Shop Amazon

Saturday, March 22, 2014

በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ተነስቶ የነበረው እሳት በቁጥጥር ስር ዋለ

ዲስ አበባ  መጋቢት 13/2006  በአዲስ አበባ በአራት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ተነስቶ የነበረው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉን የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከያና መቆጣጠሪያ ባለስልጣን አስታወቀ።በእሳት ቃጠሎው አንድ ከባድና አምስት ቀላል ጉዳት ደርሷል፡፡
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኦፕሬሽን ዘርፍ ሃላፊ ኮማንደር አማኑኤል ረዳ እንደተናገሩት ዘጠኝ ሰአት ከ12 ጥሪ እንደደረሳቸው፣ በሁለት ደቂቃ ቦታው ላይ በመገኘት በሰላሳ ደቂቃ እሳቱን በቁጥጥር ስር ውሏል።
እሳቱ የተነሳው በድርጅቱ የወረቀት መጋዘን ሲሆን የቃጠሎው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን በንብረት ላይም ግምቱ ያልታወቀ ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል።
በአደጋው አራት የእሳት አደጋ ሰራተኞች ላይ ቀላል ጉዳት አድርሷል።
አደጋውን ለመቆጣጠር አስር መኪናዎች በምልልስ የሰሩ ሲሆን ንብረቶችን በማንሳት አንዳንድ የማጣሪያ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም በመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች፣ በፌደራል እና በአዲስ አበባ ፖሊስ በኩል ለተደረገላቸው ከፍተኛ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተካ አባዲ በበኩላቸው በ9 ሰዓት ገደማ የተነሳው እሳት ምክንያት ምን እንደሆነ አሁን ለመናገር ቢያስቸግርም ምናልባት እሳት ወይም መብራት ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
በአደጋው በመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ላይ አንድ ከባድና አንድ ቀላል  አደጋ ደርሷል።
እሳት የተነሳበት ጊዜያዊ የድርጅቱ መጋዘን ላይ  ሲሆን ዋናውና ትልቁ መጋዘን በሌላ ቦታ ይገኛል።
እሳቱ የድርጅቱ የህትመት ስራዎች ላይ የህትመት መቋረጥም ሆነ ሌላ ምንም አይነት ተጽእኖ እንደማይፈጥር  ዋና ሥራ አስፈፃሚው ተናግረዋል፡፡
የመስሪያ ቤቱን ሰራተኞች ጨምሮ ትብብር ላደረገላቸው አካል ሁሉ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment