የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Tuesday, November 10, 2020

አይን ያወጣ ሙስና። የበለሳ ሊቀመንበር ዘመዶቹን መርጦ ወደ ዘመቻ በመላክ ህዝባዊ ክስ ቀረበበት!



"#የበለሳ ወረዳ # ሊቀመንበር ዘመዶቹን መርጦ ወደ ዘመቻ በመላክ ህዝባዊ ክስ ቀረበበት!

የጋይንት ህዝብ ደግሞ ከኮታ በላይ የዘመች ቁጥር ከአቅም በላይ በመብዛቱ የዘመቻው አስተባባሪዎች ቁጥሩን ለመቀነስ የተጠቀሙበት፣የዕድሜ ጣራ፣የአካል ብቃት ና መሰል የምልመላ ስልት ሁሉ ውድቅ ሁኖባቸው መቸገራቸው ከቅርብ ምንጮች ባረጋገጥኩ ጊዜ...!

#እውነትም #"ጦርነት ሰርግና ምላሹ የሆነ ህዝብ ነው" አልኩ

//////////ይኸው ነው!///////////

በትግራይ የሕግ የበላይነት የማስከበር ስራ በታቀደው መሰረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ

በትግራይ የሕግ የበላይነት የማስከበር ስራ በታቀደው መሰረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ
*************************

በትግራይ የሕግ የበላይነት የማስከበር ስራ በታቀደው መሰረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገልጸዋል፡፡

በትግራይ ክልል የተጀመረው ኦፕሬሽን  ወንጀለኛው ጁንታ የሕወሃት ቡድን  ትጥቅ እንዲፈታ ከተደረገ በኋላ፣ ችግር ፈጣሪዎች ለፍርድ ሲቀርቡ እንዲሁም  በክልሉ ሕጋዊ ተቀባይነት ያለው አስተዳደር ሲመሰረት እንደሚቆም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

ሁሉም ስራዎች በተገቢው ፍጥነት እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትዊተር ገጻቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል፡፡

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን 

 Prime Minister Abiy Ahmed said the rule of law is being implemented in Tigray as planned
 ***************************

 Prime Minister Abiy Ahmed said the rule of law is being implemented in Tigray as planned.

 The operation, which began in Tigray State, will end after the disarmament of the criminal Junta TPLF, the perpetrators will be brought to justice and a legitimate administration will be established in the state, he said.

 In a message posted on his Twitter account, Prime Minister Abiy Ahmed said that all the work is being carried out at the proper pace.

 The right way to get our video information

የኦነግ ታጣቂዎችን ጨምሮ የማፊያው ሕወሓት ቡድን ልዩ ኃይል አባላት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በማድረስ ተሳትፈዋል

"የኦነግ ታጣቂዎችን ጨምሮ የማፊያው ሕወሓት ቡድን ልዩ ኃይል አባላት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በማድረስ ተሳትፈዋል" - ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ 
******************** 

በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ያደረሱ አካላት የማፊያው ሕወሓት ቡድን ልዩ ኃይል፣ የአካባቢው ሚሊሺያ እና በማይታመን መልኩ ደግሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድንም ጭምር እንደነበር ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ አስታወቁ። 

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ውጊያ እየተካሄደባቸው ያሉ የጦር ቀጠናዎችን የጎበኙት ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ፣ የሕወሓት ማፊያ ቡድን በአካባቢው በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰሜን እዝ ላይ ያደረሰውን ጥቃት በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል። 

ሌ/ጄኔራሉ ከሌሎች ጓዶች ጋር በመሆን በአካባቢው ባደረጉት ጉብኝት ማፊያው የሕወሓት ቡድን እየተናገረ እንዳለው የሰሜን እዝ ከማፊያው የሕወሓት ቡድን ጋር በማበር የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እየወጋ እንዳልሆነ ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል። 

የሰሜን እዝ ፈተና ቢገጥመውም እና እንዲሸረሸር በሆዳሞች ጥረት ቢደረግበትም የዓላማ ፅናት ያላቸው የጦሩ አባላት በጀግንነት የሕይወት መሥዋዕትነት በመክፈልም ጭምር ጁንታውን ቡድን ተፋልመዋል ነው ያሉት። 

ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ በሰሜን እዝ ላይ የደረሰውን ጥቃት ሲያብራሩ፣ እዙ በመቐለ በመሸገው ጁንታ አማካይነት ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ ወደ ማጥቃት ከመግባቱ በፊት በሰሜን እዝ ውስጥ የሚገኙ ትግርኛ ተናጋሪዎችን በመጠቀም ሰሜን እዝን ለማፈራረስ አቅዶ እንደነበር ገልጸዋል። 

የወታደሩ ራሽን እና ደመወዝ መላኩን ቀድመው የማረጋገጥ ሥራ ሠርተዋል ያሉት ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ፣ ይህ ከሆነ በኋላ የሰሜን እዝ ከየትኛውም ሠራዊት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳይኖር ሬዲዮ መገናኛውን አቋርጠዋል ብለዋል። 

ለዚህ ዓላማ መሳካትም ዋና የሬዲዮ መገናኛ ኃላፊው በማፊያው ቡድን መጠለፋቸውን እና ከዚያ በኋላ ጁንታው ጥቃት መፈፀሙን ገልጸዋል። 

ግንኙነቱ ከተቋረጠ በኋላ የ20ኛው ክፍለ ጦር አዛዥን ጨምሮ የተወሰኑ የጦር አመራሮችን ማፈናቸውን፣ በተለይም ደግሞ አጋዥ ኃይል የሚባለውን ለ21 ዓመታት የሀገሩን ዳር ድንበር ሲጠብቅ የነበረውን ሠራዊት ምንም ባልተዘጋጀበት ሁኔታ ጨፍጭፈው አስከሬኑን አውሬ እንዲበላው በማድረግ ዘግናኝ ድርጊት መፈፀማቸውን ተናግረዋል። 

የጨፈጨፏቸውን ወታደሮች አስከሬን ራቁት አድርገው እስከ ትላንትናው ዕለት እንዳይቀበር አድርገዋል ያሉት ሌ/ጄኔራሉ፣ በአስከሬኑ ላይ ሲጨፍሩ እንደነበሩም ገልጸዋል። 

ከጭፍጨፋ የተረፉ የሰሜን እዝ ወታደሮችን ልብስ አስወልቀው ራቁታቸውን ወደ ኤርትራ ሠራዊት እንዲቀላቀሉ ማድረጋቸውን፣ ድንበሩን እየጠበቀ የነበረው የኤርትራ ሠራዊት ግን ራቁታቸውን ለሔዱት የሠራዊታችን አባላት ልብስ ማልበሱን መረጃው እንዳላቸው ጠቁመዋል። 

የሰሜን እዝ በርካታ ጥፋቶች ቢፈፀምበትም በተለያዩ መንገዶች ከሌሎች የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር ግንኙነት ፈጥሮ በአሁኑ ሰዓት በእልህ እና ለባንዲራው ባለው ታማኝነት የጠላት ጦርን በተለያዩ ግንባሮች እየደመሰሰ እንደሆነ እና በየቀኑ አዳዲስ ድሎችን እያስመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል። 

በአጠቃላይ የሞት ድግስ የተደገሰለት የሰሜን እዝ ሁሉንም ድል አድርጎ የሀገር ዳር ድንበረን እያስጠበቀ የትግራይን ሕዝብ ከዚህ ግፈኛ ጁንታ ነፃ ለማውጣት እየሠራ እንደሆነ እና ባንዲራውን ከፍ እያደረገ ነው ብለዋል። 

በጥላሁን ካሳ 

Monday, November 9, 2020

በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ዙሪያ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ገለጻ እየተደረገ ነው

በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ዙሪያ  በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ገለጻ እየተደረገ ነው
************************

በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ዙሪያ  በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ገለጻ እየተደረገ ይገኛል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እየተሰጠ ባለው በዚህ ገለጻ፣  ዘራፊው የህወሃት ቡድን በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመው ክህደትና በአገራዊ አንድነት ላይ ያተኮረ ነው፡፡

በመድረኩ የኪነጥበብ ባለሙያዎችና  ታዋቂ ሰዎች እየተሳተፉ ነው፡፡

በአስማማው አየነው

የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሁመራ ኤርፖርትን ተቆጣጣረ

የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሁመራ ኤርፖርትን ተቆጣጣረ
**********************

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዘራፊው የህውሓት ቡድን ከጠላት ጋር ጥምረት በመፍጠር ለእኩይ አላማ ሊጠቀምበት የነበረውን የሁመራ ኤርፖርት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።

በርካታ ህውሓት ያደራጃቸው የልዩ ኃይል፣ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት ለመከላከያ ሰራዊት እጃቸውን እየሰጡ ነው።

ሰራዊቱ ዘራፊው የህውሓት ቡድን ያደረሰበትን ድንገተኛ ጥቃት በመመከት የመልሶ ማጥቃት ስራ እየሰራ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ከዳንሻ ጀምሮ በርካታ ቦታዎችን እየተቆጣጠረ እንደሚገኝ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያሳያል። 


Prime Minister Abhiy Ahmed has made new appointments

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዳዲስ ሹመቶችን ሰጡ
********************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የተሰጡት ሹመቶች የሚከተሉት ናቸው።

- አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
- ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም

- ሌ/ጄኔራል አበባው ታደሰ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም

- አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብሔራዊ መርጃና ድህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር

- ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር

አዳዲሶቹ ሹመቶች የሀገሪቱን የጸጥታና የደኅንነት ብሎም የውጭ ግንኙነት አካላትን በማጠናከር የተጀመረውን ሕግ የማስከበር ዘመቻ በአጭር ጊዜ በብቃት ለመወጣት የተደረገ የአመራር ሽግሽግ እንደሆነም ተገልጿል።
Prime Minister Abhisit Vejjajiva has made new appointments

 ********************


 The following are the appointments made by Prime Minister Abiy Ahmed since October 25, 2013.


 - Demeke Mekonnen Deputy Prime Minister and Minister of Foreign Affairs

 - General Berhanu Jula, Chief of Staff of the Armed Forces


 - Lt. Gen. Ababaw Tadesse, Deputy Chief of Staff of the Armed Forces


 - Ato Temesgen Tiruneh Director General of the National Relief and Security Service


 - Commissioner Demelash G. Michael, Federal Police Commissioner


 The new appointments are part of a leadership transition to strengthen the country's law enforcement and foreign relations.


Saturday, November 7, 2020

The Federal Government is working to uphold the rule of law in accordance with the country's constitution, the Prime Minister's Office said

የፌዴራል መንግስት በአገሪቱ ሕገ መንግስት መሰረት የሕግ የበላይነት የማስከበር ስራ እየሰራ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ገለጸ
********************************

 ህወሃት የአገሪቱን ሕገ መንግስት በመጣስ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የፌዴራል መንግስት በአገሪቱ ሕገ መንግስት መሰረት የሕግ የበላይነት የማስከበር ስራን እየሰራ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ገልጿል፡፡

አሁን ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ከሁለት ዓመታት በፊት ወደ ስልጣን መምጣቱን ተከትሎ አገሪቱን በሕግ ሳይሆን በጭቆና ለ27 ዓመታት ሲገዛ የነበረው ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራት /ህወሃት/ ሰላማዊ ዜጎችን እንደ ጋሻ በመጠቀም በመቐለ ከተማ ከፍትሕ ሸሽተው መቆየቱን ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡

ቡድኑ  ባለፉት ሁለት ዓመታት ለተለያዩ ቡድኖች ድጋፍ በማድረግ አገርን የማተራመስ ተግባር ላይ ተጠምዶ የነበረው ቢሆንም፣ የፌዴራል መንግስት ሁኔታውን በትዕግስት ሲከታተል መቆየቱ ተገልጿል፡፡

የፌዴራል መንግስቱ ህወሃት በአገሪቱ ውስጥ የተፈጠረው የሪፎርም አካል እንዲሆን የውይይት፣ የድርድርና የጋራ መግባባት እድሎች ተከፍተው ሁሉም የሰላም አማራጮች የተጠቀመ ቢሆንም ቡድኑ ባሳማራቸው የጥፋት ኃይሎች  አማካኝነት በምዕራብ ጎንደር፣ ሻሸመኔ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ቤኒሻንጉል፣ ጉራ ፈርዳ፣ እንዲሁም በቅርቡ በምዕራብ ወለጋ ጥቃት መፈጸሙን ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡

መንግስት በገለልተኛ አካላት በኩል ድርድር እንዲደረግ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም ህወሃት ሕገ ወጥ ምርጫ በማድረግና የፌዴራል መንግስቱን እንደ ሕገ ወጥ አካል በመቁጠር ለፌዴራል መንግስቱ እውቅና እንደማይሰጥ ገልጸ ነበር ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም ቡድኑ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መሰነዘሩን ተከትሎ የፌዴራል መንግስት የመከላከያ ሰራዊት ራሱን እንዲከላከል እንዲሁም በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ትእዛዝ ማስተላለፉ ተገልጿል፡፡

 በትግራይ ለ6 ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅም በኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሰብሳቢነት የሚመራና አግባብነት ካላቸው አካላት የተውጣጡ አባላት ያሉት ግብረ ኃይል በዚህ አዋጅ መቋቋሙ የተገለጸ ሲሆን፣ ግብረ ሀይሉ አስፈላጊ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ፦
• ፖሊስን ጨምሮ ማንኛውንም የፀጥታ ሃይል ትጥቅ እንዲፈቱ ማድረግ፣ 
• የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ጨምሮ አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸው ሌሎች እንቅስቃሴዎች 
ላይ ገደብ መጣል፣ 
• የሰአት እላፊ ገደብ የማውጣት፣ 
• የጦር መሳሪያ እንቅስቃሴዎችን የማስቆም፣
• የመገናኛ ዘዴዎች እንዲቋረጡ የማድረግ፣ እንዲሁም 
• ህገ ወጥ በሆነ ተግባር ላይ ተሳትፈዋል ብሎ የጠረጠራቸውን ግለሰቦችና ቡድኖች የመያዝና የማቆየት ኃላፊነት ይኖረዋል መባሉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡።

Curated Products for Generation X

https://amzn.to/3VhbwJz GenX Essentials - Curated Products for Generation X ...

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon