የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Saturday, November 7, 2020

24 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተደመሰሱ

24 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተደመሰሱ

****************

በህወሃት ደጋፊነት በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ አካባቢ በነዋሪዎች ላይ ጭቃኔ የተሞላበት ግድያና ጥቃት ያደረሱ 24 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መደምሰሳቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡

ሰሞኑን የኦነግ ሸኔ ቡድን በፈጠረው የሽብር ተግባር የዜጎች ህይወት ማለፉና ንብረት መውደሙ የሚታወስ ነው።

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ዘግናኝ የግድያ ጥቃትና የንብረት ማውደም ባደረሱ የኦነግ ሸኔ ቡድን አባላት ላይ የክልሉ ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን እርምጃ መውሰዱን ገልጸዋል።

በተለይ በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ አካባቢ በነዋሪዎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት በኦነግ ሸኔና በህወሃት ደጋፊነት የተወሰደው እርምጃ በጣም አሳዛኝ እንደነበር ይታወቃል ብለዋል።

የክልሉ ፖሊስ ድርጊቱ በተፈጸመበት አካባቢ ባደረገው ክትትል በምዕራብ ኦሮሚያ እና በደቡብ ኦሮሚያ በኦነግ ሸኔ ላይ በተደረገ ክትትልና በተወሰደው እርምጃ እስካሁን 24  የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መደምሰሳቸውን አስታውቀዋል።

26 የሚሆኑ የኦነግ ሸኔ አባላት መማረካቸውን እና 23 የሚሆኑት ደግሞ በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ለጸጥታ ኃይሉ መስጠታቸውን ኮሚሽነሩ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን 

Friday, November 6, 2020

ከወንበዴው ህዋሃት የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በህዝብ እልቂት በማድረስ አገርን ለማፍረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጥፋት ቡድኖች በቁጥጥር ሥር

ከወንበዴው ህዋሃት የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በህዝብ እልቂት በማድረስ አገርን ለማፍረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጥፋት ቡድኖች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
*************************

ከወንበዴው ህዋሃት የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በህዝብ እልቂት በማድረስ አገርን ለማፍረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጥፋት ቡድኖች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጉዳዩን አስመልክቶ ለኢቲቪ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ከወንበዴው ህዋሃት የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው በጋምቤላ ክልል በብሔር ብሄረሰቦች መካከል ግጭት በመፍጠር አካበቢውን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሀይሎች በተደረገባቻው ጥብቅ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውሷል፡፡

የዚህ የጥፋት ቡድን አካል የነበሩ ነገር ግን ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ተልዕኮቸውን በድብቅ ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አለም ደስታ ሃየሎምና ጋትክቦም የተባሉ የጥፋት ቡድኑ ተጠርጣሪዎች ባሉበት ታድነው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል፡፡

ቀደም ሲል ይፋ በተደረገው መረጃ ላይ እንደተመለከተው፤ በህዝብ ላይ እልቂት በመፈጸም ክልሉን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት ተጠርጣሪዎች መካከል ጸጋዬ መብርሃቱ (ካህሳይ)፣ ገብረማሪያም አናንያ፣ ዋስትና ተሾመ (ጃል ሴና)፣ አብርሃም መሃሪ፣ ኮሎኔል ተስፋዬ (ባሌስትራ) እና በድምሩ 19 የወንበዴው የህዋሃትና የኦነግ ሸኔ የጥፋት ኃይሎች በቁጥጥር እንደዋሉ መግለጫው አስታውሷል።

በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ተፈጽሞ የነበረውን ተመሳሳይ ጥፋት በአሶሳና ካማሼ ዞኖች ብሔር ብሄረሰቦችን በማጋጨት አካበቢውን የትርምስ ቀጠና በማድረግ በህዝብ ላይ እልቂት ለመፈጸም ከወንበዴው ህዋሃት የጥፋት ቡድን አባል ከሆነው አባይ ፀሃዬ ተልዕኮ ወስደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጥራጥሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መገለፁ ይታወቃል፡፡

 የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ በተጨማሪም አራት የወንበዴው የህዋሃት የጥፋት ቡድን አባላት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ተደርጓል። 

የተያዙት አራት የዚህ የጥፋት ቡድን አባላት ተጠርጣሪዎችም ተክላይ ገብረ መድህን ፣ ፍሰሃ ወልደ እግዚአብሄር ፣ አብርሃ ገብረ ሚካኤል እና ተስፋ ገብረ ሚካኤል የተባሉ መሆናቸውን አገልግሎቱ በላከው መግለጫ አስታውቋል። 

