Shop Amazon

Thursday, March 13, 2014

የሱዳኑ እርአይ

የሱዳኑ እራይ
" የባሰ አለ ቤትህን  አትፍታ" ይላል ያገሬ ሰው። ያው ያለነው ስደት ነውና ከሌሎች አገር ስደተኞች ጋ መዋል ያለ ነው። በቃ የእድል ነገር ሆኖ ከሱዳን ወንድሞች እና እህቶች ጋር በጣም እንግባባለን። ታዲያ አንዱ የዳርፉር (Darfur ) አካባቢ ሱዳን ያለኝን ላውጋች ሁ። እሱ የሚለው ይህንን የሰማው ድሮ  ከታወቁ የሱዳን ፕለቲከኞች ነው። በዚህ ግለስብ አገላልጥ ሱዳን ለአራት ትከፋፈላልች። ምስራቅ ሱዳን፣ ምራብ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና ሰሜን ሱዳን። ሁሉም እራሳቸውን የቻሉ አገሮች ይሆኑና ትንሽ ቆይተው ግማሹ ከኢትዮጵያ፣ ግማሹ ደግሞ ከኤርትራ ጋር የቀረው ደግሞ ከግብጽ ጋር ይዋሃዳል። ታዲያ የወደፊቱ የኢትዮጵያ ካርታ ምን ይመስል ይሆን? ድሮ ጀበና ይመስል ነበር፣ ክዚያ አንገር የሌለው ጀበና ሆነ::  ሁሉም በያለበት እገነጠላለሁ እያለ ሲያስፈራራን ዛሬ ደግሞ እዋሃዳለሁ የሚለውን ወሬ አሰማን። ታዲያ በኔ ግምት የወደፊቷ የኢትዮጵያ ቅርጽ ማጨድ ሳይሆን ይቀራል? የእርስዎን ደግሞ ልስማው::

No comments:

Post a Comment