የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አስተካክለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment), የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViber ሆነ Whatspp ይደውሉልን። 619 255 5530 ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Tuesday, January 4, 2022

Large quantities of wheat and oil were purchased to stabilize market prices

የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት ከፍተኛ መጠን ያለው የስንዴና ዘይት ግዢ ተፈጸመ
******************
የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ከማስፍን አንጻር የዋጋ ግሽበትን የመቆጣጠርና የገበያ ዋጋን የማረጋጋት ፋይዳ ያለው የ4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴና የ12.5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት የመቶ ቀን እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በተካሄደበት ወቅት እንደተገለጸው ባለፉት ጥቅምትና ህዳር ወራት የ4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ግዥ  ተፈፅሟል፡፡  

ግዥ ከተፈፀመው ስንዴ ውስጥ አንድ ሚሊዮን ሀምሳ አንድ ሺ አንድ መቶ ስልሳ ኩንታል ስንዴ ወደ ሃገር ውስጥ የገባ ሲሆን ይህም የስንዴ ዋጋ ከፍ እንዳይል የራሱ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ነው የተገለጸው፡፡ 

ቀሪው ስንዴ በተቻለ ፍጥነት ተጓጉዞ ወደ ሀገር ውስጥ አንደሚገባም ታወቋል፡፡
በዚሁ ወቅት የ12.5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ግዢ ተፈጽሞ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት በሂደት ላይ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የምግብ ዘይትና ዱቄት ከውጭ በፍራንኮ ቫሉታ (አስመጪዎች በራሳቸው የውጭ ምንዛሪ) እንዲያስገቡ በመደረጉ የሸቀጦች ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል ማስቻሉም ተገልጽዋል፡፡

በጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም 34.2 በመቶ የነበረ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በህዳር ወር ወደ 33.0 በመቶ ዝቅ ብሏል ተብሏል። 

የሕዳር 2014 ወርሃዊ የምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ጥቅምት 2014 ጋር ሲነጻጸር በ1.8 በመቶ የቀነሰ ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት 1.0 ከመቶ የጨመረ መሆኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው  መረጃው  ያመለክታል፡፡
Large quantities of wheat and oil were purchased to stabilize market prices
 ******************
 The Ministry of Finance said it has procured 4 million quintals of wheat and 12.5 million liters of cooking oil, which is important for controlling inflation and stabilizing market prices.

 According to the Ministry of Finance and its affiliated institutions, 4 million quintals of wheat was procured last October and November.

 Out of the purchased wheat, one million fifty-one thousand one hundred and sixty quintals of wheat was imported, which is said to contribute to the increase in the price of wheat.

 It is learned that the rest of the wheat will be transported as soon as possible.
 Meanwhile, 12.5 million liters of cooking oil has been procured and is in the process of being imported.

 It is also stated that the importation of cooking oil and flour by Franco Valuta (importers on their own foreign exchange) has helped keep commodity prices stable.

 Total inflation fell to 34.0 percent in November 2014 from 34.2 percent in November 2014.

 According to the Ministry of Finance, inflation in non-food items increased by 1.0 percent in November 2014, while food inflation fell by 1.8 percent compared to October 2014.

Monday, January 3, 2022

New Year, New location

ከ20 አመታት የአንድ  ቦታ  ቆይታ  በኋላ  የቦ ወደ አዲሱ ህንፃ  ገብቷል። ለደንበኞቻችን  በቀላሉ  ለመገኘት  ብለን  አሁን  ያለነው  ከትልቅ አውራ ጎዳና  ፊት  ለፊት  ነን። የሳንድያጎ ከተማ  ነዋሪ ከሆኑ  እኛን  ለማኘት  አይቸገሩም። አሁን  ያለነው  ብዙ የከተማ  አውቶቡሶች ፌርማታ  አጠገብ  ስለሆነ  በመኪናም ሆነ  በአውቶቡስ  እኛ ጋር  ለመምጣት  እጅግ  በጣም  ቀላል ነው።  
ታዲያ በዚህ  አመት  አገልግሎታችንን በሰፊው  በመዘርጋት  ከሳንድያጎ  ውጭ  ያሉ  ደንበኞቻችንን  ለማገልገል  ቆርጠን  ተነስተናል። በተለይም  ደግሞ  የታክስ  ደንበኞቻችን  የትም  ግዛት  ቢኖሩ  እነሱን  ለማገልገል  ሁሉንም  ነገር አሟልተን  እንገኛለን።

After 20 years in one location, Yebbo have  moved into the new building.  We are now in front of a highway for easy access to our customers.   It is very easy to come by car or bus to us.
 So this year we are committed to expanding our service to serve our customers outside of San Diego.  In particular, we do everything possible to serve our taxpayers, no matter where they live.






 

The majestic life of the King of Laughter and the world record holder of Belachew Girma is in jeopardy.

የአለም የሳቅ ንጉሱና የጊስቡክ የአለም ሪከርድ ባለቤቱ የበላቸው ግርማ ህይወት አደጋ ላይ ነው እንድረስለት ።

ታዋቂው የአለም የሳቅ ንጉስና የደግነት አንባሣደር፣ በጊነስ ቡክ የተለያዩ የአለም ሪከርዶች ባለቤት የሆነው ማስተር  በላቸው ግርማ ባጋጠመው የጭንቅላት እጢ ሆስፒታል ገብቶ ቀዶ ጥገናውን በተሳካ ሁኔታ ቢያጠናቀቅም አሁንም ቢሆን ህይወቱ አስጊ ደረጃ ላይ ነው። የተሻለ ህክምና ያለበት ሀገር ሄዶ ህክምና ያገኝ ዘንድ ሁላችንም ልንረዳው ይገባል።

ይህ ከከምባታ ምድር የፈለቀው ኩሩ ኢትዮጵያዊ ሀገሩን በአለም መድረክ ላይ ብዙዎች በማይሳካላቸውና ከባድ በሆነው የአለም ድንቃድንቅ ተግባራት በሚመዘገቡበት Guines Book of World ላይ በተደጋጋሚ ሪከርዶችን በመስበርና ስሙን እና ሀገሩን በተደጋጋሚ ሰዓት ያስጠራ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ነው።

ሆኖም ግን አሁን በበሽታ ተጠቅቶ የአልጋ ቁራኛ ሆኗል ፤ ስለዚህ ይህን ኩሩ ኢትዮጵያዊ ለመርዳትና ለማገዝ ቅዳሜ ህዳር 5/2013 በSky Light Hotel ከቀኑ 9:00 ሠዓት ጀምሮ  የገቢ ማሰባሰቢያና የኪነ ጥበብ ዝግጅቶች ሊደረግለት በአብርሃም ግዛዉ ኢንተርቴመንት አዘጋጅነት ይካሄዳል።

ስለዚህ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የምትገኙ ዘመድ አዝማዱ ፣ ጓደኞቹ ፣ አድናቂዎቹ ፣ የመንግስት አካላት ፣ ባለሀብቶች እና ሌሎችም መርዳት የምትፈልጉ ወገናቹን ታግዙና ትረዱት ዘንድ በኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ አካዉንት ቁጥር 1000058068277 ማስተር በላቸዉ ግርማ ብላችሁ መርዳት ትችላላችሁ እሱን ለማግኘት በስልክ ቁጥር 0911244101 ወይም 0912374014 ይደዉሉ::
በአክብሮት እንጠይቃለን።
#ሼር በማድረግ መልዕክቱን ለሁሉም ያድርሱት

The majestic life of the King of Laughter and the world record holder of Belachew Girma is in jeopardy.

 The world-renowned laughter and benevolent ambassador, Guinness Book of World Records, has successfully undergone surgery on a brain tumor, but his life is still in danger.  We all need to help him get to a better country and get treatment.

 Born in Kembata, he is a proud Ethiopian who broke his record in the Guinness Book of World Records, one of the most unsuccessful and difficult events in the world.

 But now he is sick and bedridden;  Therefore, to help and support this proud Ethiopian, a fundraising and arts event will be held at the Sky Light Hotel on Saturday, November 5, 2013 at 9:00 AM hosted by Abraham Gizaw Entertainment.

 Therefore, relatives, friends, admirers, government officials, investors and others who want to help, both at home and abroad, can help him by contacting Oromia Cooperative Bank Account No. 1000058068277.
 We respectfully ask.
 # Share the message with everyone

A second round of repatriation program for Diaspora members from Italy was held in Turin

ከጣሊያን ወደ ሀገር ቤት ለሚገቡ የዳያስፖራ አባላት ሁለተኛ ዙር የሽኝት ፕሮግራም በቶሪኖ ተካሄደ
************************ 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለዳያስፖራው ያቀረቡትን ግብዣ ተቀብለው በጋራ ወደ ሀገር ቤት ለመግባት በዝግጅት ላይ ለሚገኙ በጣሊያን ቶሪኖ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሽኝት ፕሮግራም ተደርጓል። 

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳ ኢትዮጵያ በዓይነት እና በገንዘብ ሀገሩን የሚደግፍ እና አንዳንድ ምዕራባውያን በሀገሩ ላይ ለማድረግ የሚፈልጉትን ጫና እና ጣልቃ-ገብነት በድፍረት የሚታገል ጀግና የዳያስፖራ ኮሚኒቲ አላት ብለዋል። 

ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ከጊዜያዊ ችግሮቿ ቶሎ ለመላቀቅ አይተኬ ሚና እንዳለው አብራርተዋል። 

“እናንተ ሀገር እና ወገኑን ከዘርፈ ብዙ ተግዳሮት ለመታደግ የምትዘምቱ ዘማቾች ናችሁ፤ ስለሆነም ጉዟችሁ እስከዛሬ ታደርጉት ከነበረው ጉዞ የተለየ መሆን አለበት።” ሲሉም ወደ ሀገር ቤት ለመጓዝ ለተዘጋጁት ወገኖች ተናግረዋል። 

“በምትይዟቸው ሻንጣዎች የድጋፍ ቁሳቁሶችን ቅድሚያ ስጡ፣ ብራችሁ በሕጋዊ መንገድ ብቻ መመንዘሩን አረጋግጡ፣ በጦርነቱ የተጎዱትን ከቤተሰብ እኩል ጎብኙ፣ በአጠቃላይ በሚኖራችሁ ቆይታ እና በምታደርጉት እንቅስቃሴ ለሀገርና ወገን ድጋፍ በሚያስገኝ እንዲሁም የሀገራችንን ገፅታ በሚገነባ መልኩ ይሁን” ሲሉም አደራ ማለታቸውን ሮም ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። 

ዘማች የዳያስፖራ አባላት በበኩላቸው መንግሥት ባቀረበው ጥሪ መሠረት ወደ ሀገር ቤት በመግባት የደረሰውን ጥፋት በአካል በመመልከት በመልሶ ግንባታው የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚሄዱ ገልጸዋል። 

ወደ ሀገር በሚሄዱበት ጊዜም የተለያዩ መድኃኒቶች እና የሕክምና ቁሳቁሶች ይዘው ለመሄድ መዘጋጀታቸውን ነው የገለጹት። 

A second round of repatriation program for Diaspora members from Italy was held in Turin
 ***********************

 A reception was held for Ethiopians and Ethiopians of Ethiopian descent in Turin, Italy, who were preparing to enter the country together in response to Prime Minister Abiy Ahmed's invitation to the Diaspora.

 Ambassador Demitu Hambissa, who was present at the event, said Ethiopia has a heroic Diaspora community that supports the country in kind and financially and boldly fights the pressure and interference of some Westerners in the country.

 He said Ethiopia has an important role to play in getting rid of its temporary problems.

 "You are the ones who are fighting to save the country and its people from many challenges;  So your journey should be different from what you have been doing so far. ”  He told those who were preparing to travel home.

 "Priority should be given to luggage, ensure that your money is spent only legally, visit the victims equally as a family, during your stay and in your activities in a way that is supportive of the country and the country and builds the image of our country," according to the Ethiopian embassy in Rome.

 Campaign members of the Diaspora, for their part, said they would go to the country and play their part in rebuilding the dam at the invitation of the government.

 He also said that they are ready to carry various medicines and medical supplies on their way home.


ዳያስፖራው ለኢትዮጵያ ሕልውና ያደረገው ተጋድሎ ባንዳን ያስደነገጠና የኢትዮጵያውያንን አንድነት በተግባር ያሳየ ነው

ዳያስፖራው ለኢትዮጵያ ሕልውና ያደረገው ተጋድሎ ባንዳን ያስደነገጠና የኢትዮጵያውያንን አንድነት በተግባር ያሳየ ነው - አቶ አወል አርባ
*******************
"ዳያስፖራው ለኢትዮጵያ ሕልውና ያደረገው ተጋድሎ ባንዳና ጠላትን ያስደነገጠና የኢትዮጵያዊያንን አንድነት በተግባር ያሳየ ነው'' ሲሉ የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አወል አርባ ተናገሩ፡፡

ዳያስፖራው በአፋር ክልል በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት የደረሰባቸውን ግለሰቦችና ተቋማት በመደገፍ ረገድ እያደረገው ላለው አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በአፋር ክልል ርእሰ መዲና ሰመራ የዳያስፖራ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ሲሆን፤ በመድረኩም የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አወል አርባና የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለምን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡

ርእሰ መስተዳደሩ በዚህን ወቅት ዳያስፖራው በኢትዮጵያ ህልውና ዘመቻ አኩሪ ታሪክ መስራቱን ተናግረዋል፡፡

በ "#NoMore" ንቅናቄ ብርቱ ተጋድሎ አድርጋችኋል፤ ጫና ለማድረግ የሚፈልጉ አካላትን ደግሞ አሳፍራችኋል" ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡

ንቅናቄው ለባንዳና ጠላት ትልቅ ድንጋጤ የፈጠረና የኢትዮጵያውያንን አንድነት በተግባር ያሳየ ሁነት መሆኑንም ርእሰ መስተዳድሩ አንስተዋል፡፡

አሸባሪው ህወሓት በአማራና አፋር ክልሎች ሚሊዮኖች እንዲፈናቀሉ፤ በርካቶች በጅምላ እንዲጨፈጨፉ፣ ሴቶች እንዲደፈሩ ማድረጉንና በዚህም ኢትዮጵያ ጠልነቱን በተግባር እንዳሳየ ተናግረዋል።

የአፋር ህዝብ በአፋር በኩል ኢትዮጵያን ማፍረስ እንደማይቻል በተግባር ማረጋገጡን አንስተው፤ ኢትዮጵያውያን ለአገራቸው ህልውና ዳግም የአድዋ ተጋድሎ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

አፋርን በተለይም "ሚሌን ይዤ መደራደሪያ አደርጋለሁ' ያለው አሸባሪ ቡድኑ፤ የጸጥታ መዋቅሩ ከአፋር ህዝብ ጋር የእግር እሳት ሆኖበት ተመልሷል ብለዋል።

ድሉ በአገር ውስጥና የውጭ ኢትዮጵያውያን ርብርብ እንደተገኘ ሁሉ አሁንም በአገር ግንባታው ሌላ ድል መቀዳጀት ይጠይቀናል ብለዋል።

"ኢትዮጵያን በአፋር በኩል መቼም መንካት እንደማይቻል አረጋግጣለሁ" ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ፤ ኢትዮጵያዊነት እንደ ጃኬት የሚወልቅና የሚለበስ እንዳልሆነ ዳያስፖራው በተግባር አሳይቷል ብለዋል።

ዳያስፖራው ከዚህ ቀደም ሲያደርግ ለነበረው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አመስግነው፣ በቀጣይም በመልሶ ግንባታው አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ጠይቀዋል።

ለበርካታ ኢንቬስትመንት አማራጮች በታደለውና የቱሪስት መዳረሻዎች በተቸረው አፋር ክልል ኢንቬስት በማድረግ እንዲሳተፉና አገርና ወገን እንዲጠቅሙ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም በበኩላቸው ኢትዮጵያ የገጠማትን ፈተና እንደወርቅ ተፈትና እያለፈች ነው፤ በዚህም ትውልዱ ደማቅ ታሪክ እየፃፈ ይገኛል ብለዋል።

አሸባሪ ቡድኑ የፈጸመው ጭካኔ የተሞላበት ግፍና ያደረሰው ውድመት የባዕድ አገር ወራሪ እንኳ ይፈፅመዋል ተብሎ የማይገመት መሆኑን ጠቅሰው፤ "ያጋጠመንን ችግር ተጋግዘን ማለፍ አለብን" ነው ያሉት፡፡

ዳያስፖራው ወደ አገር ቤት መምጣቱ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ከመምጣታቸው በፊትም በየአገራቱ ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም ታሪክ የማይረሳው ታላቅ ጀብድ መፈጸማቸውን ተናግረዋል።

"ወደ አገር ቤት መምጣታችሁ ዜጎቻቸውን እንዲወጡ የሚወተውቱ ጠላቶችን ሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ ያጋለጠና ኢትዮጵያውያንን ያኮራ ነው" ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በአፋር ክልል በአካል መገኘታችሁ ለክልሉ መልሶ ግንባታ አሻራ ለማስቀመጥ የምትጀምሩበት አጋጣሚ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሐመድ እድሪስ የዳያስፖራው ማህበረሰብ ተሳትፎ ለአገረ መንግስት ግንባታ ስኬት ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ዳያስፖራው በአገሩ ጉዳይ ላይ ቀጣይነት ባለው መልኩ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

The nomination of commissioners to the National Consultative Commission has begun

The nomination of commissioners to the National Consultative Commission has begun
 ***************************

 The commissioners' recommendations were launched to the National Consultative Commission, which was established to help create national consensus.

 The suggestion is valid from today until January 6.

 The Speaker of the House of Peoples' Representatives, Tagesse Chafo, said 11 commissioners will be appointed to ensure the success of the national consultation, which plays a key role in putting Ethiopia on a strong footing.