ከወንበዴው ህዋሃት የጥፋት ቡድን ተልዕኮ በመቀበል በህዝብ ላይ ጭፍጨፋ እንዲፈጸም ስምሪት የተሰጣቸው አራት ከላይ የተገለፁት የጥፋት ሃይሎች በእጃቸው 59 የሚሆኑ የባንክ ደብተሮችን የያዙ ሲሆን፤ ተክላይ ገብረ መድህን የተባለው ተጠርጣሪ በአገር ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ባንኮች 19 የሂሳብ ደብተሮችን ከፍቶ ሲያንቀሳቅስ ከመቆየቱም በላይ በአንዱ የሂሳብ ደብተር ውስጥ ብቻ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ መገኘቱን መግለጫው ጠቁሟል ። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማነ ግርማይና ዮሃንስ ግርማይ የተባሉ የህዋሃት የጥፋት ቡድን ተላላኪዎችን ጨምሮ በድምሩ 23 ተጠርጥሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስተውቋል፡፡

ከወንበዴው ህዋሃት የጥፋት ቡድን ተመሳሳይ ተልዕኮ ተቀብለው በአዲስ አበባ ከተማና በዙሪያው በከፍተኛ ባለስልጣናትና በንፁሃን ዜጎች ላይ እንዲሁም በትላልቅ መሰረተ ልማቶች ላይ ለአብነትም ለገዳዲና ገፈርሳ የሚገኙ የውሃ ግድቦች እንዲሁም በለገጣፎ የሚያልፍ ከፍተኛ የውሃ ማስተላለፊያ መስመር ላይ የፈንጂ ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩ የኦነግ ሸኔ አባላት ለጥፋት ተልዕኳቸው ካዘጋጇቸው ተቀጣጣይ ፈንጂዎችና ሌሎች ቁሶች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብሄራዊ መረጀና ደህንነት አገልግሎት በላከው መግለጫ ገልፆል፡፡ 

የጥፋት ተልዕኮቸው ባይከሽፍ ኖሮ፤ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ሰብኣዊ ቀውስ ያስከትል እንደነበር መግላጫው አስታውሷል፡፡የዚሁ ጥፋት አካል የነበሩትና የጥፋት ቡድኑ ያሰማራቸው ቶሎሳ አብዲሳ፣ ደጀኔ ፍቃዱ፣ ሀብታሙ ተስፋየ መርጋ፤ ንጉሴ አሰፋና ፈልማት ታከለ የተባሉ ተጠርጣሪዎች መሆናቸውን መግላጫው አመልክቷል፡፡

በሌላም በኩል ጋዲሳ ሞሲሳ ባይሳ የተባለው የጥፋት ቡድኑ አካልና ግብርአበሮቹ በአዲስ አበባ በንጹሃን ዜጎች ላይ የቦንብ ጥቃት ለመፈጸም ካዘጋጇቸው ቦንቦች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስተውቋል፡፡

በተለይ የወንበዴው የህዋሃት ቡድን ለጥፋት ተልዕኮው ሽፋን ንስር ጥበቃ ድርጅትን በመጠቀም በስራቸው ከወንበዴው ስልጠና የወስዱ ሃይሎችን በስሩ በማደራጀት በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃት ለመፋፀምና ጥፋት ለማድረስ በዝግጅት ላይ እያሉ በቁጥጥር ስር እንዲውሉም ተደርጓል፡፡ 

የህዋሃት የጥፋት ቡድን በትግራይ ክልል ሃግቦ በተባለ አካባቢ ወታዳራዊ ስልጠና በመስጠት የገዳይ እስኮድ ቡድን ባለቤትነቱ ሀይሉ በርሄ በቅፅል ስሙ ሀይሉ ሳንቲም ተብሎ በሚጠራው የወንበዴው የጥፋት ቡድን አስተባባሪ ስም በተቋቋመው ንስር የግል ጥበቃ ኤጀንሲ ሽፋን ካስገባ በኃላ ነበር ጥቃት ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፌደራል ፖሊስና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በቅንጅት ባደረጉት ጥብቅ ክትትል የቡዱኑ አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋል የተቻለው፡፡

በተመሳሳይ አዲስ አበባ ሆኖ ለወንበዴው ለህዋሃት የጥፋት ቡድን የተለያዩ መረጃዎችን እያሰባሰበ ሲልክ የነበረና ከኦሮሚያ ወጣቶችን እየመለመለ ለስልጠና ወደ ትግራይ በመላክና የተለያዩ የአመፅ ተልዕኮዎችን ከጥፋት ቡድኑ በመቀበል ኦሮሚያ ክልል ለሚገኙ የኦነግ ሸኔ የጥፋት ቡድኖች ሲያስተላልፍ የነበረው ቶማስ ገብረማሪያም የተባለው ተጠርጣሪም በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የጥፋት ቡድኑ በኦሮሚያ ክልል በአዳማ፤በሲዳማ ክልል ሃዋሳ፤በደቡብ ክልል ደግሞ በወላይታ፤ ጋሞጎፋ፤ሃድያ፤ስልጤና ጌዲዮ ዞኖች እንዲሁም በሱማሌ ክልል ጅጅጋና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተመሳሳይ ትርምስና እልቂት በተላላኪዎች ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ በድምሩ 21 ተጠርጣሪዎች በተለያዩ የጦር መሳሪዎችና መሰል ቁሳቁሶች ጋር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን አግልግሎት መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡ 

በመጨረሻም ለዚህ ኦፕሬሽን ስኬት የአገራችን ህዝቦች ተሳትፎ የማይተካ ሚና ያለው ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፤ የአገር መከላከያ ሰራዊት፤የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፤የክልል ፖሊስ ኮሚሽኖችና ሌሎች የጸጥታ አካላት በቅንጅት ይሄ ዉጤት እንዲመጣ ግዴታቸውን ተወጥተዋል ተብሏል፡፡

ስግብግቡ ጁንታ በህወሓት ውስጥ የመሸገው ኃይል ላይ የተወሰደው የመጀመሪያው ዙር ኦፕሬሽን በስኬት እንደተጠናቀቀ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ

ስግብግቡ ጁንታ በህወሓት ውስጥ የመሸገው ኃይል ላይ የተወሰደው የመጀመሪያው ዙር ኦፕሬሽን በስኬት እንደተጠናቀቀ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ
*************

ባለፉት ሁለት ቀናት ስግብግቡ ጁንታ በህወሓት ውስጥ የመሸገው ኃይል፣ ለስልጣን የሚስገበገበው፣ ለገንዘብ የሚስገበገበው፣ ለሀገር ሉዐላዊነት ለሕዝቦች ደህንነት ደንታ የሌለው ኃይል በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመከላከያ ሰራዊት እንዲሁም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፖሊስ ሰራዊት ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ይታወሳል።

ይህ ጥቃት ድንገተኛ ቢሆንም የመጀመሪያው የመከላከል እቅድ ሙሉ ለሙሉ በስኬት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል።

የእቅዱ ዋነኛ አላማዎች 1ኛ ጥቃቱን መግታት- የመጀመሪያው ዓላማ ጠላት በሁሉም አቅጣጫ ጥቃት እየሰነዘረ በህዝብ፣ በሰራዊቱ፣ በፖሊስ ላይ እና በአንዳንድ ወሳኝ የመሰረተ ልማቶች ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት መግታት ነበር። 

ከዚህ አንፃር በተለያየ አካባቢ ይገኝ የነበረ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ወደ ስፍራው በማንቀሳቀስ የጠላትን ጉዞን ሙሉ ለሙሉ በማስቆም ተጨማሪ ጥቃት መሰንዘር ወደማይችልበት ደረጃ ማድረስ ተችሏል ብለዋል።

ሁለተኛው አላማ የመከላከያ እና የፖሊስ ሰራዊት የደረሰበትን ጥቃት ተከትሎ ይህንን ኃይል የመታደግ እና ወሳኝ ሀገራዊ ሀብቶች አና ትጥቆች የመታደግ ስራ እንደነበር ተገልጿል።

ከዚህ አንፃርም በባድመ ግንባር፣ በፆረና እና በዛላንበሳ በዋና ዋና ስፍራ ተሰልፈው ያሉ የሰራዊት አባላት እና ትጥቆች ሙሉ ለሙሉ ከጠላት ፍላጎት ውጭ ለማድረግ ተችሏል።

 
3ኛው አላማ የጠላትን የማድረግ አቅም ማዳከም ነው። የጠላት ኃይል የኢትዮጵያ ህዝብ ከሌለው ሀብት ላይ ቀንሶ ሀገሩን ለመከላከል የገዛቸውን ዋና ዋና ትጥቆች፣ ሚሳኤሎች፣ ሮኬቶች በመጠቀም ጥፋት ማካሄድ እንዳይችል አቅሙን ማዳከም ነበር።

በዚህም ሦስቱ ዓላማዎች መቶ በመቶ መሳካታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም በዳንሻ ግንባር ያለውን ጠላት ሙሉ ለሙሉ በመደምሰስ አካባቢውን መቆጣጠር መቻሉንም አስታውቀዋል።

በቀጣይም ስግብግቡ ጁንታ ሙሉ ለሙሉ ለሕግ እስከሚቀርብ ድረስ የሚደረገው እራስን እና ሀገርን የመከላከል ዘመቻ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አረጋግጠዋል። 

የአየር ሀይሉ በወሰደው እርምጃም በተለያዩ ስፍራዎች ላይ የነበሩ ሮኬቶችን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ለማውደም መቻሉንም ገልፀዋል።

እነዚህ ሮኬቶች እስከ 300 ኪሎ ሜትሮች መወንጨፍ የሚችሉ በመሆናቸው እና በወንጀለኛው ቡድን ሮኬቶቹን የመጠቀም ፍላጎት በመኖሩ በመቀሌ እና አካባቢዋ በነበረው የከባድ መሳሪያ ማስቀመጫ ላይ የአየር ኃይሉ እርምጃ እንዲወስድ መደረጉ ተገልጿል።

በአስማማው አየነው 

Ethiopia, Austria sign air service agreement

ኢትዮጵያ እና ኦስትሪያ የአየር በረራ አገልግሎት ስምምነት ተፈራረሙ 
********************* 

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግሥት ከኦስትሪያ ፌዴራል መንግሥት ጋር እ.ኤ.አ. ታኅሣሥ 10/2013 በአጭር ፊርማ የነበረውን የአየር በረራ አገልግሎት ስምምነት የተሻለ የበረራ ምልልስ እና የሕግ መሠረት በሚሰጥ መልኩ በትላንትናው ዕለት አዲስ አበባ ላይ በተካሄደ የምክክር ስብሰባ አሻሽሎ ተፈራረመ። 

ስምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኮ/ል ወሰንየለህ ሁነኛው እና የኦስትሪያ ፌዴራል መንግሥት በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ የኦስትሪያ አምባሳደር ሚስተር ሮላንድ ሐውሰር ተፈራርመዋል። 

የስምምነቱ በሙሉ ፊርማ ደረጃ መጠናቀቅ ለብሔራዊ አየር መንገዱ የበረራ መብቶች ሕጋዊ መሠረት የሚሰጥ መሆኑን እና የበረራ ምልልሱንም በየጊዜው በሚኖረው የአየር ትራፊክ ገበያ ልክ ማሳደግ የሚያስችል መሆኑን በባለሥልጣኑ የኢኮኖሚክ ሬጉሌሽንና ስትራተጂክ አመራር ዳይሬክተር አቶ እንደሻው ይገዙ ገልጸዋል። 

እንደ አቶ እንደሻው ገለፃ ስምምነቱ ተወካይ አየር መንገዶች ከበረራ የሚያገኙትን ገቢ ከተደራራቢ ግብር ነፃ የሚያደርግ፣ ከአዲስ አበባ እና ቪዬና ከተሞች በተጨማሪ በከተሞቹ መካከል እና ባሻገር ባሉ ሌሎች መዳረሻ ከተሞች የበረራ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል እና አየር መንገዶችን በሽርክና እንዲሠሩ የሚፈቅድ ነው። 

ስምምነቱ ኢትዮጵያ ከኦስትሪያጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት በበለጠ የሚያጠናክር እና በሀገራዊው የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ዓለም አቀፍ የበረራ መዳረሻዎችን ቁጥር ማሳደግ በሚል የተጣለውን ግብ ስኬታማነት የሚያረጋግጥ ይሆናል። 

ከዚህ በተጨማሪም የአየር ትራንስፖርቱ ንግድ እና ኢንቨስትመንትን በማበረታታት፣ የወጪ ንግዱን በመደገፍ፣ ቱሪዝምን በማስፋፋት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በውጭ ምንዛሪ ግኝት ያለውን ሚና እንደሚያጎለብት ይታመናል ሲል የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አስታውቋል። 
Sourcev EBS

በጅማ ከተማ ባለፉት ሁለት ቀናት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በጅማ ከተማ ባለፉት ሁለት ቀናት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
**************** 

በጅማ ከተማ ባለፉት ሁለት ቀናት በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ በህዝብ ላይ ጥቃት ለማድረስ የተዘጋጁ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት 8 ሽጉጦች፣ 7 ክላሾች፣ ከ130 በላይ የተለያዩ ጥይቶች፣ የጦር ሜዳ መነፅር እና የተለያዩ አገራት ፓስፖርቶች ከያዙ 31 ተጠርጣሪዎች ናቸው። 

በህዝቦች መካከል ልዩነት በመፍጠር ኢትዮጵያን ወደ ብጥብጥ የሚመሩ አካላትን በፅኑ እንደሚያወግዙም የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ገልፀዋል። 

በወቅታዊ የጅማ ከተማና አካባቢው ሰላም ላይ ውይይት እያደረጉ የሚገኙት ነዋሪዎቹ የአካባቢውን ሰላም ነቅቶ ለመጠበቅ መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል። 

በከሀዲው የህውኃት ቡድን በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊታችን ላይ የተሰነዘረው ጥቃት አሳዛኝ፣ አሳፋሪም ነው ያሉት ነዋሪዎቹ ቡድኑ ድባቅ እስኪመታ ድረስ ከአገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በፅናት እንደሚቆሙም ነዋሪዎቹ አረጋግጠዋል። 
በዮናስ ካሳ

Ethiopian Civil Aviation Authority announces closure of Mekelle, Shere, Axum and Humera airports

Ethiopian Civil Aviation Authority announces closure of Mekelle, Shere, Axum and Humera airports


የመቐለ፣ ሽረ፣ አክሱም አና ሁመራ ኤርፖርቶች ለማንኛውም የበረራ አገልግሎት ዝግ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ
*************************

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ከዛሬ ጥቅምት 27/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ የመቐለ፣ ሽረ፣ አክሱም አና ሁመራ ኤርፖርቶች ለማንኛውም የበረራ አገልግሎት ዝግ መሆናቸውን አስታወቀ። 

ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በተመሳሳይ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት (ኤርሜንስ) በተገቢው የመገናኛ ዘዴ በ(ኖታም) አንዲያውቁት መደረጉንም አስታውቋል።

Thursday, November 5, 2020

Ethiopia, Israel agree to work together on information and security

ኢትዮጵያ እና እስራኤል በመረጃ እና ደህንነት ዘርፍ ተባብረው ለመሥራት ተስማሙ
******************
Ethiopia, Israel agree to work together on information and security ****************** Ethiopia and Israel have agreed to work together in the information and security sector, according to the National Intelligence and Security Service. Israeli Deputy Minister of Security Gadi Yvirkan met with Director General of the National Intelligence and Security Service Demlash Gebremichael. During the meeting, the two countries agreed to work together to fight terrorism, exchange information, transfer technology and build capacity in the Horn of Africa.

"Ethiopia and Israel can work together in the information and security sector to strengthen peace and stability in the Horn of Africa," he said.
For his part, Deputy Foreign Minister Gadi Yvirkan said Ethiopia wants to further strengthen its cooperation with Ethiopia in the information and security sector as it has a significant role to play in maintaining peace and stability in the Horn of Africa.
He also said that Israel supports the change initiated by Ethiopia in the information sector. 



ኢትዮጵያ እና እስራኤል በመረጃ እና ደህንነት ዘርፍ ተባብረው ለመሥራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ።
የእስራኤል ደህንነት ምክትል ሚኒስትር ጋዲ ይቫርካን ከብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል ኮሚሽነር ደምላሽ ገብረሚካኤል ጋር ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም ሁለቱ አገራት በአፍሪካ ቀንድ ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት፣ የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በአቅም ግንባታ ዘርፍ ይበልጥ ተባብረው ለመሥራት መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ እና እስራኤል በመረጃ እና ደህንነት ዘርፉ ተባብረው ቢሠሩ በአፍሪካ ቀንድ እና አካባቢው ሰላም እና መረጋጋት በማጠናከር በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ይችላሉ ሲሉ ኮሚሽነር ደምላሽ በውይይቱ ገልጸዋል።
ምክትል ሚኒስትር ጋዲ ይቫርካን በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ሰላም እና መረጋጋት በማስፈን ረገድ ትልቅ ሚና ያላት እና ተሰሚ በመሆኗ ምክንያት እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር በመረጃ እና ደህንነት ዘርፉ ያላትን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር ትፈልጋለች ብለዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ በመረጃ ዘርፍ የጀመረችውን ለውጥ እስራኤል እንደምትደግፍም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ እና እስራኤል በመረጃ እና ደህንነት ዘርፍ በጋራ ለመሥራት የደረሱትን ስምምነት በቅርቡ ወደ ተግባር ይሸጋገራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት የላከው መረጃ አመልክቷል።

Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon