Shop Amazon

Sunday, May 24, 2015

የተወዳዳሪ ፓርቲዎች የምርጫ አስተያየት

የተወዳዳሪ ፓርቲዎች የምርጫ አስተያየት

ዛሬ ድምፃቸውን ለመስጠት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የሄዱ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንደገለፁልን፤ ድምፃቸውን በሰላማዊ መንገድ መስጠት ችለዋል። ሆኖም አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲ ተጠሪዎች እንደገለፁልን ግን የተቃዋሚ እጩዎቹ በሚሳተፉበት የምርጫ ጣቢያዎች በታዛቢነት በመደቧቸው ሰዎች ላይ ጫና ሲደረግ ተስተውሏል።
የሰማያዊ ፓርቲ ምክትክ ሊቀመንበር እና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሺ ፈይሳ የዛሬውን ምርጫ አስመልክቶ ሰማያዊ ፓርቲ በተወዳደረበት ቦታ ሁሉ ፤ የምርጫ ታዛቢዎቹን መልምሎ ቢመድብም ፤ ታዛቢዎቹ ከፍተኛ ጫና እንደገጠማቸው ገልፀውልናል።
ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፤ ዶ/ር መራራ ጉዲና የትውልድ ቦታቸው ከሆነው የአምቦ ከተማ ሆነው የታዘቡትን እንዲህ ሲሉ ለዶይቸ ቬሎ ገልፀዋል።
የመኢአድ ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሐሪ ደግሞ ምርጫውን ሁለት ቦታ ከፍለው ነው የሚመለከቱት። በአዲስ አበባ እና በክፍለ ሀገር ደረጃ ብለው።
ገዢው ፓርቲ ኢሀዲግ የዛሬውን ምርጫ እንዴት እንደገመገመው ለመጠየቅ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የህዝብና የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደስታ ተስፋውን ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረግነው የስልክ ጥሪ፤ ስብሰባ ላይ እንደሆኑ ተነግሮን ምላሽ ሳናገኝ ቀርተናል። እንዲሁ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ፤ አቶ ሬድዋን ሁሴን መልሰን እንድንደውል በቀጠሩን ጊዜ ስልኩን ሳያነሱት በመቅረታቸው፤ ከመንግሥት በኩል እንዲሁ አስተያየት ሳናገኝ ቀርተናል።
ልደት አበበ
አርያም ተክሌ

No comments:

Post a Comment