቀኙን ተከራካሪ የሚሰበስብ ዳኛ በጋራ እንዲመርጡና በሽምግልና ዳኝነት እንዲታይ የተወሰነ ቢሆንም፣ በአንድ ወር ውስጥ መምረጥ ባለመቻላቸው በፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር በኩል የግልግል ዳኛ እንዲሾም አዞ ነበር፡፡

የግልግል ዳኞች በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን አቤቱታ በመመርመር ላይ ቢሆኑም፣ ከሳሽ ወ/ሮ ብሥራት የግልግል ዳኝነቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከድራማው የሚገኘው ገቢ እንዲታገድላት ለግልግል ዳኞቹ ማመልከቻ በማቅረብዋ፣ የግልግል ዳኞቹ በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 154 መሠረት ክርክሩ እልባት እስከሚያገኝ፣ ለተጠቀሱት ተከሳሾችም ሆነ ለሦስተኛ ወገን ምንም ዓይነት ክፍያ እንዳይፈጸም የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥንን ድርጅት ታዟል፡፡

Sunday, March 23, 2014

ጎበዝ ከዚህ ሁሉ ሰማይ ላይ ካለው የሳተላይት ጋጋታ የኢትዮጵያ ደብተራ ወይም ጠንቋይ ሳይሻል አይቀርም

እያንጓላለው እንዲሉ የማሌዥያውን አየር መንገድ በረራ MH370 አንዴ እዚህ ታዬ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወዲህ ከሚሉ እነሱን ደብተራ ወይም ጠንቋይ ማማከሩ ጥሩ አይመስላችሁ? እነሱ በሰማይ የሚያይ እውር ሳተላይት ቢኖራቸው እኛ ደግሞ ከመሬት ሆኖ ሁሉን የሚያ አለን።

Saturday, March 22, 2014

በሄሊኮፕተር አሜሪካ መግባት ተቻለ እንዴ? ከየት ተንስቶ ከአዲስ አበባ?

በሄሊኮፕተር አሜሪካ መግባት ተቻለ እንዴ? ከየት ተንስቶ ከአዲስ አበባ? እረ ተው ጥሩ አይደለም። የ አሜሪካን ድንበር በሄሊኮፕተር ተሻግሬ መጣሁ የሚል ቪዲዮ አይቼ በጣም ትንሽ ገረመኝ። የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያምን ይችላል እዚህ ላለኖች ግን ኤዲያ ወዲያ ነው። የክራይ ሄሊኮፕተር (ቱር Tour helicopter) በመስኮት የ ሃጢያጣቷ ከተማ (Sin City) ላስቬጋስ (Las Vegas) ወለል ብላ እየታዬች። እረ ምነው? በኔ ገምት ቪዲዮውን በ አቸኳይ ቀየር፣ ወጣ ማደርግ ነው። ወንድማዊ ምክር ነው

የዳላስ ቴክሳሷ አሰተማሪ አምሰት ልጆችን በሰላም ተገላገለች::

የዳላስ ቴክሳሷ አሰተማሪ አምሰት ልጆችን በሰላም ተገላገለች

Texas teacher gives birth to quintuplets at Dallas hospital

Steven and Michelle Seals of Maud, Tex., welcomed Mia, Tessa, Bryant, Gracie and Rayleigh into the world on Tuesday. The quintuplets are the first to be born at Baylor University Medical Center and weighed between 2 pounds, 7 ounces and 3 pounds, 6 ounces. Doctors say the tiny infants have ‘done remarkably well.’

 

በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ተነስቶ የነበረው እሳት በቁጥጥር ስር ዋለ

ዲስ አበባ  መጋቢት 13/2006  በአዲስ አበባ በአራት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ተነስቶ የነበረው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉን የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከያና መቆጣጠሪያ ባለስልጣን አስታወቀ።በእሳት ቃጠሎው አንድ ከባድና አምስት ቀላል ጉዳት ደርሷል፡፡
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኦፕሬሽን ዘርፍ ሃላፊ ኮማንደር አማኑኤል ረዳ እንደተናገሩት ዘጠኝ ሰአት ከ12 ጥሪ እንደደረሳቸው፣ በሁለት ደቂቃ ቦታው ላይ በመገኘት በሰላሳ ደቂቃ እሳቱን በቁጥጥር ስር ውሏል።
እሳቱ የተነሳው በድርጅቱ የወረቀት መጋዘን ሲሆን የቃጠሎው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን በንብረት ላይም ግምቱ ያልታወቀ ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል።
በአደጋው አራት የእሳት አደጋ ሰራተኞች ላይ ቀላል ጉዳት አድርሷል።
አደጋውን ለመቆጣጠር አስር መኪናዎች በምልልስ የሰሩ ሲሆን ንብረቶችን በማንሳት አንዳንድ የማጣሪያ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም በመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች፣ በፌደራል እና በአዲስ አበባ ፖሊስ በኩል ለተደረገላቸው ከፍተኛ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተካ አባዲ በበኩላቸው በ9 ሰዓት ገደማ የተነሳው እሳት ምክንያት ምን እንደሆነ አሁን ለመናገር ቢያስቸግርም ምናልባት እሳት ወይም መብራት ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
በአደጋው በመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ላይ አንድ ከባድና አንድ ቀላል  አደጋ ደርሷል።
እሳት የተነሳበት ጊዜያዊ የድርጅቱ መጋዘን ላይ  ሲሆን ዋናውና ትልቁ መጋዘን በሌላ ቦታ ይገኛል።
እሳቱ የድርጅቱ የህትመት ስራዎች ላይ የህትመት መቋረጥም ሆነ ሌላ ምንም አይነት ተጽእኖ እንደማይፈጥር  ዋና ሥራ አስፈፃሚው ተናግረዋል፡፡
የመስሪያ ቤቱን ሰራተኞች ጨምሮ ትብብር ላደረገላቸው አካል ሁሉ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።

አዲስ አበባ አዲስ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሊሰራ ታስቧል ተባለ

አዲስ አበባ አዲስ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሊሰራ ታስቧል ተባለ
The Addis Ababa and Oromia Integrated Development Plan Project Office has drafted a plan for a grand airport to be built on the western outskirts of Addis Ababa in the Oromia special zone.
Reports indicate that the airport forms part of a new metropolitan capital master plan that includes the relocation of the Bole International Airport, one of the major hubs on the continent.
Fetuma Lemessa, Deputy Manager of the Addis Ababa and The Surrounding Oromia Integrated Development Plan Project Office, told Capital FM that Teji, about 30km west of Addis Ababa on the road to Jimma, is the proposed site for the location of the new airport.
The project office had been working on refining the new master plan for the past year, reports indicate.
The proposed plan, which work will commence on in a year, replaces the ten-year old master plan for Addis Ababa and incorporates several new details.
Reports indicate that the growth in air traffic at the Addis Ababa Bole International Airport prompted the Ethiopian Airport Enterprise to plan on building a new international airport between the towns of Mojo and Meki on the road to Hawassa, about 90km southeast of Addis.
The Ethiopian Airport Enterprise had reportedly been conducting a study on the establishment of a new international airport for some time.
When the major expansion project at the Addis Ababa Bole International Airport was drafted in the early 1990s, it was assumed that the airport would adequately accommodate air traffic easily up until 2017. However, the airport reached its maximum capacity in 2010, hence, the need to venture into the construction of a new international airport.
According to the master plan, the new airport’s location was favored for several reasons, including the fact that it is relatively close to the capital than the original planned location.
Officials have disclosed that the Addis Ababa Bole International Airport will be used for regional and domestic flights, VIP flights and other general aviation services. “The new airport is expected to accommodate long-haul international flights,” he said.
According to information obtained from the Public Relations Department of Ethiopian Airlines, Addis Ababa Bole International Airport currently accommodates an average of 800 departures per week.
The capacity of Ethiopian Airlines is also growing swiftly in terms of the number of airplanes and destinations. The national flag carrier currently operates 58 airplanes providing services to 72 destinations, of which 45 are in Africa

Breaking News ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በእሳት እየጋየ ነው ተባለ

Breaking News
እውነት ይሁን ውሸት አይታዎቅም
ማተሚያ ቤቱ ቃጠሎ ደርሶበታል።