 "Ethiopians need to actively participate in the success of the national consultation," he said.

 In addition to the Speaker of the House, the President of the Federal Court, the Speaker of the House of Federation, the Secretary General of the Council of Religious Institutions and civil society organizations have been established.

 He asked for suggestions on how to make the consultation more effective, and said it would be possible to do so from today.

 According to the FBC, submission forms can be found on the council's website.


ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የኮሚሽነሮች ጥቆማ ተጀመረ
**************************

ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ያግዛል በሚል ለተቋቋመው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የኮሚሽነሮች ጥቆማ ተጀመረ፡፡

ጥቆማው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥር 6 የሚቆይ ነው፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ መግለጫ የሰጡ ሲሆን ኢትዮጵያን በጠንካራ መሰረት ላይ ለማስቀመጥ ቁልፍ ሚና ያለው ሀገራዊ ምክክር ውጤታማ እንዲሆን 11 ኮሚሽነሮች እንደሚሾሙ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያውያን ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬት በንቃት መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል ያሉት አፈጉባኤው አጠቃላይ የኮሚሽነሮች ምርጫ ሂደቱ በአንድ ወር ከ15 ቀን ይጠናቀቃል ብለዋል።

ለውጤታማነቱ በአዋጁ ሥልጣን ከተሰጣቸው የምክር ቤቱ አፈጉባኤ በተጨማሪ የፌደራል ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊና የሲቪክ ማኅበራት የተካተቱበት አማካሪ ኮሚቴ መቋቋሙን ተናግረዋል።

ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችሉ ግለሰቦች እንዲጠቆሙ የጠየቁ ሲሆን÷ ከዛሬ ጀምሮ መጠቆም እንደሚቻልም ገልፀዋል።

የጥቆማ መስጫ ቅጾችን በምክር ቤቱ ድረገፅ ማግኘት እንደሚቻልም መግለፃቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

The community has donated over 2.4 billion birr in cash and over 971 million birr in kind to the Defense Forces

ህብረተሰቡ ለመከላከያ ሰራዊት ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብና ከ971 ሚሊዮን ብር በላይ የዓይነት ድጋፍ አድርጓል
********************

ለአገር መከላከያ ሰራዊት እስካሁን ከ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ እና ከ971 ሚሊዮን ብር በላይ የአይነት ድጋፍ በህዝቡ መደረጉን የአገር መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ የኀብረተሰቡን ድጋፍ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ ጫፍ አንድ በመሆን ለሰራዊቱ ያላቸውን ደጀንነት በተግባር አሳይተዋል ብለዋል።

የህልውና ማስከበር ዘመቻው ከተጀመረ እስካሁን ድረስ ለሰራዊቱ 971 ሚሊዮን 500 ሺህ ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ ከህዝቡ መደረጉን ተናግረዋል።

ይህም ኢትዮጵያዊያን ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነት በተግባር ያረጋገጠ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡

ለሰራዊቱ ገቢ ማሰባሰቢያ በተከፈተው የባንክ አካውንት ከ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡   

"ይሄን መግለጫ እስከምሰጥበት ጊዜ ድረስ 2 ቢሊዮን 41 ሚሊዮን 155 ሺህ 16 ብር በመከላከያ ሚኒስቴር ማዕከል በተከፈተው 1000421912134 አካውንት ቁጥር ገቢ ተደርጓል" ብለዋል።  

በ6800 አጭር የጽሁፍ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያም ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል።

በዚህም ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ነው የተናገሩት።    

የኢትዮጵያ ህዝብ ለሰራዊቱ በተግባር እያሳየ ያለውን ደጀንነት አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
The community has donated over 2.4 billion birr in cash and over 971 million birr in kind to the Defense Forces
 ********************

 The Ministry of Defense said over 2.4 billion birr in cash and over 971 million birr has been provided to the public so far.

 State Minister for Defense Martha Luigi said in a statement that Ethiopians have shown solidarity with the army.

 He said 971 million birr has been provided to the army so far.

 He said this confirms the Ethiopians' partnership with the Defense Forces.

 He said over 2.4 billion birr cash has been donated to the army's bank account.

 "As of this writing, 2 billion 41 million 155 thousand 16 birr has been deposited in the account number 1000421912134 opened at the Ministry of Defense," he said.

 He also mentioned that he has supported more than 200,000 citizens with 6800 text messages.

 He said more than 500 million birr has been collected.

 ENA also called on the Ethiopian people to continue their support for the army.

check

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon