Shop Amazon

Friday, November 9, 2018

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሶማሊያ አቋርጦት የነበረውን በረራ ከ41 ዓመታት በኋላ ዳግም ጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሶማሊያ አቋርጦት የነበረውን በረራ ከ41 ዓመታት በኋላ ዳግም ጀመረ
********************************************************************************

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ሶማሊያ ላለፉት 41 ዓመታት አቋርጦት  የነበረውን  በረራ ዳግም ጀመረ፡፡

አየር መንገዱ በሶማሊያ በነበረው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት በረራውን አቋርጦ እንደነበር የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም አስታውቀዋል፡፡

አየር መንገዱ በአገሪቱ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሞቃድሾ ይፋዊ በረራ መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡

ይህም ለሶማሊያዊያን አየር መንገዱን በመጠቀም  ከቀሪው አለም ጋር ለመገናኘት በር እንደሚከፍትላቸው አመልክተዋል፡፡

ለሶማሊያ መልሶ ግንባታና ለኢትዮጵያና ሶማሊያ ህዝቦች የቀደመ ትስስር መጠናከርም የበረራው መጀመር ፋይዳው የጎላ መሆኑን አቶ ተወልደ ተናግረዋል፡፡

አየር መንገዱ ዳግም በረራ የማስጀመር ስነ ስርዓቱ ዛሬ ማለዳ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በይፋ አብስሯል፡፡

በአባይነህ ጥላሁን

No comments:

Post a Comment